#እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽሙ በዓል ጥር ፲፰ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል።
ዐመዱን ሰው የሚያደርግ አምላክ አለኝ
ስባረ አጽሙ ዘገበዘ ኢትዮጵያ - ሰባር አጥሙ
ሞትን እንደ ጎዳና የተመላለሰበት። ብዙዎችን በማስደንገጥ ዝና የገነባውን ሞትን ራሱን ያስደነገጠ። ሞተልን አበቃለት ሲሉት በእግዚአብሔር ኃይል ከሞት እየተነሣ ገዳዮቹን ያብረከረከ። ቤሩታዊትን ከገዳዩ ደራጎን መንጋጋ ፈልቅቆ ያዳነ።
ኢትዮጵያንም ከዋጠው ሰልቅጠው ፋሺስቶች የታደገ። ገበዘ ኢትዮጵያ ቅዱስ ጊዮርጊስ!
በጋለ ብረት ምጣድ በድኝ እሳት አቃጥለው አጽሙን በመንኮራኩር (በወፍጮ) ፈጭተው ደሞ እንዳይነሣ ብለው የተፈጨውን አጽሙን በደብረ ይድራስ በተኑት።
እግዚአብሔር መጣ። ነፋሳት ሆይ የወዳጄን የጊዮርጊስን አጽም ሰብስቡልኝ አለ። ቅጠሎቹ ሁሉ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ እያሉ ተውለበለቡ። ከሞት አስነሣው።
እርሱም ቀጥ ብሎ ወደ ገዳዩ የሮማ ንጉሥ ገሰገሰ። አንተ ጊዮርጊስ ነህን? ቢለው አዎ ነኝ ብሎ መለሰለት። ዐመድ አድርገን ፈጭተን በትነንህ አልነበረምን? አለው። አዎ አለ ቅዱስ ጊዮርጊስ። እንዴት ተነሥተህ መጣህ? ቢለው:-
ዐመዱን ሰው የሚያደርግ አምላክ አለኝ ሲል መልሶለታል።
እንኳን ለገበዘ ኢትዮጵያ ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ስባረ አጽሙ አደረሳችሁ !!!
ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo.