ፍኖተ ብዕር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"እኔስ ኖሬዋለሁ ሲከፋኝ ሲደላኝ
ከእንግዲህ ተወልዶ ሰው ለሚሆን ይብላኝ "
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ሰው
መጣ
ሰው
መጣች
ሁሉ ሞላ
ፍቅር ጎላ
ሰው
መጣ

እንዲያድግም ሆነ
ህይወት ወ ቅዠቱን
ተማረ
መረመረ
በእውቀት መነነ
ከሱ ላላወቀው መከታ እንዲሆን
አደራ ተሰጠው ወሰደ ስያሜን
ሰው

በጠባዩ ተራቆ
በእውቀቱ ልቆ
ካለማወቅ ተላቆ
ከአዕምሮ ፅልመት ተሸሽጎ ርቆ
መንደሩን ባኮራ በአንድ ብላቴና
ሰው ዘር ተማመነ ተመካ በጠና
ህዝብ
እምነቱን ሰጠ
ለውጥ አለመ ቋመጠ
ጉጉቱም ፈጠጠ

የመንደር ልጅ የቤት ኩራት
ተሰናድቶ ሊሆን መብራት
ሊቅለጠለጥ ታጥቆ ሰርቶ
ሊያተረፈርፍ ትጋት ሞልቶ
ያሸለበም እንዲያነቃ
የፈዘዘም እንዲያበቃ
ሰነፍ ሊሆን እንደ ብርቱ
ተስፋ ሆኖ መድሀኒቱ
እንዲጠግን እንዲሰራ
እንዲያኮራን እንድንኮራ
ተቀባ የተማረ
ተሰየመ ላቅ ተብሎ ተመከረ
ሁሉም ከሚያውቀው ጫፍ
ከበስትያ በኩል ቀጭን መስመር ሰራ
በመስመሩም እጅግ ኮራ

እናም አለ
ስያሜ እና ሙገሳቹ
ቀለም እና ቅባታቹ
መከታና መሸሻቹ
እውቀት እና መላቃቹ
ሁሉን
ስጡኝ
አደራም
ይሁነኝ

ያስቸገረ ያደከመ ውስብስብ ስጋታቹ
በእኔ እውቀት በእናንተ ክንድ
ተመልሶ እንዳይመጣ
ጉድጓድ ምሰን እንቀብራለን
እንደንቃለን ላንደነቅ
እንልቃለን ላንሳቀቅ
እንቆማለን ፍፁም ላንወድቅ

ደግሞሞ እንዲህ አለ
እንደክር ህዋስ ነን
ማንም አይሰነጥቅ አይነጣጥለነ
ፍቅርችን ቋሚ ነው ጊዜ አይለውጠነ
ብሎ እንዳበቃ
ህልም ውጥኑን አሳካ
ስኬቱንም ትውልድ ለካ
ሞላ
በስራውም እጅግ ረካ

እናም
ዛሬ
ሰው
ደከመ
ጉብዝናውም
ጠየመ
አበቃ አረፈ
ዛሬን ወ ነገን አስተቃቅፎ አለፈ
እሱ ሄደ
ነጎደ
ሳራው ቆመ ተሰለፈ
ተስፋ ሞላ ተረፈ

የመንደር ልጅ የቤት ኩራት
አጠናቁአል ሆኖ መብራት
ሰው
አረፈ
አለፈ

@Ribka Sisay
March 30,2009
12:30am


Belay Bekele Weya
ሲቀርፁ መዶልዶም
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በጥይት እርሳስ ጫፍ...
የተሳተ ስህተት ፣ በላጲስ ባይጠፋም
ቢቀርፁት መዶልዶም...
በሆነ የእርሳስ ህግ ፣ ያጥራል እና ተስፋም
ሁለት ምርጫ የለም
ጨለማ ብርሃኑን
ኑሮኖ አፈሩን ፣ ሰው እኩል አይገፋም፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡
ዘጠኝ ሞት ቢመጣ ፣ ሰው አንዱን ይመርጣል
ሰው አንድ ሞት ሲመርጥ ፣ ስምንት ሞት ያመልጣል
ሁለት ምርጫ የለም
መይ ወድቆ ማንሳት ነው ፣ ወይ ተነስቶ መጣል!!!
።።።።።።
@quoteseverr


Belay Bekele Weya
አንድ ቀን ፍለጋ ፣ አንድ ዘመን ጥሎ
አይሆኑትን ሆኖ ፣ አይችሉትን ችሎ
ማለፍ በጎ አይደለም ፣ ለበጎ ነው ብሎ!
።።።
ለበጎ ነው እያልን
ምናልፈው መጥፎ አካል ፣ ጥሩ መልክ አይሰጥም
ፍቅርም ህግ አለው !
ምህረት እያበዛ ፣ በጥላቻ እስኪረክስ አይለማመጥም
ብርሀን የሚነግድ
ጨረቃን ለማትረፍ ፣ ፀሐይን አይሸጥም!!!
።።።።
@quoteseverr


Belay Bekele Weya
"ፈጣሪ ነው እንጂ ፣ ሰው በሰው አይፈርድም "
ብለው በሚሰብኩኝ ፣ ሰዎች ብናደድም
ሰዎች ፈርደውበት
የተሰቀለ አምላክ ፣ ሰዎችን ይወዳል
ፈጣሪ ዝም ሲል ፣ሰው በሰው ይፈርዳል።
።።።
እኔ ግን እላለሁ!
የሰው ልጅ ነው እንጂ ፣ አምላክ ፍርድ አያውቅም
በበደሎች ሁሉ...
የማይሸነፍ ነው ፣ የቸርነቱ አቅም፡፡
፡፡፡፡
ከሐጢያቶች ሁሉ ፣ ምህረቱ ያይላል
እኛ "ፍረድ" ስንል ፤ እርሱ "ይቅር" ይላል።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አናም እኔ ለኔ...
የማንጎራጉረው ፣ አንድ ዘፈን አለኝ
ፍርዱ ቢለያይም
ይቅር ብሎ ማለፍ ፣ ፍርድ ነው መሠለኝ!"
@quoteseverr


ያማል!
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ
ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶብሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የዕንባ ቅጥልጥሉ
ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ
እና እንደ ነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ
ጨጓራ በገነ
እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ
እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ
እና እንደ ነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል…??
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፑችኖ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን ባንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ? ይላል
አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ?
አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል?
ከጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል
የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት
እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደ ነገርኩሽ
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረ መጣ
ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት
እ. . . .ና. . . .ቷን !
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ
ግን አንቺን ስወድሽ
ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል !!!!
* * *
© ሰለሞን ሳህለ
# Solomon Sahele - ጫፍ ላይ ወራጅ የለም
@quoteseverr




@:የአላማጣ ቆንጆ
አቤት
@:ሳልፍ እንኳን አይቼሽ ልቤ የራደልሽ
@:ተኳሽ እንዴት ችሎ ቃታውን ሳበብሽ?
@quoteseverr




ለግላችን የቆየ ፍቅር እናካፍለው ዘንድ ደስታው ትልቅ ይሆናል።

እኛ ባለንበት ሰላም
መዋደድ
መከባበር
መተሳሰብ
መደማመጥ እንዲሁም ከምንም እና ከየትኛውም ሁኔታ ጋር ውስንነት የሌለውን ፍቅር እንካፈል ዘንድ እንበርታ።

በፍቅር ሁሉም ነገር ቀላል ነው።
ፍቅር ካመንበት በቂ ነው።

ሰላም ቤተሰብ
ርብቂ
@quoteseverr


ለምንድነው መኖር የደከመህ??

ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ?
ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም
ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ?
አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ
ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም
ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው
በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም
ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ፡
☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ
ታስፈልገናለህ፡፡
ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ
ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን
ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡
እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡
አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ
ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው
ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ
ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል
መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ
መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ
መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው
ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን
አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት
አትቸኩል ኢኼ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት ሞክር ማለት ነው፡፡
ታሪክህን ፃፍ እናንብህ፡፡
መልካም ኑሮ
@quoteseverr


ዝም እንበል
አብረን ዝም እንበል
(ጸጋዬ ገብረመድኅን)
ከሰው መንጋ እንገንጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።
ምነው አዋሽ ማዶ፣ ቆቃ ሸለቆው ግርጌ ሸሽተን
የቆቃን ሰቆቃ ሰምተን
ሲቃውን ሲሰብቀው አይተን
ሰቀቀኑን ተወያይተን
የምሽት ጀምበር ቢውጠን ….
ውኃ እንደ ዱታ ሲተምም፣ በድን ሸለቆ ሲናገር
በሰማይ ፈረስ ተጭኖ ከአጽናፍ አጽናፍ ሲንደረደር
ሲያጉተምትም ሲያስገመግም ባይነ ህሊና ለመመስከር
ሳንጨነቅ ሳንገደር
ለምንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር
ከዐይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር
አዋሽ ማዶ አብረን እንውረድ
አጉል ነው ብለን ሳንፈርድ
ድንቅም ነው ሳንል ሳንወድ
ዝም ብለን አብረን ብንወርድ…
ከሰው መንጋ ተለይተን
ከጠረኑ ተነጥለን
ከጉምጉምታው ተገንጥለን፣ ከኳኳታው ብንከለል
ከላንቃው ከድምፁ ሸሽተን በእፎይታ ጥላ እንጠለል
በቆ ይታ በጸጥታ ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።
መቼስ አይሆንም ካልሽ ቅሪ
ግዴለም አትገደሪ
ልቦናሽ በመተረልሽ ባሳደረብሽ እደሪ
ተስፋ መቀነን ነው መቼም
የሰው ልብ አይችለው የለም።
ብቻ ዳግመኛ ሞት ሳንሞት፣ አዲስ ቀን ሳይጨልምብን
ድፍን ደመና ሳይቋጥር፣ ክረምት ውርጅት ሳይወርድብን
ኮከባችንን ሳንጠራ፣ ሳንቆጥርባት ሳትቆጥርብን
ሞራችንን ሳናስነብብ፣ ሳናሳያት ሳታይብን
ጨረቃን መስክሪ ሳንል፣ ሳናውቅባት ሳታውቅብን
አዋሽ ማዶ ቆቃ በረን፣ እባክሽ ጀምበር ትጥለቅብን።
ውኃ እንደ ዱታ ሲተምም፣ በድን ሸለቆ ሲናገር
በሰማይ ፈረስ ተጭኖ፣ ከአጽናፍ አጽናፍ ሲንደረደር
ሲያጉተምትም ሲያስገመግም፥ ባይነ ህሊና ለመመስከር
ሳንጨነቅ ሳንገደር
ለማንም ምንም ሳናዋይ፣ ሳንናገር ሳንጋገር
ከዐይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር።
ከሰው ኳኳታ እንነጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።
@quoteseverr


© ዕድል ©
ልጅ (Petros)
.
እናቴ አድምጭኝ ~ ልጠይቅሽ አንዴ፣
አዋለዱኝ ያልሽው ~ እኒያ እማማ ውዴ፤
በጥሰው የጣሉት
እትብት መስሏቸው ~ ዕድሌን ነው እንዴ?
@quoteseverr


ማመልከቻ ቀን 2/7/1888 ዓ.ም
ለፌዴሬሽን ም/ቤት
"አዲሳባ"
ጉዳዩ :-ብሄር መሸጥን ይመለከታል
እኔ አመልካች አበበ ተክላይ መገርሳ በኖርኩበት ደብረ ብርሃን ከተማ (በከፋፍለህ ግዛው ቋንቋ) የኔን አማራነት የአባቴን ትግሬነት የአያቴን ኦሮሞነት ያለማወላዳት ተቀብዬ ለ21 ዓመታት መኖሬ ይታወቃል።ነገር ግን በብዙ ትግል የገነባሁትን ዘረኛ አስተሳሰቤን የሚቃወሙ እንደ በላይ በቀለ ወያ አይነት ፀሀፍት እንደ ለማ አይነት ፖለቲከኞች ጠዋት እና ማታ የደከምኩበት ልፋቴን መና ሊያስቀሩብኝ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ግልፅ ነው ።እናም አሁን ባለኝ አቅም ትጥቅ አልፈታም ብሎ መፈራገጡ ሰማይን የመግፋት ያህል እየሆነብኝ እንደሆነ ታውቆልኝ ከተቻለ ያለ ጦርነት 3ቱን በአንድ ኢትዮጵያዊነት የሚቀይርልኝ ይሄ ካልተቻለ ደግሞ መከላከያ ሰራዊቱ ቤተ መንግስት ድረስ ሄዶ እንዲሸጥ እና በስም ያልጠቀስኩትን የቅ.አያቴን ንብረት የሆነውን ኢትዮጵያዊነቴን ከንፁህ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቄ ጋር እንዲያስመልስልኝ ስል ጥርሴ እየሳቀ ውስጤ እያረረ በአክብሮት እጠይቃለሁ: ሁለት ነጥብ
ፊርማ
አበበ ተክላይ መገርሳ
@quoteseverr


stay strong
Stay positive
NEVER GIVEup
@quoteseverr


ሃቅ ያንቃል...!
(ሰለሞን ሳህለ)

እውነት አይበጠስ
ሲስቡት ይቀጥናል
የሆነውን አይቶ
ልባችን መዝግቧል
የህጻናት እንባ
ያዛውንቶች ጩኅት
በሰማይ ይሰማል
ታሪክ እንደ ፍጡር
ራሱን ይወልዳል
በቅኑ የሰራ
በቀኑ ይካሳል
በቀኑ ያጠፋም
በቀኑ ይቀጣል።
ሃቅ ያንቃል!!!
@quoteseverr


(በላይ በቀለ ወያ)
ሳልነግርሽ...

አፍቅሬ እንዳጣሁሽ…
በነብያቶች አፍ፣
ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ…
ጎትቶ ጎትቶ ፣
በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ
ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡
በሰባራ መርፌ….
ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ…
ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡
………………………………….
ሳልነግርሽ…
የኔ አለም ያላንቺ ፣እንደሆነ ራቁት
ባንቺ እንደነበር ፤ ቀንና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡
እንደተለየሽኝ …
አለም ባዶ ሆና ፣ መኖር እንዳስጠላኝ
ፍቅርሽ እከክ ሆኖ…
በልቤ ተተክሎ ፣ ነፍሴን እንደበላኝ፡፡
…………………………………
ሳልነግርሽ….
የነብያት ትንቢት ፣ በኔ መፈፀሙን
‹‹ታምሪያለሽ ›› እያልሁኝ ፣ ‹‹ተአምር ›› ማክተሙን
የተለየሽኝ ለት…
ምፅአት መምጣቱን ፣ የኔ አለም መቆሙን፡፡
…………………………………………
ሳልነግርሽ….
ካጣሁሽ በኋላ….
ባለፍኩት ጭንቅ ዓለም ፣ የስቃዬን መአት
አፍቅሮ ማጣት ነው…
በሰባራ መርፌ፣
እውነትን መስፋት ነው ፣ ለካንስ ምፅአት፡፡
@quoteseverr


ለሴቲቱ
የምሽት አፍቃሪ በዳይ የኔ ሚላት
ቀሚሷን ካላየ ቅኔ ማይፈታላት
፨ይቺ ድንግል ጠረን፨
÷የነጭ ሞት፦፡ሽታ ፤የጥቁር ሠው፤ አቅም÷
፡፡ውሽማ ነው እንጂ ባል ኖሯት አያውቅም።
©....ምናልባት ግን አሁን....©
ሰሙ
@quoteseverr




አንዳንድ ግዜ ምናለ ህይወት አማርኛ ፊልም ላይ እንዳለው ቀላል ቢሆን ብዬ እመኛለሁ፡፡ ... በቃ አለ አይደል የሆነች የሀብታም ልጅ መንገድ ላይ የመኪና ጎማዋ ተበላሽቶባት ጎማዋን ስለሰራህላት በፍቅርህ ብትወድቅ... ... በቃ አለ አይደል ተከራይተህ የምትኖርበት ቤት ኮርኒስ ውስጥ አይጥ ለመግደል ስትገባ የተደበቀ 300ሺ ብር አግኝተህ ከተማውን በአንድ እግሩ ማቆም ብትችል... ... በቃ አለ አይደል ኑሮ መሮህ ጎዳና ተዳዳሪ ስትሆን የሆነች የሀብታም ልጅ ጎዳና ላይ የተኛህበት የአተኛኘት ስታይልህ ተመችቷት በፍቅር ብትንበረከክልህ... ... በቃ አለ አይደል ከአንድ ቦዘኔ ቻይናዊ ጓደኛህ ጋር በመሆን የሰፈርህን ሰው በሙሉ ሰብስበህ መንገድ ልንሰራላችሁ ስለሆነ ብር አዋጡ ስትላቸው ያለምንም ቅሬታ ያለ የሌለ ገንዘባቸውን አዋጥተው በከረጢት ቢያስረክቡህ... ... በቃ አለ አይደል አንተ ተጎሳቁለህ ስትኖር የሆኑ ከውጪ የመጡ ዲያስፖራዎች የቤትህን በር አንኳኩተው "አባትህ ከመሞቱ በፊት ያስቀመጠልህን የሀምሳ ሚሊዮን ብር ውርስ ልንሰጥህ ነው የመጣነው" ምናምን ብለው በደስታ ጮቤ ቢያስረግጡህ... ... በቃ አለ አይደል አንዳንዴ ምናለ ህይወት እንደ አማርኛ ፊልም አስማት ቢሆንልኝ ብዬ እመኛለሁ፡፡ እስቲ አሜን በሉ ህይወታችሁን እንደ አማርኛ ፊልም የተአምር ህይወት ያድርግላችሁ፡፡
@quoteseverr


ዕድሌ ነው...
(መላኩ አላምረው)
.
ዕድሌ ነው...
በሚስት ልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤
ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድም ሴት አትገኝ
.
ዕድሌ ነው...
እኔ ዲግሪ ስይዝ፣ ዲግሪ ዋጋ ያጣል፤
ገንዘብ ያለው ሁሉ፣ ዶክትሬት ያመጣል
.
ዕድሌ ነው...
እኔ መድረክ ስይዝ፣ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ፣ ይሆናል ትንሣኤ።
.
ዕድሌ ነው...
በቁርባን ለመኖር፣ ንሰሐ ስገባ፤
አቁራቢው ፖትልኮ፣ ቤተመንግሥት ገባ።
.
ዕድሌ ነው...
እኔ ኳስ ስገዛ፣ ሜዳው ይታረሳል፤
እኔ ቤት ሲኖረኝ፣ ሰፈሬ ይፈርሳል።
.
ዕድሌ ነው...
ለተሾመ ሁሉ፣ እንዳልኖርሁ ስለፋ፤
እኔ አለቃ ስሆን፣ የሚታዘዝ ጠፋ።
.
ዕድሌ ነውና...
ከዕለታት አንድ ቀን፣ መንገሤ ባይቀርም፤
እኔ ንጉሥ ስሆን፣ ሀገሪቱ አትኖርም።
@quoteseverr

Показано 20 последних публикаций.

154

подписчиков
Статистика канала