(በላይ በቀለ ወያ)
ሳልነግርሽ...
አፍቅሬ እንዳጣሁሽ…
በነብያቶች አፍ፣
ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ…
ጎትቶ ጎትቶ ፣
በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ
ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡
በሰባራ መርፌ….
ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ…
ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡
………………………………….
ሳልነግርሽ…
የኔ አለም ያላንቺ ፣እንደሆነ ራቁት
ባንቺ እንደነበር ፤ ቀንና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡
እንደተለየሽኝ …
አለም ባዶ ሆና ፣ መኖር እንዳስጠላኝ
ፍቅርሽ እከክ ሆኖ…
በልቤ ተተክሎ ፣ ነፍሴን እንደበላኝ፡፡
…………………………………
ሳልነግርሽ….
የነብያት ትንቢት ፣ በኔ መፈፀሙን
‹‹ታምሪያለሽ ›› እያልሁኝ ፣ ‹‹ተአምር ›› ማክተሙን
የተለየሽኝ ለት…
ምፅአት መምጣቱን ፣ የኔ አለም መቆሙን፡፡
…………………………………………
ሳልነግርሽ….
ካጣሁሽ በኋላ….
ባለፍኩት ጭንቅ ዓለም ፣ የስቃዬን መአት
አፍቅሮ ማጣት ነው…
በሰባራ መርፌ፣
እውነትን መስፋት ነው ፣ ለካንስ ምፅአት፡፡
@quoteseverr
ሳልነግርሽ...
አፍቅሬ እንዳጣሁሽ…
በነብያቶች አፍ፣
ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ…
ጎትቶ ጎትቶ ፣
በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ
ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡
በሰባራ መርፌ….
ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ…
ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡
………………………………….
ሳልነግርሽ…
የኔ አለም ያላንቺ ፣እንደሆነ ራቁት
ባንቺ እንደነበር ፤ ቀንና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡
እንደተለየሽኝ …
አለም ባዶ ሆና ፣ መኖር እንዳስጠላኝ
ፍቅርሽ እከክ ሆኖ…
በልቤ ተተክሎ ፣ ነፍሴን እንደበላኝ፡፡
…………………………………
ሳልነግርሽ….
የነብያት ትንቢት ፣ በኔ መፈፀሙን
‹‹ታምሪያለሽ ›› እያልሁኝ ፣ ‹‹ተአምር ›› ማክተሙን
የተለየሽኝ ለት…
ምፅአት መምጣቱን ፣ የኔ አለም መቆሙን፡፡
…………………………………………
ሳልነግርሽ….
ካጣሁሽ በኋላ….
ባለፍኩት ጭንቅ ዓለም ፣ የስቃዬን መአት
አፍቅሮ ማጣት ነው…
በሰባራ መርፌ፣
እውነትን መስፋት ነው ፣ ለካንስ ምፅአት፡፡
@quoteseverr