ጌታ ሆይ! አስተምረን! (ክፍል አንድ)
“አስተማሪህ ከእንግዲህ አይሰወርብህም፤ ዐይኖችህም አስተማሪህን ያያሉ። ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል” - ኢሳ. 30:20 - 21
ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት “ጌታ ሆይ አስተምረን” በሚል ርእስ ስር ተከታታይ ሃሳቦችን አጋራችኋለሁ፡፡
መኖር እስካለን ድረስ ማደግ የግድ ነው፡፡ ለማደግ ደግሞ ዋነኛው መንገድ መማር ነው፡፡
አስተማሪያችን እግዚአብሔር ነው፡፡ ጌታችንን እና መድሃኒታችንን ኢየሱስን መከተል ከጀመርን ጀምሮ በብዙ መልኩ ያስተምረናል፡፡ ጌታ እንዲያስተምረን ግን በትህትና እና በተማሪነት መንፈስ በመቅረብ፣ “አስተምረኝ” ልንለው ይገባል፡፡
በሕይወታችን ትክክለኛው መስመር ውስጥ እድንገባ ጌታ እንዲያስተምረን ልንጠይቀው የሚገባንን ነገሮች ከቃሉ ባገኘነው መመሪያ መሰረት አንድ በአንድ እንመለከታለን፡፡
ዛሬ የማካፍላችሁ፣ “መጸለይን አስተምረን” የተሰኘውን ይሆናል፡፡
“ጌታ ሆይ . . . መጸለይን አስተምረን” - ሉቃ. 11:1
ይህንን ትምህርት እንዲያስተምረን ጌታን የምንጠይቀው፣ በአንድ መልኩ “ጸሎትን የመጸለይን ልማድ የማዳበርን” ትምህርት እንዲያስተምረን ሲሆን፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ስንጸልይ እንዴት መጸለይ እንዳብን እንዲያስተምረን ነው፡፡
“በሁሉ ዐይነት ጸሎት” (ኤፌ. 6፡18) መጸለይ እናዳለብን ቃሉ ያስተምረናል፡፡ ስለሆነም፣ የትኛውን አይነት ጸሎት መቼ ልንጸልይ እንደሚገባን ጌታ እንዲያስተምረን መጠየቅና ራሳችንን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
እንደ አማኞች አንድ ተግባርና “ዓላማ” ውስጥ ከመግባታችን በፊትም ሆነ ምርጫና ውሳኔዎችን ከማድረጋችን በፊት መጸለይን አስተምረኝ ብለን ጌታን ልንጠይቀው ይገባናል፡፡
ትክክለኛውን ጸሎት በትክክለኛው መንገድ ስንጸልይ ጌታ መንገዳችንን ያቀናልናል፤ የተሰወረውን ይገልጽልናል፣ ኃይልና ጸጋንም ይሰጠናል፡፡
ጌታ ሆይ፣ ሁል ጊዜ የራሳችንን መንገድ ከመከተል መለስ ብለን መጸለይን አስተምረን!
ጌታ ሆይ፣ እንዴት መጸለይ እንዳለብንም አስተምረን!
Dr. Eyob Mamo
@revealjesus