ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤ
“ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ” (1ጴጥ. 4፡1)፡፡
እስከዛሬ የኖርነውን ሕይወት መለስ ብለን ስንመለከት ምናልባት እንደቃሉ ያልሆኑ ልምምዶቻችን እናስታውስ ይሆናል፡፡ ያለፈው ልምምዳችን ያም ሆነ ይህ፣ በቀረልን ዘመን የሰውን ምኞት ተወት በማድረግ እንደ ጌታ ፈቃድ የምንኖርበት የሕይወት ዘይቤ እንድንይዝ ቃሉ ያበረታታናል፡፡ እንደ ቃሉ ስናስብና እንደ ቃሉ ስንናገር እንደቃሉ ወደሆነ የሕይወት ዘይቤ አንድ እርምጃ እንደተጠጋን ማስታወስ አለብን፡፡ ለዚህ አይቱ ሰማያዊ የሕይወት ዘይቤ ምሳ የሚሆኑን ብዙ ምስክሮች አሉን፡፡
“ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ” (ዘፍ. 6:9)፣ “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔርጋር አደረገ” (ዘፍ. 5:22)፡፡ ኢያሱም ቢሆን፣ “በምትሄድበትም ሁሉ እንዲሳካልህ፣ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል” (ኢያ. 1፡7) የሚለውን ቃል ሰምቶ ልቡን ያበረታ ሰው ነበር፡፡
እነዚህና ሌሎች እንደመና የከበቡን ምስክሮች የተውልንን ፈለግ በመከተል ሰማያዊውን የሕይወት ዘይቤ ለማዳበር ዋነኛው ጉዳይ ምርጫ ይባላል፡፡ የትኛውን የሕይወት ዘይቤ እንመርጣለን? የሚከተሉትን ምርጫዎቻችንን እንመልከት፡፡
1. እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመመላለስ ምርጫ
“በመንፈስ ተመላለሱ” (ገላ. 5፡16)፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ቃል የተናገረበት አውድ የስጋን ስራ የመፈጸምንና እኛ የምንፈልገውን ሳይሆን ጌታ የሚፈልገውን ነገር የማድረግን እውታ ያካተተ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በትእዛዝ መልክ ተቀምጦ ለእኛ ምርጫ የተተወ እንደሆነ ቃሉ ይጠቁመናል፡፡ እርስ በርስ የሚቀዋወሙትን የመንፈስና የስጋ አሳብ በመለየት ለመንፈስ አሳብ መወገን በመንፈስ እንድንመላለስ በርን ይከፍትልናል፡፡
2. እንደ ሰው ልማድ የመመላለስ ምርጫ
“ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?” (1ቆሮ. 3፡3)፡፡
ዙሪያችንን እንመለክተው፡፡ በስራና በማሕበራዊ መስኮቻችን የሚገኙ የዚህ አለም ሰዎች ያላቸውን የሕይወት ዘይቤ እናጢነው፡፡ የቅንአቱ፣ የክርክሩ፣ የዘረኝነቱ፣ የክፋቱ … ዘይቤ ከእኛ የተሰወረ አይደለም፡፡ ቃሉ በግለጽ የሚያስተምረን እንደነሱ እንዳንመላለስ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን በእኛም ሳይቀር እነዚህ የሰው ልማዶች ብቅ ሲሉ እናያቸዋለን፡፡ ዛሬ ግን በመንፈስ የመመላለስን ምርጫ መውሰድ እንችላለን፡፡
3. እንደ ጠላት ፈቃድ የመመላለስምርጫ
“በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው” (ኤፌ. 2:1)፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ ከላይ በተጠቀሰው ሃሳብ ላይ ራሱን በመጨመርና እርሱም የዚያ አይነት ሕይወት ተሳታፊ መሆኑን ካመነ በኋላ “ነገርግንበምሕረቱባለጠጋየሆነእግዚአብሔር … በክርስቶስሕያዋንአደረገን” በማለት በጸጋው ጉልበት አዲስ የሕይወት ዘይቤን መምረጡን ይጠቁመናል፡፡ እዚህም ጋር ምርጫው የእኛ ነው፡፡ ክፉው ሹክ እንዳይለንና ወደ ክፉ እንዳይመራን የመንፈስን መንገድ የመምረጥ ጸጋው ተሰጥቶናል፡፡
የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ሰማያዊ የውጊያ ዘይቤ”
Dr. Eyob