መርህን ሳይለቁ በዓለም የመሰማራት ሰፊነት
“ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም” (ዮሐ. 17፡15-16)፡፡
ብክለት የአለማችን ችግር ነው፡፡ አየሩ በየዕለቱ በምንናነደው ነዳጅ የተበከለ ነው፡፡ ባሕሩ በየጊዜው በምናራግፍበት ኬሚካና ቆሻሻ የተበከለ ነው፡፡ ምግቡ በማዳበሪያውና በተለያየ ቆሻሻ የተበከለ ነው፡፡ በእነዚህና መሰል የተበከሉ አካባቢዎች ውስጥ እየኖርን በተጽእኖው ስር አለመውደቅ እጅግ ከባድ ሁኔታ ነው፡፡ ከላይ የተመለከትነውም የክርስቶስ ጸሎት ይህንን መሰሉን ስዕል ነው የሚያመለክተን፡፡
ዓለም በተለያዩ ሁኔታዎች የተበከለች ነች፡፡ ይህ ብክለት ወደእኛ የተለያዩ ፈተናዎችን ይዞብን ይመጣል፡፡ የተበከለን አየር ላለመተንፈስ ካስፈለገ ያለን አማራጭ ከዚህ ዓለም መውጣት ነው፡፡ ይህኛውን ምርጫ ግን ክርስቶስ አልመረጠውም፡፡ በዚያው ሆነን እንድንጠበቅ ነው የጸለየልን፡፡
የጌታ የልቡ ፍላጎት በዓለም እንጂ ከዓለም እንዳልሆንን በማወቅ ክብራችንን ጠብቀን በዚህ ዓለም የመመላለስን ሰፊነት እንድንይዝ ነው፡፡ እውነታውን ትንሽ ዘርዘር አድርገን ስንመለከተው የሚከተሉትን ነጥቦች ማጤን እንችላለን፡፡
1. የዚህ አለም ገዢ ፈተና
“የዚህ ዓለም ገዥ ስለሚመጣ ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም። እርሱም በእኔ ላይ ሥልጣን የለውም” (ዮሐ. 14:30)፡፡
በዚህ ዓለም እስካን ድረስ የዚህ ዓለም ገዢ የሆነው ጠላታችን ዲያቢሎስ ካለማቋረጥ ፈተናውን ይዞ ወደ እኛ ይመጣል፡፡ በዚህ የጠላት አመጣጥ ላይ ድልን የሚሰጠን በክርስቶስ ያገኘነውን ስልጣን በማወቅ መለማመድ ነው፡፡ እኛም ከጌታችን ጋር በማበር “በእኔ ላይ ስልጣን የለውም” በማለት በእምነት ልንሞግተው ይገባናል፡፡
2. የአለም ጥላቻ
“ወንድሞች ሆይ፤ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ” (1ዮሐ. 3:13)፡፡
አንዳንድ አማኞች በፍጹም ሊለምዱት ያልቻሉት ሃቅ በተሰማሩበት አካባቢ ሰዎች እነሱን የመጥላታቸውንና ክፋትንና ወጥመድን በእነሱ ላይ ለማድረግ የመሞከራቸውን ሁኔታ ነው፡፡ ለዚህ ነው ጌታ “አትደነቁ” በማለት አዲስ ነገር እንደደረሰብን ማሰብ እንደማይገባን ያሳሰበን፡፡ ደግሞም እንዲህ ብሎናል፡- “ዓለም ቢጠላችሁ፣ ከእናንተ በፊት እኔን እንደጠላኝ ዕወቁ” (ዮሐ. 15:18)፡፡ የዓለም ጥላቻ ክርስቶስን አልደነቀውም፤ መንግስቱም ሆነ አስተሳሰቡ ሰማያዊ ስሆነ ምድራዊው ሊቀበለው አይችልም፡፡
3. የአለም ጉድፍ
“በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ነውር የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው … ከዓለም ርኵሰት ራስን መጠበቅ ነው” (ያዕ. 1:27)፡፡
ቀደም ሲል እንደጠቀስነው ዓለም በጉድፍ ተሞልታለች፡፡ ፍልስፍናውን፣ ምድራዊውን ጥበብና የኃጢያቱን ጥልቀት ስንመለከተው በቀላሉ ለዚህ ጉድፍ የተጋለጥን እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ በዓለም ባለን ስምሪት ውስጥ ከዚህ ጉድፍ ራሳችንን ጠብቀን መኖር ታላቅ ሰፊነት ነው፡፡ በንስሃ፣ ራስን ከክፋት በመለየትና ካለማቋረጥ ሃሳባችንን ከክፉ ሃሳብ፣ እግሮቻችንን ደግሞ ከአልባሌ መንገድ መከልከል የዚህ ሰፊነት ተግባራዊ እርምጃዎች ናቸው፡፡
የሚቀጥለው ትምህርት፡ “ትህትናን ሳይለቁ ምስጋናን የመቀበል ሰፊነት”
@revealjesus