ማንን ይበልጥ ትወዳለህ እናትህን, አባትህን, ሚስትህን ወይስ ልጆችህን ሁሉንም ከልብህ ልትወድ እና ፊዳ ልትሆንላቸው ዝግጁ ነህ? አዎን ነው መልስህ ነገር ግን ሰዓቲቱ ስትቀርብ ሁሉም ላቡ ሲያጠምቀው ሁሉም ወደ ራሱ ሲዞር እና ነብሴ ነብሴ ሲል ቤተሰብህን እንኳን መርዳት ሲያቅትህ የለፋህበት ፆም እና ሰላትህም ሃጅ ያደረግከው ሰደቃም የሶደቅከው ሁሉ መና የሚያስቀር ክስተት ዋ! ጥፋቴ ያስብላል የሰው ቀልብ የሰበርነው, የዞለምነው, ያስከፋነው, ብር ተበድረን የካድነው ሁሉ እየመጣ ሲበዘብዘን ዋ! ጥፋቴ ማለት ብቻ ሳይሆን እንኖረዋለን ታድያ ይሄን ሁሉ መልካም ስራህን አሁን ማንም እንዳይወስድብህ ለምን አትጠብቀውም bro አፉ በለኝ ማለትን ልመድ ልቡን ያቆሰልከውን ሁሉ ለመጠገን ሞክር🤌