አስራት ሀይሌ (ጎራዴው)እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር
በዘመን ቅብብሎሽ 89 ዓመታትን ታሪክ ያስቆጠረው ታላቁ ስፖርት ማህበራችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በተለያየ ዘመንና ወቅት ታሪክ ጽፈው ታሪክ ሰርተው ያለፉ የእልፍ ጀግኖች ቤት ነው፣ ከእነዚህ እልፍ ጀግኖች መካከል አንዱ የሀገር ኩራት የእኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማህበር ምልክት የሆነው አስራት ሀይሌ(ጎራዴው) ነው፡፡
አስራት ሀይሌ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች በመሆን አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ ከተቀላቀለ ጀምሮ በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በስፖርት ማህበራችን ታሪክ ሰርቷል፡፡ ስሞት ብቻ ነው ያለው አስራት ሀይሌ በህይወት ዘመኑ የቅዱስ ጊዮርጊስ የዋንጫ መደርደሪያ ካስዋቡና ታሪከኞች ተርታ አስራት ሀይሌ በቀዳሚነት ይሰለፋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በመደበኛ ጨዋታዎች አምስት ዋንጫዎችን ያገኘ ሲሆን በዚህ ታሪኩ ዘወትር ስናስታውሰው እንኖራለን፡
በ1975 ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በአዲስ አደረጃጃት ከዋቀረበት ዘመን ጀምሮ ክለቡን ለማገዝ እግር ኳስ ለመቆም እና ጫማውን ለመስቀል እድሜው በደረሰበት ዘመን ላይ ቢሆንም የምወደው የልጅነት ክለቤ ተቸግሮ ማየት ህሊናየን ሰላም አይሰጠውም በማለት ከሌሎች የቀድሞ አንጋፋ ተጫዋቾች ጋር በመሆን ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ጽፏል፡፡
አስራት ሀይሌ ጫማውን ከሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስፖርት ማህበራ ዋናውን ቡድን በአሰልጣኝነት እየመራ በ1986፤1987፤1988 ለተከታታይ ሶስት ዓመታት ዋንጫ በማንሳት ታሪክ በመስራት ቀዳማዊ ሰው ነው፡፡
✓ አስራት ሀይሌ ያስመዘገባቸው ውጤቶች በአደባባይ ምስክሮች ናቸው ከነዚህም መካከል መቼም የማይረሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት አጋጣሚዎች በ1977እና በ1991 ከወረደበት ከታችኛው ሊግ ወደ ላይኛው ሊግ ያሸጋገረበት ታሪክ ለዘላለም ላይረሳ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ወደ ከፍተኛ ሊግ ባመጣበት ዓመት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳ ብቸኛ ሰው ያደርገዋል፡፡
✓ አስራት ሀይሌ በአሰልጣኝነት ዘመኑ ያሰለጠናቸው ተጫዋቾች አብዛኛውን ዛሬ ላይ በሀገራችን ባሉ ውድድሮች ውሰጥ አሰልጣኝነት በቅተው ለሀገሪቱ የእግርኳስ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፆ እያደረጉ በመሆኑ ፍሬውን አፍርቶ በአደባባይ አስመስክሯል ፡፡
✓ አስራት ሀይሌ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለት ገዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ታሪክ ከሀገር ውጭ የምሰራቅ አፍሪካን ዋንጫ ለማምጣት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
✓ አስራት ሀይሌ ሀገሩን ብሎ ክለቡን ቅዱስ ጊዮርጊስን ብሎ የሚወዳትን ኳስ ብሎ በጥቅም ሳይደለል ለሚወደው እግር ኳስ ስፖርት መስዋት የከፈለ ጀግናችን ነው፡
✓ አስራት ሀይሌ በወጣት ተጫዋቾች ሙሉ እምነትና ተስፋ ስለነበረው አብዛኞቹ ወጣቶች ከታች በማሳደግ ለስፖርት ማህበራቸችንም ለብሄራዊ ቡድንም የሚታይ ታሪክ ሰርቷል፡፡
✓ አስራት ሀይሌ በህፃናት ክህሎትና ለወጣቶች ባለው ጥልቅ ፍቅር በየዘመናቱ በድከጃ እሳቆመበት ድረስ በህጻ ናት ወጣቶች ፕሮጀክት ማስፋፈት ለሚወደው የእግር ኳስ ስፖርት የማይረሳ ታሪክ ሰርቷል፡፡
✓ አስራት ሀይሌ በተጫወቃችነትም ሆነ በአሰልጣኝት በስራ ጠንቃቃ እና ፍጹም ታማን ሁኖ አልፏል፡፡
✓ ሌብነትን እና ውሸትን የሚጸየፈው አስራት ሀይሌ በአንድ ወቅት በስፖርት ማህበራችን ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንዲህ ብሎን ነበር
"እኔ ቅዱስ ጊዮርጊስን የምለየው ስሞት ብቻ ነው"!
የስፖርት ማህበራችን ደጋፊዎች የቦርድ አመራር የጽህፈት ቤት ሰራተኞች አሰልጣኞች እና ተጫዋቾች እንዲሁም ደጋፊዎቻን ከልብ የሚወዱት አስራት ሀይሌ እስክሞት እወደዋለሁ ያለው ክለብ እየወደደው እያከበረው እያፈቀረው ጥቅምት 15/2017ዓ.ም በሞት ተለይቶናል ፡፡ አስራት ሀይሌ(ጎራዴው) አንተ እስከምትሞት ድረስ እወድዋለሁ ያልከው ቅዱስ ጊዮርጊስ ማህበር በትውልድ ቅብብሎሽ ታሪክን እያወሳ ለዘላለም ሲዘክርህ ይኖራል ፡፡
ሁሌም በልባችን ትኖራለህ ምንግዜም ጊዮርጊስ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር
👉
@SAINTGEORGEFC 👈
👉
@SAINTGEORGEFC 👈
👉
@SAINTGEORGEFC 👈
፩ ክለብ ፩ ቤተሰብ
ሁሌም ስለ ሳንጃው እንዘግባለን✌️