ከመሞቴ ትንሽ ቀደም ብሎ ...
[ ኑረዲን ዒሳ ]
ከስራ ወጥቼ
አምሽቼ
ወደ ቤት እየገባሁ ነው
ያገኙኝ ።
እየመጣሁ አስባለሁ...
አሁን ቤት ገብቼ
ግንባሯን እስማታለሁ
ቱታ እቀይራለሁ
እራት እበላለሁ
እላለሁ ።
እውነቷን እኮ ነው ...
ሰውና እንጨት ተሰባሪ ነው
እውነቷን እኮ ነው
አሁን ቤት ገብቼ አፀንሳታለሁ ።
ካመንሽኝ...
ይሄን እያሰብኩ ነው ያገኙኝ
«ቁም !» አሉኝ
ቆምኩኝ
«ድው !» ሲል ወደቅኩኝ ።
ምነው ዛሬን ዘለው ነገ በገደሉኝ
እያልኩ ነው የገደሉኝ
ካንቺና ከዛሬ እኔን የነጠሉኝ
እ ወ ድ ሻ ለ ሁ ኝ ።
@Samuelalemuu
[ ኑረዲን ዒሳ ]
ከስራ ወጥቼ
አምሽቼ
ወደ ቤት እየገባሁ ነው
ያገኙኝ ።
እየመጣሁ አስባለሁ...
አሁን ቤት ገብቼ
ግንባሯን እስማታለሁ
ቱታ እቀይራለሁ
እራት እበላለሁ
እላለሁ ።
እውነቷን እኮ ነው ...
ሰውና እንጨት ተሰባሪ ነው
እውነቷን እኮ ነው
አሁን ቤት ገብቼ አፀንሳታለሁ ።
ካመንሽኝ...
ይሄን እያሰብኩ ነው ያገኙኝ
«ቁም !» አሉኝ
ቆምኩኝ
«ድው !» ሲል ወደቅኩኝ ።
ምነው ዛሬን ዘለው ነገ በገደሉኝ
እያልኩ ነው የገደሉኝ
ካንቺና ከዛሬ እኔን የነጠሉኝ
እ ወ ድ ሻ ለ ሁ ኝ ።
@Samuelalemuu