ልኬ እንደቆጨችኝ ፡ ቴክስት ሜሴጄ
እኔም ከተሸኘሁ ፡ላልመለስ ሄጄ
አታቻኩለኝ እግሬ፡ አታጣድፈኝ እጄ
ቀናት ከማፋሰስ ፡የማይለቀሙ
ቃላት ከማፋለስ ፡ለትርጉም አዝግሙ
ያኖሩትን ማንበብ ፡
የኖሩትን ማሰብ፡ እየደጋገሙ።
ልፃፍ ጊዜ ስጡኝ
ልረፍ ብዕር ስጡኝ
ፊደላት አድምጡኝ፡ አካላቴም ስሙ...
መንገዱን ላትዘልቁ፡ ልቤን አታድክሙት
የደረስኩበትን፡ ልድረስና ልሙት።
By red-8
@Samuelalemuu
እኔም ከተሸኘሁ ፡ላልመለስ ሄጄ
አታቻኩለኝ እግሬ፡ አታጣድፈኝ እጄ
ቀናት ከማፋሰስ ፡የማይለቀሙ
ቃላት ከማፋለስ ፡ለትርጉም አዝግሙ
ያኖሩትን ማንበብ ፡
የኖሩትን ማሰብ፡ እየደጋገሙ።
ልፃፍ ጊዜ ስጡኝ
ልረፍ ብዕር ስጡኝ
ፊደላት አድምጡኝ፡ አካላቴም ስሙ...
መንገዱን ላትዘልቁ፡ ልቤን አታድክሙት
የደረስኩበትን፡ ልድረስና ልሙት።
By red-8
@Samuelalemuu