ይኸው ደሞ ክረምት ሆነ
ትዝታ ከደጅ አደረ፤
የአምናን መዝሙር
በአሁን አቅም
በክራሩ ደረደረ።
ናፈቀ አዲስ መስከረም፤
ተመኘ ፍካት ልጅነት፤
በመጸው ልብ በፅጌ ወር፤
የዐደይ እንቁ መሸመት።
ቢጫ ዕንቁ፣
የማር ሰፈፍ፣
ህቱም ጸጋ፤
የአበባ ልብ፣
ምዑዝ ጠረን፣
ነይ በዝናም፤
ነይ ክረምቱን፤
ስለ ወቅትሽ፤
ስለ ወቅቴ ፤
በሙላህ ሆነን
እናውጋ።
ነይ ሐምሌን ክረሚ፤
ነይ ጳጉሜን ታገሺ፤
የመጠበቅ ልክ፤
የመክረምን አቅም፤
ከዘመን ተዋሺ።
የወንዙን ሙላት ዕይ፤
ማለፊያ ፍለጋ የከፋፈተውን
የአፈር ገላ ለይ።
ቅመሺው አየሩን፤
ቀዝቃዛውን ንፋስ፤
ቀላል እንዳይመስልሽ፤
ይሔንን ቁር አልፎ
መስከረም ዜማሽን
ካንቺ ጋ መደነስ።
( ወቅትሽ ላይ መነስነስ....!)
ኹለን ወር አውቃለኹ፤
አንቺ አታውቂም እንጂ፤
ነይ እስኪ ነሐሴ
የደረሰ ተስፋ
የጨለመን ሌሊት፤
ከትዝታ ጋራ
ማሳለፍ ልመጂ።
የአፈር ቀለም ይንካሽ፤
ሰው ሰው
ይሽሽተት ገላሽ፤
ከ ዓመት እስከ ዓመት
እንዳትሰወሪ ...
ግጥም እፅፋለኹ
ቃሌ ነው መታያሽ።
ወንዙን ተከትለሽ
ሂጂ ከባህሩ፤
ያስቀመጥኩት ዕንባ፤
ከዚያ ነው መገኛው
በቀደመ ክብሩ።
ዕንባ ክብር አለው፤
አለው ቅድስና ፤
ይሄንም ቅመሺ
እንደኔ ኹኚና።
ሰው መሆን ቻይበት፤
ታናሽ የመሰለሽ
ይሔ ቤተ አምልኮ፤
መለኮት አለበት።
ማን እንደሆንሽ ዕይ፤
ቃልን ተሸከሚ፤
በእኔ እድሜ ቁመት
ክረምቱን አዝግሚ ።
ነይ ወንጌል ድገሚ፤
ነይ ሃሌ ዘምሪ፤
ቤተ ውበትሽን፤
በጉባኤ ምሪ፤
ነይ ፅጌን ሞሽሪ።
ነይ ከኔ ክረሚ ፤
ነይ ከኔ ክረሚ
ቁሩን አሳልፉሽ
መፀው ላይ አዝግሚ።
[ መንበረ ማርያም ሃይሉ ]
@Samuelalemuu
ትዝታ ከደጅ አደረ፤
የአምናን መዝሙር
በአሁን አቅም
በክራሩ ደረደረ።
ናፈቀ አዲስ መስከረም፤
ተመኘ ፍካት ልጅነት፤
በመጸው ልብ በፅጌ ወር፤
የዐደይ እንቁ መሸመት።
ቢጫ ዕንቁ፣
የማር ሰፈፍ፣
ህቱም ጸጋ፤
የአበባ ልብ፣
ምዑዝ ጠረን፣
ነይ በዝናም፤
ነይ ክረምቱን፤
ስለ ወቅትሽ፤
ስለ ወቅቴ ፤
በሙላህ ሆነን
እናውጋ።
ነይ ሐምሌን ክረሚ፤
ነይ ጳጉሜን ታገሺ፤
የመጠበቅ ልክ፤
የመክረምን አቅም፤
ከዘመን ተዋሺ።
የወንዙን ሙላት ዕይ፤
ማለፊያ ፍለጋ የከፋፈተውን
የአፈር ገላ ለይ።
ቅመሺው አየሩን፤
ቀዝቃዛውን ንፋስ፤
ቀላል እንዳይመስልሽ፤
ይሔንን ቁር አልፎ
መስከረም ዜማሽን
ካንቺ ጋ መደነስ።
( ወቅትሽ ላይ መነስነስ....!)
ኹለን ወር አውቃለኹ፤
አንቺ አታውቂም እንጂ፤
ነይ እስኪ ነሐሴ
የደረሰ ተስፋ
የጨለመን ሌሊት፤
ከትዝታ ጋራ
ማሳለፍ ልመጂ።
የአፈር ቀለም ይንካሽ፤
ሰው ሰው
ይሽሽተት ገላሽ፤
ከ ዓመት እስከ ዓመት
እንዳትሰወሪ ...
ግጥም እፅፋለኹ
ቃሌ ነው መታያሽ።
ወንዙን ተከትለሽ
ሂጂ ከባህሩ፤
ያስቀመጥኩት ዕንባ፤
ከዚያ ነው መገኛው
በቀደመ ክብሩ።
ዕንባ ክብር አለው፤
አለው ቅድስና ፤
ይሄንም ቅመሺ
እንደኔ ኹኚና።
ሰው መሆን ቻይበት፤
ታናሽ የመሰለሽ
ይሔ ቤተ አምልኮ፤
መለኮት አለበት።
ማን እንደሆንሽ ዕይ፤
ቃልን ተሸከሚ፤
በእኔ እድሜ ቁመት
ክረምቱን አዝግሚ ።
ነይ ወንጌል ድገሚ፤
ነይ ሃሌ ዘምሪ፤
ቤተ ውበትሽን፤
በጉባኤ ምሪ፤
ነይ ፅጌን ሞሽሪ።
ነይ ከኔ ክረሚ ፤
ነይ ከኔ ክረሚ
ቁሩን አሳልፉሽ
መፀው ላይ አዝግሚ።
[ መንበረ ማርያም ሃይሉ ]
@Samuelalemuu