ልፃፍሽ ወይ ግጥም?
አንቺ ውብ በራሪ፡
አንቺ ትንግርት ሀሳብ
አፈር ላይ በልቤ፡ ወድቄ ከምሳብ
ከኔ ዘንድ የመጣሽ
አንች ሀሳብ ምረጪ፡
ምንድን ይሁን እጣሽ?
ንገሪኝ...ልፃፍሽ?
ልግለጥሽ በግጥም?
ወይ ልቤ ደብቄሽ፡ ውበትሽን ላጣጥም?
ወይስ እንዳላየ፡ ልተውሽ በእንጥልጥል?
ከኔ የላቀ ሊቅ፡ ዐይኖቹን እስኪጥል
ያ'ፈር ላይ ኑሮዬን፡ አርፌ ልቀጥል?
አንቺ ውብ በራሪ
ክንፋም ተወርዋሪ
ሀሳብ ተናገሪ
ምን ላርግሽ? ወስኚ
መልክሽን ገጥሜው የኔ ብትሰኚ
የብርሃን ክንፍሽ፡ በቃል ይታሰራል
ልትሆኝ የነበረ፡
እጣ ፈንታሽ ሁሉ፡ ግጥም ሆኖ ይቀራል
ረቂቅ ነውና፡ የሀሳብ ፍጥረቱ
ፊደል ሲወስነው፡ በጠባብ ደረቱ
ውብ ቢሆን መናኛ፡ ድንቅም ቢሆን ከንቱ
እንዳከሳሰቱ፡ የሚያሳሳ የታል?
ያሰቡት ድንቅ ሁሉ፡ ሲፅፉት ይሞታል።
አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ምን ላርግሽ?
ላኑርሽ? ሳልገጥም?
ታምርሽን በልቤ ፡ሰውሬ ላጣጥም
አውጥቼ አውርጄ፡ ላስብ ላብሰልስልሽ
በህልም በሰመመን፡ በምናብ ላድንቅሽ
ዝም ብዬ ላልቅስሽ? ዝም ብዬ ልሳቅሽ?
የሌቴን መከራ ፡ የቀኔን አበሳ
አስታወሼሽ ልርሳ?
አልል ልቤ ሳሳ
ስኖር የኖርኩብሽ፡ ስሞት ብትሞቺሳ?
አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ልተውሽ? ጉጉቴን ገትቼ
ውበት ትንግርትሽን፡ ለሚገባው ትቼ
ስትበሪ አቅርቅሬ፡ ትቢያውን ቃርሜ
ሚስጥርሽን ባዕድ፡ ውበትሽን እርሜ
ላድርግ ልፀየፈው?
የሆንሽውን ሁሉ፡ የሆነ እስኪፅፈው
አንች ሀሳብ ክንፍሽን፡ ተስቤ ልለፈው... ?
ንገሪኝ? ሀሳቤ
ከግጥም ከልቤ
ወይ ደሞ ከመተው
ከየቱ ስልቻ፡ እጣሽን ልክተተው?
የት ላርግሽ ንገሪኝ፡ እኔ ልክ አላውቅም
መጠየቅ ብቻ ነው፡ የፀሐፊ አቅም።
#rediet_assefa
@Samuelalemuu
አንቺ ውብ በራሪ፡
አንቺ ትንግርት ሀሳብ
አፈር ላይ በልቤ፡ ወድቄ ከምሳብ
ከኔ ዘንድ የመጣሽ
አንች ሀሳብ ምረጪ፡
ምንድን ይሁን እጣሽ?
ንገሪኝ...ልፃፍሽ?
ልግለጥሽ በግጥም?
ወይ ልቤ ደብቄሽ፡ ውበትሽን ላጣጥም?
ወይስ እንዳላየ፡ ልተውሽ በእንጥልጥል?
ከኔ የላቀ ሊቅ፡ ዐይኖቹን እስኪጥል
ያ'ፈር ላይ ኑሮዬን፡ አርፌ ልቀጥል?
አንቺ ውብ በራሪ
ክንፋም ተወርዋሪ
ሀሳብ ተናገሪ
ምን ላርግሽ? ወስኚ
መልክሽን ገጥሜው የኔ ብትሰኚ
የብርሃን ክንፍሽ፡ በቃል ይታሰራል
ልትሆኝ የነበረ፡
እጣ ፈንታሽ ሁሉ፡ ግጥም ሆኖ ይቀራል
ረቂቅ ነውና፡ የሀሳብ ፍጥረቱ
ፊደል ሲወስነው፡ በጠባብ ደረቱ
ውብ ቢሆን መናኛ፡ ድንቅም ቢሆን ከንቱ
እንዳከሳሰቱ፡ የሚያሳሳ የታል?
ያሰቡት ድንቅ ሁሉ፡ ሲፅፉት ይሞታል።
አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ምን ላርግሽ?
ላኑርሽ? ሳልገጥም?
ታምርሽን በልቤ ፡ሰውሬ ላጣጥም
አውጥቼ አውርጄ፡ ላስብ ላብሰልስልሽ
በህልም በሰመመን፡ በምናብ ላድንቅሽ
ዝም ብዬ ላልቅስሽ? ዝም ብዬ ልሳቅሽ?
የሌቴን መከራ ፡ የቀኔን አበሳ
አስታወሼሽ ልርሳ?
አልል ልቤ ሳሳ
ስኖር የኖርኩብሽ፡ ስሞት ብትሞቺሳ?
አንች ሀሳብ ያሰብኩሽ
ንገሪኝ ልተውሽ? ጉጉቴን ገትቼ
ውበት ትንግርትሽን፡ ለሚገባው ትቼ
ስትበሪ አቅርቅሬ፡ ትቢያውን ቃርሜ
ሚስጥርሽን ባዕድ፡ ውበትሽን እርሜ
ላድርግ ልፀየፈው?
የሆንሽውን ሁሉ፡ የሆነ እስኪፅፈው
አንች ሀሳብ ክንፍሽን፡ ተስቤ ልለፈው... ?
ንገሪኝ? ሀሳቤ
ከግጥም ከልቤ
ወይ ደሞ ከመተው
ከየቱ ስልቻ፡ እጣሽን ልክተተው?
የት ላርግሽ ንገሪኝ፡ እኔ ልክ አላውቅም
መጠየቅ ብቻ ነው፡ የፀሐፊ አቅም።
#rediet_assefa
@Samuelalemuu