🤚የሸዋል ዒድ (ትንሹ ዒድ)
በኢስላም አመታዊ ዒዶቻችን ሁለት ናቸው። ማስረጃውም አነስ ብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው። ነብዩ ﷺ መዲና ሲመጡ ነዋሪዎቿ የሚጫወቱባቸው ሁለት ቀናት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነዚህ ሁለት ቀናት?” ብለው ጠየቁ። “በጃሂሊያው ጊዜ እንጫወትባቸው ነበርን” አሉ። በዚህን ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ﷺ “የላቀው አላህ ከነሱ በላጭ በሆኑ ሁለት ቀናት ተክቶላችኋል። እነሱም የአድሓ ቀንና የፊጥር ቀን ናቸው” አሉ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1039]
“ተክቶላችኋል” የሚለው አነጋገር የሙስሊሞች ዒዶች የተወሰኑና፣ በሸሪዐ የሚደነገጉ እንደሆኑ ጥቆማ ይሰጣል። የሰለፎቻችን አካሄድም ይህን ግንዛቤ ይበልጥ ያጠነክራል። ኋላ ላይ እንግድ ቢድዐዎች እስከሚመጡ ድረስ ነብዩ ﷺ ከደነገጓቸው ዒዶች ውጭ ሌላ ዒድ አልተንፀባረቀም። በተለይም ደግሞ ነብዩ ﷺ “ከሰው ሁሉ በላጩ የኔ ትውልድ ነው። ከዚያም ከእነሱ ቀጥለው የሚመጡት፤ ከዚያም ከነሱ ቀጥለው የሚመጡት” ብለው ምስክርነት የሰጡት ሶስቱ ወርቃማ ዘመን ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር አልነበረም።
ኋላ ላይ ከመጡ እንግዳ በዓላት ውስጥ አንዱ ታዲያ የሸዋል ዒድ የሚባለው ቢድዐ ነው። ይሄ በአል በሸሪዐ ቦታ ቢኖረው ኖሮ በቁርአንና በሐዲሥ ውስጥ ይጠቀስ ነበር። ቁርአንና ሐዲሥ ውስጥ ከሌለ፣ ቀደምቶች ካላወቁት ቢድዐ ከመሆን ውጭ ሌላ ምርጫ የለም። ነብዩ ﷺ “ወደ ጀነት የሚያቀርባችሁና ከእሳት የሚያርቃችሁ ሆኖ በእርግጠኝነት የነገርኳችሁ ቢሆን እንጂ የተውኩት ነገር የለም” ብለዋል። [አሶሒሐ፡ 4/416]
ይሄ የሸዋል ዒድ የተወገዘ ቢድዐ እንደሆነ ዑለማኦች ይናገራሉ። አንድ ሁለቱን ልጥቀስ፦
1- ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
وأما اتخاذ موسم غير المواسم الشرعية كبعض ليالي شهر ربيع الأول التي يقال: إنها ليلة المولد, أو بعض ليالي رجب, أو ثامن عشر ذي الحجة, أو أول جمعة من رجب, أو ثامن من شوال الذي يسميه الجهَّال عيد الأبرار: فإنها من البدع التي لم يستحبها السلف , ولم يفعلوها.
"ሸሪዐዊ ያልሆኑ ክብረ በዓላትን ክብረ-በዓል አድርጎ መያዝ ግን ‘የመውሊድ ሌሊት’ የሚባሉትን የተወሰኑ የረቢዐል አወል ሌሊቶችን ወይም የረጀብ ሌሊቶችን ወይም ደግሞ ዙልሒጃ አስራ ስምንትን ወይም ደግሞ የረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐን ወይም ደግሞ መሃይማን 'የደጋጎች ዒድ' እያሉ የሚጠሩትን #ሸዋል_ስምንትን የመሰሉ እነዚህ ሰለፎች እንደሚወደዱ ያልገለጿቸውና ያልተገበሯቸው #ቢድዐዎች ውስጥ ናቸው።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/298]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
وأما ثامن شوال : فليس عيداً لا للأبرار ولا للفجار , ولا يجوز لأحد أن يعتقده عيداً, ولا يحدث فيه شيئاً من شعائر الأعياد
"ሸዋል ስምንትን በተመለከተ ለደጋጎችም ይሁን ለባለ -ጌዎች ዒድ አይደለም። ለማንም ቢሆን ዒድ አድርጎ ሊያምንበት አይፈቀድም። በሱ ውስጥ የትኛውም የበዓላት መገለጫዎች ሊንፀባረቁበት አይገባም።" [አልኢኽቲያራቱል ፊቅሂያህ፡ 199]
2- ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲሰላም ኸዲር አሹቀይሪይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
ويكون الاحتفال بهذا العيد في أحد المساجد المشهور فيختلط النساء بالرجال ويتصافحون ويتلفظون عند المصافحة بالألفاظ الجاهلية, ثم يذهبون بعد ذلك إلى صنع بعض الأطعمة الخاصة بهذه المناسبة
"ይሄ ዒድ የሚከበረው ከታዋቂ መስጂዶች ውስጥ በአንዱ ይሆናል። ከዚያ ሴቶች ከወንዶች ጋር ይቀላቀላሉ። በሰላምታ ይጨባበጣሉ። ሲጨባበጡም የጃሂሊያ ቃላትን ይናገራሉ። ከዚያም በኋላ ለዚህ ጊዜ የተለዩ የተወሰኑ የምግብ አይነቶችን ያዘጋጃሉ።" [አሱነኑ ወልሙብተደዓት፡ 166]
በመጨረሻም በአንድ ማሳሰቢያ ልዝጋ። የጉዳዩን ብይን የሚያሳዩ የሸሪዐ መሰረቶች እና የዑለማእ ንግግር እየተጠቀሰ አይኑ እያየ ልክ እኛ ከኪሳችን የተናገርን ይመስል "ሁሉን ነገር ቢድዐ አደረጋችሁብን" አይነት የአላዋቂዎች ተቃውሞ የሚያሰማ አካል ቦታ የለውም። እለቱን ዒድ አድርጎ መያዝ አይገባም ስለተባለ ዱንያ ሁሉ ቢድዐ እንደተባለ እያስመሰሉ ማቅረብም ራስን መሸወድ ነው። ሲጀመር በአንዳንድ አካባቢዎች ካልሆነ በስተቀር ይሄ ልማድ በብዙ ቦታዎች አይታወቅም። ይልቅ ከሙስሊም የሚያምረው ለማስረጃ እጅ መስጠት ነው።
©IbnuMunewor