መፅሀፍትን አሳትሞ ለአንባቢያን የማቅረብ ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መሆኑ ተገለፀ
ከዚህ ቀደም በዓመት እስከ አምስት መፀሀፍት የማሳተም ስራ ሲሰሩ የነበሩ አሳታሚ ድርጅቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙሉ ለሙሉ የህትመት ስራ ማቆማቸውን ሰምቻለሁ በማለት ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
የወረቀት ዋጋ መወደድን ተከትሎ አሳታሚዎች መፀሀፍቶቻቸውን እንዳያሳትሙ አድርጓቸዋል የተባለ ሲሆን በዚህ ሁሉ ችግር ታትሞ ለገበያ ቢቀርብም አንባቢ እንደማይኖረው በአንድ የመፀሀፍ ኤግዚቢሽን ላይ የተሳተፉ ደራሲያንን እና መፀሀፍ ሻጮች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ይህ የሆነበት ምክንያት መፀሀፍቱ የሚሸጡበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ነው ሲባል መፀሀፍ ማሳተም አስቸጋሪ እንደሆነና ይህ ችግር በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ነባር ደራሲያንን ብቻ ሳይሆን ወደ ዘርፉ የሚመጡ ጀማሪ ደራሲያንንም ያሳጣል ተብሏል።
ፀሀፊያን እና ደራሲያን መንግስት ከቀረጥ ነፃ ወረቀት እንዲገባ እና በህትመት ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ምክረ ሀሳብ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ባለሀብቶች የህትመት ኢንዱስትሪው ላይ እና የወረቀት ማምረት ስራ ላይ ሊሳተፉ ይገባልም ነው የተባለው።
ፎቶ፦ ፋይል
@TikvahethMagazine