ልቤን ክፈተው!
ከራስ ጋር ንግግር፦ "ታውቃለህ አባቴ የጠፋው ልጅህ ነኝ፣ ከጉያህ የሸሸው፣ ከቤትህ የተሰወርኩ፣ ህግጋትህን የጣስኩ፣ በደልን የተለማመድኩ ምስኪን ልጅህ ነኝ። ነገር ግን ቢረፍድም ዛሬ ጥፋቴ ገብቶኛል፣ ጊዜው ቢርቅም ዛሬ ፀፀት ውስጤን ቀፅፎ ይዞታል፣ ምንም እንኳንም ቢዘገይም አሁን ግን እኔም አንተን መፈለግ ጀምሬያለሁ። ከልቤ ናፍቀሀኛል፣ የምርም እንደምታስፈልገኝ ገብቶኛል። ህይወት ያላንተ ባዶ እንደሆነች ገብቶኛል፣ መኖር ካንተ እቅፍ ወጥቶ ትርጉም እንደሌለው ተረድቼያለሁ። ቤትህ መምጣት ባይገባኝ፣ የጥፋቴ ብዛት፣ የበደሌ ግዝፈት ፊትህ ባያቆመኝ እኔ ግን ዛሬም ደጅህን እጠናለሁ፣ ከነጉድፌ፣ ከነጥፋቴ ከበሩ ቆሜ እጠብቅሃለሁ። የልቤን አንተ ታውቃለህ፣ የውስጤን ቀድመህ ትረዳለህ። እያወከኝ ዝም ብለሀኛል፣ እያወከኝ ጠብቀሀኛል። እንግዲህ እኔው በፍቃዴ የምታውቀውን እኔ መቼ ላሳይህ ልምጣ?
አዎ! አባቴ ትባርከኝ ዘንድ መቼ ልምጣ? መቼ ወደቤትህ ልጠጋ? መቼህ እቅፍህ ውስጥ ልግባ? መቼስ ዝቅ ብዬ፣ አቀርቅሬ ልለምንህ? ለዝቅታዬ ከተሰበረው ልብ በላይ፣ ከተፀፀተው ማንነት፣ እራሱንም ካዋረደው እኔነት በላይ የሚያስፈልግ ነገር ይኖር ይሆን? ቢኖርም ነፍሴ ወጥታ ወዳንተ ከመሄዷ በፊት እኔው እራሴ ከነነፍሴ ወዳንተ ለመምጣት ወስኜያለሁና ምንም ለማድረግ ዝግጁ ነኝ። የልቤ ስብራት እንዲጠገን እፈልጋለሁ፣ ዳግም ባንተ ሙሉ ሰው መሆን እፈልጋለሁ፣ ከቀደመው ማንነቴ በላይ ላንተ መገዛትን፣ ባንተ መመራትን መርጬያለሁ። ልቤ ታሟል፣ ውስጤ ሰላም አጥቷል፣ መንፈሴ አንተን ተጠምቷል። የህመሜ መድሃት ደግሞ ካንተ ውጪ ማንም ጋር የለም፣ የምድነው ባንተ ብቻ ነው፣ መንፈሴ የሚረጋጋው፣ ሰላሜም የሚመለሰው ባንተ ብቻ ነው። ልቤን ክፈተው! ወደቤትህ ምራኝ፤ አስጠግተህ ገስፀኝ፣ አስተምረኝ፣ በፍቅርህ ከዘላለም ሞት ነፃ አንዳወጣሀኝ ዛሬም ነፍሴ አንተን ትናፍቃለችና ድረስላት፣ እረፍት ከሌለው የዓለም ውጥንቅጥ ታደጋት።"
አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ለፈጣሪህ አሳይ፣ የሚያውቀውን ማንነትህን ገልጠህ አስረዳው። እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ከዋኒ አምላክ ነው። እያንዳንዱ ተግባሩ የኛን ምርጫ ከግምት ያስገባ ነው፤ የትኛውም ምርጫውም የኛን ፍላጎት ያገናዘበ ነው። ዘወትር እያመሰገንከው እንድትኖር፣ ሁሌም ማንነትህን ለእርሱ እንድታስገዛ፣ በየጊዜው ደጁ እንድትጠና ማድረግ አቅቶት አይደለም። ይልቅ ማናችንም ለገዛ ህይወታችን ሃላፊነት መውሰድ ስላለብን ነፃ አድርጎናል፣ በሰጠን ነፃ ፍቃድ በፍላጎታችን ፈልገን እናገኘው ዘንድ መንገዱን ሁሉ ክፍት አድርጎልናል። ፈጣሪ የሌለበት ህይወት ከባዶው ምድረበዳ የሚበልጥ ነው። ምደረበዳ ምንም አያበቅል ይሆናል እግዚአብሔር የሌለበት ህይወት ግን ክፋትና ጭካኔን ያበቅላል፣ ለሃጢአት የተመቸ ይሆናል፣ እለት እለት መንፈስን እያደሀየ፣ ስሜትን እየሰበረ፣ ውስጥን እያረከሰ ከሰውነት ከብር በታች ያኖራል። ለፈጣሪህ እራስህን አሳይ፣ ወደቤቱ ግባ፣ ከምድረበዳ የባሰውን ህይወትህን ወደ ለምለም ትርፋማ ምድር ቀይረው።
═════════❁✿❁ ═════════
💪💯 ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!👌የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/selafeker
@selafekerbot
@Addisu32