ጥበቃህን ግታው!
ተሸናፊዎች ሲወድቁ ያቆማሉ፣ በቃላት ፈጥነው ይሰበራሉ፣ ከስኬታቸው በላይ ውድቀትና ስህተታቸውን ደጋግመው ያስባሉ። አሸናፊዎች ግን እስኪሳካላቸው ደጋግመው ይወድቃሉ፣ ለሚገጥማቸው አደጋ እራሳቸው ያዘጋጃሉ፣ ከስህተታቸው እንዴት እንደሚማሩ፣ እንዴት ጥፋታቸውን እንደሚያስተካክሉ፣ እንዴት ሃላፊነት መውሰድ እንደሚችሉ በሚገባ ያውቃሉ። ማናችንም ሁለት ወሳኝ ድምፆችን በአዕምሯችን ውስጥ እናስተጋባለን። አንደኛው "አሁን የሚጠቅመውን ብቻ አድርጉ፣ ቀላሉን ምረጡ፣ አደጋ ሽሹ፣ አሁን ደስታ የሚሰጣችሁን ብቻ አድርጉ፣ ህይወትን እንደአመጣጧ ኑሯት" የሚል ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ "ዛሬ ጠንክራችሁ ስሩ፣ ዛሬ አትተኙ፣ እራሳችሁን ለአደጋ አጋልጡ፣ እራሳችሁን ፈትኑት፣ እራሳችሁን ወደፊት ግፉት፣ እራሳችሁን ምቾት ንሱት፣ ህይወትን በውጣውረድ ውስጥ ኑሯት።" የሚል ድምፅ ነው። የትኛውን እየሰማችሁ ነው? በየትኛው እየተመራችሁ ነው? በየትኛው ቁጥጥር ስር ናችሁ?
አዎ! ጀግናዬ..! ጠቃሚውን ድምፅ አስተጋባ፣ አሻጋሪውን ሃሳብ ኑረው፣ ነገህን የሚያስተካክለውን የውስጥ ንግግር ደጋግመህ አዳማጠው፣ ወጥነት እንዲኖርህ የሚያደርግህን፣ ዋጋህን የሚጨምረውን፣ ወደ ህይወት አላማህ የሚያስጠጋህን ድምፅ በሚገባ ተከተለው። በህይወት ሁሌም ልታዳምጠው የሚገባው ሰው እራስህን ነው፣ በህይወትህ በሙሉ ሊመራህ የሚገባው የገዛ አላማህ ነው። በውጫዊ ጫጫታ አትረበሽ፣ በውጫዊ ጫና አትሰበር፣ በሚናፈሰው ወሬ ሁሉ አትታወክ። አዕምሮህን ጠብቀው፣ አስተሳሰብህን ከበካይ አስተምህሮዎች፣ ዋጋህን ከሚያሳንሱ ትርክቶች ጠብቀው።
የራስህን ህልም መገንባት ካልጀመርክ ዘመንህን በሙሉ የሰው ህልም እየገነባህ እንደምትኖር እወቅ። በየአቅጣጫው የሚመጡ ፈተናዎች እንዲያጠነክሩህ ካልፈቀድክ እስረኛ አድርገው ያስቀምጡሃል።
አዎ! የምትከተለው መርህ፣ አምነህበት የምታከናውነው ተግባር፣ ወስነህ የገባህበት ስራ የህይወት አቅጣጫህ ዋና ቁልፎች ናቸው። ጥበቃህን ግታው፣ ጊዜህን ማባከን አቁም፣ በቀላሉ መታለል ይብቃህ፣ በጊዜያ ደስታ መደለል ይበቃሃል። ማቆም ያለብህን አቁመህ እራስህ ላይ መስራትን ጀምር፣ መለየት ያለብህን ሰው ቆርጠህ ተለየው፣ መሆን የምትመኘውን ሰው ጊዜ ሳታጠፋ አሁኑኑ መሆን ጀምር። እራስህን በመሆንህ ያጣሀው ላይ ሳይሆን የምታገኘው ላይ አተኩር። ወቀሳ ሁሌም የውድቅህ መሰረት ነው። ውጤት ከፈለክ ሰበብ ማብዛት አቁም፣ ለውጥን ከተመኘህ ሃላፊነት ውድ። እራስህ ላይ አተኩር፣ እራስህ ላይ ስራ፣ ለወደፊትህ አሁኑኑ ዋጋ መክፈል ጀምር። በከባዱ ተግባር ህይወትህን ቀላል አድርገህ ተገኝ።
═════════❁✿❁ ═════════
💪💯 ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!👌የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/yafekerbet