በሂሳብ አታፈቅሪም!
በሰውነት ውስጥ የመውደድ፣ የማፍቀር፣ የመወዳጀት ፀጋ አብሮ ተሰቶናል። ነገር ግን አስበን፣ አውጥተን፣ አውርደን፣ አገናዝበን፣ ተገንዝበን አንወድም። አንዳንዴ ስላንተ አስባ የማታውቅን ሴት ከልብህ አፍቅረህ፣ መናገር አቀቶህ፣ ምላስህ ተሳስሮ፣ ማንነትህ ተቀያይሮ ልትገኝ ትችላለህ። የሆነ ጊዜ መፈጠርሽንም የማያቅ ሰው ወደሽ እርሱን ጥበቃ ሌላውን ህይወትሽን የምትረሺበት ጊዜ ሊፈጠር ይችላል። ፍቅር ሂሳብ አይደለም፤ እንዲሁም ሰቶ መቀበልም አይደለም። ባላሰብሽው መንገድ ከእራስሽ በላይ የምታስቀድሚው ሰው ወደ ህይወትሽ ይገባል፤ ሁሉ ነገርሽን ልትሰጪው ትፈቅጂያለሽ፤ ከጊዜያዊ የደስታ ስሜትሽ ውጪ የሚታይሽ ነገር የለም። በፍቅሩ መዓበል ትወሰጂያለሽ፤ የውቂያኖሱን እንቅስቃሴ የማቆም ሃይል ታጪያለሽ። ፍቅርን ብለሽ መሔድሽ ፍቅርን ለማግኘትሽ ዋስትና አይሆንሽም።
አዎ! ጀግኒት..! በሂሳብ አታፈቅሪም! አመዛዝነሽ የሰው ህይወት ውስጥ አትገቢም። ለዚህም ነው እደማይሆንሽ እያወቅሽ መውደድሽን የማታቆሚው፤ ለዚህም ነው እየተገፋሽ የምትፈለጊበትን ጊዜ በፅናት የመትጠብቂው፤ ለዚህም ነው የደረሰብሽን በደል ሁሉ ችለሽ በፍቅር መታከምን የመረጥሽው። ፍቅር ጥልቅ ስሜት ነው። ታስቦበት የሚደረግ፣ እየታዘዘ የሚኖር፣ በህግና ደንብ የሚመራ አይደለም። ውስጥሽ የተፈጠረው የተለየ ስሜት ፍቅርን ሲጭርብሽ፣ የተለየ ፍላጎትን ሲያስከትል፣ እይታሽን ሲቀይር ትመለከቺያለሽ። በሂሳብ ከመወዳጀት ታቀቢ፤ ይህን ስላለው፣ ያንን ስላለው፣ ይህንን ስለሚያደርግለኝ ከሚል በመስፈርት የተቃኘ ፍቅር ተላቀቂ። በእውነተኛው ስሜትሽ ስትመሪ የእውነት ፍቅርን መኖር፣ በፍቅር መሞላት፣ የፍቅርን ትርጉምም መረዳት ትጀምሪያለሽ።
አዎ! ጀግናዬ..! ፍቅር በፊት ያስቀመጥካቸውን መስፈርቶች አስጥሎ፣ ለእራስህ የሰጠሀውን ክብር አሳንሶ፣ በማትጠብቀው ሰዓት የማይሆን ሰው ላይ ቢጥልህም ማፍቀርህን ላታቆም ትችል ይሆናል፣ እንደማታገኛት እያወክም ከውስጥህ ለማውጣት ይከብድሃል። ለዘመናት ከአንድ ሰው ውጪ ሌላ መመልከት ያልቻሉ፣ በአንድ ሰው ፍቅር የታሰሩ፣ እራሳቸውን የሰወሩ፣ ማንነታቸውን ያስገዙ ሰዎች አሉ። እራሳቸውን መቆጣጠር ሲኖርባቸው ማንነታቸውን በሙሉ የሚሰማቸው ፍቅር እንዲቆጣጠራቸው ያደርጋሉ፤ ህይወታቸውን ቀምቶ በበዶ እንዲያስቀራቸው፣ በጭንቀት ብዛት ሰውነታቸውን እንዲያሳጣቸው ይፈቅዳሉ። የማያፈቅርህን ሰው ታፈቅራለህ ያምሃል፤ ከልብህ ያፈቀርከው፣ በሙሉ ልብህ ያመንከው ሰው ይከዳሃል ይባስ ትታመማለህ። ነገር ግን ይህን አስብ፣ መዝነህ ያልጀመርከው ፍቅር መዝኖ አይከፍልህም፤ እውነት ስታፈቅር አለመፈቀር፣ መከዳት፣ መገፋት አብሮ ሊመጣ እንደሚችል አስታውስ። ከልብህ ወደህ ብትጎዳ፣ በሰውነትህ አፍቅረህ ብትታመም የእውነት ፍቅርን አይተሃልና ዳግም ምላሹን በመጠበቅ እራስህን አታድክም፣ እራስህን አታሳምም። በምትኩ ለአዲሱ የህይወትህ ምዕራፍ እራስህን አዘጋጅ።
═════════❁✿❁ ═════════
💪💯 ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!!👌የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/yafekerbet