በመተሃራ አካባቢ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ ‼️
በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፥ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳና በመተሃራ አካባቢ ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡
ትናንት ከምሽቱ 4፡41 ላይም በመተሃራ ከተማ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
ይህም ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛው መሆኑን ጠቅሰው ፥ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን አስረድተዋል።
በአካባቢው የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው ÷ ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡
በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር በበኩላቸው÷ከምሽቱ 4፡41 የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ንዝረቱ መቆየቱን አንስተዋል።
እስከ ሌሊቱ 7 ሰዓት ድረስም በአካባቢው የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ተናግረዋል።
ትናንት ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢም በፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ይታወሳል።
ክስተቱ በቀጣይ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳያስከትልም የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላት በጉዳዩ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።