ትራምፕ ለካፒቶል ዓመጽ ሁከት ቀስቃሾች ይቅርታ አደረጉ‼️
ትራምፕ በመጀመሪያ ቀን የስልጣን ዘመናቸው በካፒቶል ሂል ተፈጥሮ በነበረው አመጽ የታሰሩትን ሁሉ እንደሚፈቱ አስታውቀዋል፡፡
ሁሉንም ሁከት ፈጣሪዎች ነፃ ያወጣ እና በአሜሪካ ታሪክ ትልቁን የወንጀል የምርመራ ስራ የሰረዘ ይቅርታ አስተላልፈዋል።
ሰኞ ዕለት የሰጡት ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ አንዳንድ እስረኞች ከጠየቁት የመንግስት የገንዘብ ካሳ ክፍያ ውጭ ሁከት ፈጣሪዎቹ እና ደጋፊዎቻቸውን ሲጠይቁ የነበሩትን ነገሮች በሙሉ የሰጠ ነው ማለት ይቻላል።
ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በዋይት ሃውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "እነዚህ ሰዎች በእስር ቤት ዓመታትን በመጥፎ ሁኔታ አሳልፈዋል።
"አስጸያፊ እስር ቤት ነው። በጣም አሰቃቂ ነበር። ኢሰብአዊ ነው" ብለዋል።
በርከት ያሉ በሁከቱ የተያዙ ሰዎች በታሰሩበት በዋሽንግተን ዲሲ እስር ቤት፤ በተከሳሾቹ እና በደጋፊዎቻቸው በሚዘወሩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ብዙዎች ደስታቸውን ገልጸዋል።
ማክሰኞ የተለቀቀው የፕራውድ ቦይስ መሪው ኤንሪኬ ታሪዮ እናት ስለልጇ በመደበኛነት መረጃዎችን ስታጋራ ቆይታለች።
"የእኛ ፕሬዝደንት ልጄን እና ለሌሎቹም ሕይወታቸውን መልሰዋል! እንደገና መኖር ይችላሉ! እንደገና ንጹህ አየር ይተነፍሳሉ! እንደገና የፀሐይ ብርሃን ያገኛሉ" ስትል ዙኒ ታሪዮ 22 ዓመት ተፈርዶበት በፕሬዝዳንቱ ይቅርታ በነጻ ስለተለቀቀው ልጇ ጽፋለች።