👀በኢትዮጲያ የአዞ ስጋ ሽያጭ ሊጀመር ነው፡፡
የአዞ ስጋን የሚያዘጋጅ እና የሚሸጥ ምግብ ቤት በአርባምንጭ ሊከፈት መሆኑን ጣቢያችን ሰምቷል፡፡
የአርባምንጭ አዞ እርባታ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዳኜ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በሰጡት ማብራሪያ፤ በአርባምንጭ ከተማ የአዞ ስጋ ምግብ ቤት ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።
የውጪ ሃገር ቱሪስቶች የአዞ ስጋ ለመመገብ የሚጠይቁ መሆኑን የገለፁት አቶ ዳዊት፤ ጥናት ተደርጎ ከአንድ ዓመት በኋላ ሬስቶራንቱን ለመክፈት እንደታሰበም ተናግረዋል።
የውጭዎቹ ቱሪስቶች ጋር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ዳዊት አንስተው ፤ አሁን ላይ በሃሳብ ደረጃ ነው ያለው ጉዳዩ ወደተግባር አልተገባም ብለዋል፡፡
በአካባቢው አዞዎቹን የሚንከባከቡ ሰዎች የአዞ ስጋ እንደሚመገቡ የሚናገሩት አቶ ዳዊት ይህም በስፋት እንደተለመደ እና አዲስ ነገር እንዳለሆነ አስተውሰዋል፡፡
የአዞ ስጋ በጣም ጣፋጭ እና መድሃኒትም መሆኑንን በጥናት አረጋግጠናል እናም በቅርቡም የአዞ ስጋ ሽያጭ በይፋ እንደሚጀመርም ገልጸዋል፡፡
2ሺ5መቶ ኦዞዎች እንዳሏቸው እና አሁንም ሰፋ ባለ መልኩ እየተፈለፈሉ መሆኑን አቶ ዳዊት ተናረዋል፡፡
@seledadotio