" ተኩስ ተከፍቶብኝ መኪናዬ ላይ ጉዳት ደርሷል " - አቶ ሰለሙን መዓሾ
" መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " - አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት
" ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " - ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ማምለጣቸውን ተሰምቷል።
የጊዚያዊ አስተዳደሩ የማእከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ ባለፈው እሁድ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከስራ ባለደርቦቻቸው ጋር ከአክሱም ወደ መቐለ ሰጓዙ የግድያ ሙከራ እንደ ተቃጣባቸውና ከግድያ ሙከራው እንደተረፉ ተናግረዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከአክሱም ወደ መቐለ ሲመለሱ ማይቅነጣል ፈላፍል በተባለ ቦታ ሲደርሱ መኪናቸው ላይ ተኩስ እንደተከፍተባቸው ገልጸዋል።
ለጊዜው እነማን እንደተኮሱባቸው ማንነታቸውን / የታጣቂዎችን ማንነት ማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸው በተተኮሰባቸው ጥይቶች መኪናቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል።
በጥይት የተመታው መኪናቸውን የሚያሳይ ፎቶም ይፋ አድርገዋል።
በመኪናው ውስጥ ከእሳቸው በተጨማሪ ጥበቃቸው እና የመኪናው ሹፌር ነበሩ።
ዋና አስተዳዳሪው የደረሰባቸው አካላዊ ጉዳት እንደሌለ አረጋግጠዋል።
እሁድ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም በዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የመግደል ሙከራ መደረጉ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኃላ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ማይቅነጣል ወረዳ ስልክ ቢደውልም ጉዳዩ የሚያረጋግጥ አካል አልተገኘም ነበር።
የዞኑ መቀመጫ ወደሆነችው አክሱም የሚገኝ ፓሊስ ማዘዣ ስልክ ቢደወልም የተጣራ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
ይህ በእንዲህ እያለ የመግደል መከራ ተቃጥቶበታል የተባለው ቦታ የሚያስተዳድረው የማይ ቅነጣል ወረዳ " ጉዳዩ አልተፈፀመም " የሚል መግለጫ አውጥቷል።
የማይቅነጣል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ተክለሃይማኖት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ደግሞ ፣ ጉዳዩን ከወረዳው የጸጥታና ፖሊስ አባላት ማጣራታቸውን ገልፀው፣ " መረጃው ከእውነት የራቀ ነው። የተኮሰበት ሰው የለም " ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ " በአከባቢው አለ ጉዳዩ ፈፅሞታል " ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተደጋግሞ የተጠቀሰው የትግራይ ሰራዊት አርሚ 60 አዛዥ ጀነራል ህንፃ ወ/ጊዮርጊስ እሳቸው የሚያዙት በፀሃፊዎቹ የተገለፀው ሰራዊት በአከባቢው እንደሌለ በመግለፅ " ፓለቲከኞች የልዩነታችሁ ጣጣችሁን እዛው ጨርሱት ወደ ሰራዊቱ አታጋቡት " ሲሉ ተጠምደዋል።
ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዚያት መሰል የግደያ ሙከራዎች በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሹማመንት በየነ መኩሩ ፣ ነጋ ኣሰፋ ፣ ሰሎሙን ትኩእ እንዲሁም በአክሱም ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር መደረጋቸው የተነገረ ቢሆንም እስካሁን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተጣርተው የተወሰደ እርምጃ የለም።(tikvah )
@Sheger_press