እስራኤልን የሊባኖስን የእርቅ ስምምነት 52 ጊዜ ጥሳለች ስትል ፈረንሳይ ከሰሰች
የእስራኤል ይኔት ኒውስ እንደዘገበው የእስራኤል ጦር ከሄዝቦላህ ጋር የገባውን የተኩስ አቁም ስምምነት 52 ጊዜ ጥሷል፣ ከነዚህ መካከል ቅዳሜ ሶስት የሊባኖስ ሲቪሎችን የገደለውን ጥቃት ፈረንሳይ በማንሳት አስታዉቃለች፡፡የእስራኤል ጦር ሃይል በሂዝቦላ ለተፈፀመባቸው ጥሰቶች ምላሽ ነው በማለት ጥቃቱን ትክክለኛ ሲል አስተባብሏል፡፡
ነገር ግን የፈረንሳይ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ይኔት ኒዉስ እንደዘገበዉ የእስራኤል ጦር የስምምነቱን ተገዢነት ለመከታተል የተሰጠውን ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ሳያማክር እርምጃ ወስዷል።አንድ የፈረንሳይ ባለስልጣን ጠቅሶ “ሊባኖሶች የተኩስ አቁምን ለማስቀጠል እና ሂዝቦላ በደቡብ ሊባኖስ ውስጥ መገኘቱን እንደገና እንዳይቋቁም ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ናቸው ፣ ግን ይህንን ለማረጋገጥ ጊዜ ሊሰጣቸው ይገባል” ሲል የፈረንሳይ ባለስልጣን ተናግረዋል ።
የእስራኤል ባለስልጣናት ድርጊታቸውን ተከላክለዋል፣ነገር ግን የአለም አቀፍ ክትትል ኮሚቴ ከሰኞ እና ማክሰኞ በፊት ሙሉ በሙሉ ስራ እንደማይጀምር እና እስከዚያው ድረስ ጥቃታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።የእስራኤል ወታደሮች "የተከለከሉ ቦታዎች ናቸው" በማለት በሊባኖስ የሚገኙ ሰዎች ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ እንዳይጓዙ በድጋሚ አስጠንቅቀዋል።የሊባኖስ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የፈረንሳዩ የመከላከያ ሚኒስትር ሴባስቲያን ሌኮርኑ የተኩስ አቁም አፈፃፀም ላይ ለመነጋገር ሰኞ ቤይሩት ገብተዋል፡፡
@Sheger_press