በምሥራቅ ጎጃም በድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ 16 ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ቤተሰቦች ተናገሩ
በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሐሙስ የካቲት 13/2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ አራት ቤቶች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 16 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጥቃቱ በዞኑ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገሽ ቀበሌ (ሐሙስ ገበያ) በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሐሙስ ረፋድ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በሦስት ሱቆች እና ሻይ ቤት ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
"[ድሮን] ስትዞረን ነበር" ያሉ አንድ የዓይን እማኝ ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ በግምት 100 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ የጥቃቱ ሰለባዎች መንገድ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህፃናት፣ ገበያተኞች እና ሻይ እየጠጡ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።
ከፍተኛ ፍንዳታ መፈጠሩን የሚናገሩት እማኙ፤ ወዲያው "አካባቢውን አቧራው፤ የቤቱ ፍርስራሽ በጭስ" እንዳፈነው እና ድንጋጤ እና ግርግር እንደተፈጠረ ገልፀዋል።
ሌላ የዓይን እማኝም በፍንዳታው አካባቢው በአቧራ ጭስ መሸፈኑን ጠቅሰው፤ በስፍራው ለመተያትም አስቸጋሪ እንደነበር ተናግረዋል።
በደቂቃዎች ውስጥ ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው ቤቶች ደርሰው የቆሰሉ ሰዎችን እንዳወጡ እና አስከሬን እንዳነሱ የተናገሩት ሌላ የዓይን እማኝ "የሚጫወቱ ህፃናት እና ቆርቆሮ ሊገዙ የመጡ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል።
Via BBC News Amharic/meseret media
@sheger_press