❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፳ (20) ቀን።
❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት ለአንዱ #ከሌዊ_ነገድ_ከአሮን_ትውልድ ለሆነው #ለቅዱስ_ሐጌ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከንግሥት_ታውፊና ከመታሰቢያዋ፣ #ከአውጋንዮስና #ከማድዮስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ነቢዩ_ቅዱስ_ሐጌ፦ እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው። ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ ወላጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ወደ ባቢሎን አገር ተማርከው ሔዱ ዳርዮስ የተባለውም ኵርዝ በነገሠ ጊዜ በሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ይህ ነቢይ ትንቢት ተናገረ።
❤ የእስራኤልን ልጆች ወደ አገራቸው ይገቡ ዘንድ ኵርዝ ዳርዮስ በአሰናበታቸው ጊዜ እነርሱም ከገቡ በኋላ ቤተ መቅደስን ከመሥራት ቸለል በአሉ ጊዜ እነርሱ ግን በአማሩና በተሸለመ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ነበርና እንዲህ አላቸው። "ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ አለ የኔ ቤት ፈርሷል እናንተ ግን ሁላችሁም ቤታችሁን ታጸናላችሁ" አላቸው። "ስለዚህ ከምድር በላይ ያለች ሰማይ ዝናም ለዘር ትነሣለች ምድርም ፍሬዋን አትሰጥም" አላቸው።
❤ ከሕዝቡም ደናጎቻቸው ሰምተው እጅግ ፈሩ የእግዚአብሔርንም መመስገኛ ቤት እንደሚገባ መሥራት ጀመሩ። ይህም ጻድቅ ነቢይ ሰባ ዓመት ያህል ኖረ የትንቢቱም ወራት ክብር ይግባውና ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። ከዚህ በኋላም በሰላም በፍቅር ታኅሣሥ20 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሐጌ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ20 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለሐጌ_ዘተነበየ_በፆታ። ሚጠተ ፂዉዋን ሕዝብ ወሕንፀተ መቅደስ ድኅረ ንስተታ። በእንተ ማርያምኒ ዘተደንገለት በመንታ። ለቤት ደኀሪት እንተ ትገብር ድሉታ። እምነ ቀዳሚት ይቤ ይኄይስ ትርሲታ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የታኅሣሥ 20።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL