❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን #ለማኅበረ_ዴጔ_ለሦስት_ሺህ_ጻድቃን እንደ ቅዱሳን ኄኖክና ዕዝራ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው፣ ለከበሩ ደናግል #ለቅድስት_ሶፍያ_ልጆች ለቅድሳት #ለጲስጢስ_ለአላጲስና_ለአጋጲስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ስሙ መርቅያኖስ ለሚባል ለጣዖት ለሚሰግድ ለሮሜ ንጉሥ ልጅ ለከበረች #ለቅድስት_ኦርኒ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል፣ ለከበረች #ቅድስት_ጤቅላ ከእርሷ ጋር ከሚኖሩ አራት ደናግል ጋር ፎላ በሚባል ኃጥእ ቄስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋዳይ ለሆነ ለመነኰስ ለከበረ #አባ_አክርስጥሮስ ለዕረፍት በዓልና ለመለኮትን ነገር ለሚናገር ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመታሰቢያ በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ አገር አርባ ሰባተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ሚናስ ዕረፍትና #ከቅድስት_ኦርኒ_ማኅበር ከሆኑ #ከዐሥራ_ሦስት_ሺህ_ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ማኅበረ_ዴጔ፦ ማለት የደጋጎች አገር ማለት ነው። የደጋጎች አገር የተባለበት ምክንያት ብዙ ሺህ ቅዱሳን ተሰብስበው ስለሚኖሩበት ነው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በትግራይ ክልል በአክሱም አውራጃ ከአክሱም ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ በሚወስደው መንገድ ዐሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ ነው፡፡ ከገዳሙ ተያይዞ የተላከልን ዘገባ እንደሚያስረዳው ቤተ ክርስትያኑ በ39ዓ.ም እንተተተከለ በግልፅ ያስረዳል። ይኸውም መጽሐፈ ሱባኤ በተባለው በመሪ ኤ.ኤም የተዘጋጀው መጽሐፍ ከምዕራፍ 11 በገጽ 132 ላይ አቴዥን ሕንደቼ ንግሥት ነገሥታት ዘኢትዮጵያ ሆና በነገሠች በ39ዓ.ም በአንደኛው ዓመተ መንግሥትዋ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ በ40ዓ.ም ማኅበረ ጻድቃን ዴጔ ገብቶ ሲያስተምርና ሲያጠምቅ ሰምታ መኳንንትና መሳፍንትን አሰከትላ መርዌ ወረደች ይላል።
❤ በዚህም ንግሥቲቱ ቅዱስ ማቴዎስ አግኝታ "ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ የባሕሪ ልጅ መሆኑ አውቃለሁ ይሁን እንጂ ዳግመኛ ከእግዚአብሔር ከድንግል ማርያም መወለዱን አላውቅም ነበር አሁን ግን በትምህርትህ መንፈስ ቅዱስ ስለ ገለጸልኝ አጥምቀኝ" አለችው። ቅዱስ ማቴዎስም ንግሥቲቱን ካጠመቀ በኋላ ቀጥሎ መኳንንቱን፣ መሳፍንቱን የጦር ሠራዊቱን ሁሉ አጥምቋቸዋል ይላል፡፡ አያይዞም ንግሥቲቱ ቅዱስ ማቴዎስን ይዛው ወደ አክሱም ተመለሰች፣ ልጆችዋንና ቤተሰቦችዋንም አስጠመቀች እንዲሁም አክሎስ የሚባል ባልዋም አምኖ ተጠመቀ። ቅዱስ ማቴዎስ ከዚህ በፊት የነባቡና የናግራንን ህዞቦች አጥምቆ ከዚህም በኋላ የጻድቃንን ዴጔ ማህበር አቋቁሞ በጌታችን ስም በየወሩ በ29ቀን እየተሰበሰቡ ጽዋ እንዲጠጡ አድርጓቸው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዷል፡፡
❤ በ365ዓ.ም በአስፍሕ ወልደ አብርሃም ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘመነ መንግሥት "ሮምያ" ከምትባል መንደር ቅዱሳን "ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁአን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የነርሱ ናትና" ያለውን ዳግመኛም "አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም" ብሎ ጌታችን የተናገረውን አስበው ቅዱሳን የዚህም ዓለም ጣዕም ጥቅም ንቀው አገራቸውን ትተው መንነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን በአክሱም ከተማ በስተሰሜን በሐውልቱ ጀርባ ቤተ ቀጠንት በሚባል ስፍራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል እንደ ተቀመጡ በዚያም ምቾትና ድሎት ስለተሰማባቸው "ለዚህ ለዚህማ አገራችንን ለምን ትተን መጣን? ስለዚህ ሱባዔ ገብተን በጾም በጸሎት ተወስነን የምንሄድበትን ቦታ በረከተ ነፍስ የምናገኝበትን ስፍራ እግዚአብሔር እንዲያሳየን እናመልክት" ብለው ሱባዔ ገቡ ጾም ያዙ፡፡ ከሱባዔውም በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻላቸው ግማሾቹን እያንዳንዳቸው የሚኖሩበትን በዓት አመልክታቸው፣ በዚያም በጾምና በጸሎት ጸንተው እንዲኖሩ ነገረቻቸው፡፡ ሦስት ሺህ ያህሉን ደግሞ ከላይ ወደጠቀስነው ሥፍ ሄዱ፡፡ ከእነርሱ የተቀሩት ደግሞ ወደ ቆየፃ ሓባር፣ ተድባ፣ አኮርየን፣ ተንስሓ፣ ደብረ አንሳ ወደ ተባሉ ቦታዎች ሄደዋል፡፡ ተጨማሪ ሦስት ሺህ የሚሆኑት ደግሞ እዚያ ከነበሩት ጋር ተደመሩ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ እነዚህ ቅዱሳን "ከሁሉ ፍቅር ይበልጣል" የሚለውን ጠብቀው በእምነት በፍቅር በአንድነት ጸንተው በየሣምንቱ እሁድ እሁድ ተዝካረ ሰንበትን ጠብቀው ማኅበር ሲጠጡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅራቸው አይቶ በአምሳለ ነዳይ ደሀ መስሎ በመካከላቸው ተገኘ። ከነርሱ ጋርም አንድ ማኅበርተኛ ሁኖ እንዲታወቅ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ፈቀዱለት አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህልም ከነርሱ ጋር ሳይለይ ቆየ በዚሁ ጊዜ "ለእኔም ተራ ስጡኝ እንደ አቅሜ ዝክር ላውጣ"አላቸው። እነርሱም ግን "አይሆንም አንተ ደሀ ነህ ከኛ ጋር ሁነህ በዓሉን አክብር እንጂ ምን አለህ እና ነውን" አሉት፣ እርሱም "አይሆንም ስጡኝ እንጅ አላቸው" እርሱም ካልክማ ብለው ቀን ወስነው ሰጡት ቀኑም ጥር29 ነበር። ከማኅበርተኞቹ መካከል "ሣይዳን" የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህም አሳላፊ ወይም ሙሴ ማለት ነው። ይህም ሰው እንግዳና ድሀ ሰው ፈጽሞ አይወድም ነበር፣ ጌታችንም ከማኅበርተኞቹ መካከል ሲገኝ ደሀ መስሎ ስለ ነበር በጣም ይጠላው ነበር።
❤ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከነርሱ ጋር ሲቀመጥም አንድ ቀን ስኳን አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፣ ሆኖም የጌታችን ማኅበር ደረሰ፣ እንደ ማኅበሩ ሥርዓት አሳላፊው ጠርቶ "ጋኖችን እጠብልኝ አለው" አሳላፊው "ቤትህ የማይታወቅ ከየት አምጥተህ ማኅበር ልታደርግ ነው" ብሎ አናንቆ ተመለከተው ጌታም አንድ እረኛ ጠርቶ "አንተ ልጅ ከብቶችህን እኔ እጠብቅልሃለሁና ውኃ አምጣልኝ" አለው፣ ልጁም ገምቦውን ይዞ ትንሽ ወጣ እንዳለ ጌታ ዘወትር ከሚቀመጥበት ድንጋይ ላይ ሆኖ ዘንጉን ወደ ልጁ አቅጣጫ ወረወረው፣ ዘንጉንም ከልጁ ፊት ሂዶ ተተከለ ልጁንም ጠርቶ ዘንጉንም ንቀለው አለው ልጁም ዘንጉን ቢነቅለው ውኃ ፈለቀ "ከርሱ ቀድተህ አምጣልኝ" አለው። ልጁም ከዚህ ውሃ ቀድቶ አመጣለት ጌታም ልጁ ባመጣው ውኃ ጋኖቹ ቀድቶ አጠባቸው፣ በበዓሉ ቀን ማኅበርተኞቹ ምን ሊያበላን ነው ምን ሊያጠጣን ነው ሳይሉ ሁሉም ተሰበሰቡ ጌታችንም በፊታቸው ጋኖቹን ቢባርካቸው የወይን ጠጅ ሞልተው ተገኙ። ቀድቶ ቢሰጣቸውና ቢቀምሱትም በጣም ግሩም ጣፍጭ ስለነበር እጅግ አደነቁ፣ እነርሱም ጌታችን ከጻድቃን አንዱ ስለመሰላቸው ከእግሩ ላይ ወድቀው "እስካሁን ድረስ ሳንበድልህ አልቀረንምና ይቅር በለን" ብለው ለመኑት ተነሡ ብሎ ካስነሳቸው በኋላ "እናንተ አልበደላችሁም፡ በደለኝ አሳላፊያችሁ ነው አንድ ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ አልሰጠኝምና አፋራርዱኝ" አላቸው። ነገር ግን ሙሴው የማያፍር ደፋርና ርጉም ስለነበር ሲጠይቁት "ይህ ሰው ጌታችንን በልቶ አልበላውም ጠጥቶ አልጠጣሁም የሚል ስለሆነና ስለማይጠግብ ነው እንጂ እንዲያውም ለናንተ አንድ አንድ ዋንጫ ሲሰጣችሁ ለእርሱ ሁለት ሁለት ነበር የሚሰጠው" ብሎ የሐሰት ቃል መለሰ።