❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮያዊያኑ_ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚገኘው #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ጽጌ_ሰፍኣ ለመሰረቱት ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ደቀ መዝሙርቶቻቸው (ልጆቻቸውን) ከሰማይ ስንዴና ወርቅ በማዝነብ ውሃውን በመባረክ ወይን አድርገው ይመግባቸው ለነበሩ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_እንድርያስ_ዘደብረ_ጽጌ_ሰፍኣ ለዕረፍት በዓል፣ ለመካኖች ልዩ ቃል ኪዳን ለተሰጣቸው ለታላቁ አባት ለሰማዕቱ #ለአቡነ_ሲኖዳ ለፍልሠተ ዐፅማቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_እንድርያስ፦ የእናታቸው ስም ቅድስት ዓመተ መንፈስ ቅዱስ የአባታቸው ስም ቅዱስ ዘአማኑኤል ይባላል። የተወለዱትም ትግራ እንደርታ አካባቢ ነው። እናትና አባታቸው ልጅ ስሌላቸው ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እየጸልዩ እናታቸውም "አንተ ደስ የሚያሰኝ ልጅ ካልሰጠኸኝ ማኅፀኔን ዝጋ" ይሉ ነበር። የእመቤታችንንም ዝክር በየወሩ ይዘክሩ ነበር። እመቤታችንም አንድ ቀን ተገልጻ "ደስ የሚያሰኝ ልጅ ትወልዳላችሁ የሚወለደውም እኔ በተወለድኩበት ቀን ነው" አለቻቸው። አባታችን ልክ ግንቦት አንድ ቀን ሲወለዱ በእናት በአባታቸው ቤት ብርሃን ወረደ። አርባ ቀን ሲሞላቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ሊያስነሷቸው ወሰዷቸው ሲጠመቁም አባታችን "በአብ ስም አምናለሁ በወልድ ስም አምናለሁ በመንፈስ ቅዱስ አምናለሁ" አሉ። ስመ ክርስትናቸውም መሐረነ እግዚእ ተባሉ።
❤ አቡነ እንድርያስ የስለት ልጅ ስለ ነበሩ 3ዓመት ሲሆናቸው ወደ ቤተ ክርስቲያም አስገባቸው። እርሷቸው ቀን ቀን እያገለገሉ እየተማሩ ሌሊት ሌሊት እየጸለዩ ይሆሩ ነበር እመቤታች በሌሊት ሲጸልዩ ተገልጻ በክንፍ ጋረደቻቸው። ከዚያም ዕድምያቸው ለጋብቻ ሲደርስ እናትና አባታቸው "እናጋባህ" አሏቸው እርሳቸው ግን "አልፈልግም" ብለው በሌሊት ተነስተው ወደ ደብረ ፀሎላ ገብተው በአባ ገብረ ክርስቶስ እጅ በ12ዓመታቸው መነኰሱ። የምንኲስና ስማቸውም አባ እንድርያስ ተባሉ። በዚያ ጊዜ ዲቁንና ክህነት የሚሰጥ ጳስስ በኢትዮጵያ ስላልነበረ አበምኔቱሙ አባ ገብረ ክርስቶስ "ዲቁንናንና ክህነት እንድትቀበል ወደ ግብጽ እንሒድ" አሏቸው። አባታችን "አይሆኑም" ሲሉ ጌታችን በሌሊት ተገልጾ "እንድርያስ ወዳጄ ለምን እቢ አልክ እኔ ምርጬሃለሁና" አላቸው አባታችን ጠዋት ተነስተው "ኑ እሒድ" አሏቸው። ከዚም ወደ ግብጽ ሒደው ዲቁንናንና ክህነት ተቀብለው ወደ ገዳማቸው ተመለሱ።
❤ አንድ ቀን አባታችን ሲቀድሱ ከምድር አንድ ሜትር ከፍ ብለው እርሳቸው የቆሙበት ቦታ ውሃ አፈለቀ። ይህን ያዩ መነኰሳት ለአበምኔቱ ለአባ ገብረ ክርስቶስ ነገራቸው አበምኔቱ መጥተው የፈለቀው ውሃ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ አቡነ እንድርያስ አስጠርተው "አንተ ከዛሬ ጀምሮ ከእኛ ጋር ለሥራ መውጣት የለብህ ስእኛ ጸልይን እንጂ" አሏቸው እርሳቸው አይሆኑም ብለው ከእዛ ገዳም ወጥው "ወደ ኢየሩሳሌም ሔጄ ጌታ የተጠመቀበትን ማየ ዮርዳኖስ አያለው" ብለው ከኢትዮጵያ ተነስተው ወደ ኤርትራ አዲ ሞገስ ወደሚባል አካባቢ ሲደርሱ አንድ ታምነ እግዚእ የሚባል ገበሬ "አባቴ የንስሐ አባት ሁኑኝ" አላቸው። አባታችን "በአገራችሁ ካህን የለም እንዴ?" አሉት እርሱም "አዋ የለም" አላቸው አባታችንም ሕዝቡ አስተምረው አጥምቀው ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ጀመሩ። ደብረ ጽጌ ሰፍኣ ሲደርሱ ጌታ ተገልጾ,"ይህን ቦታ ዳግማዊ ኢየሩሳሌም አድርጌልሀለው ውሃውም የዮርዳኖስ ውሃ ይሆንልሃል እና ከዚህ አትህድ" አላቸው።
❤ አባታችንን አቡነ እንድርያስ ተከትለው ወደዚህ ገዳም ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ተማሪዎች ወደ እሳቸው መጡ እነዚህ ልጆቻቸውን አመነኰሷቸው። ለእነዚህ ልጆቻቸው ቀድሞ በመንገድ ላይ አስተምረው ካጠመቁት ገበሬው ከታምነ በእግዚእ እንደ ሰው እየተላላከ እህል የፈጭልላቸው የሚያገለግላቸው ገብረ ኄር የሚባል አህያ ነበራቸው ሰይጣንም ቀንቶ ይህንን አህያ ብገለው ልጆቹ በርሃብ ምክንያት ይበተናሉ ብሎ አስቦ በአንበሳ አድሮ ገደለው። አንበሳው ደግሞ አቡነ እንድርያስ በአንድ መርገም ቃል ገደሉት። ልጆቻቸውም ምግብ ሲያጡ ጥለው ሊሆዱ ሲሉ አባታችን ትዕግስት ይኑራችሁ አላቸው። እነርሱም እንቢ ብለው ወደ ታምነ በእግዚእ ሆዱ። ታምነ በእግዚእ ባለቤቱን "ምግብ አዘጋጂላቸው" አላት እሷም "አቡነ እንድርያስ ሳይመጦ አላዘጋጅ" አለችው እነርሱም እቢ ስላለቻቸው ልጆቹም "እኛ የአባታችን ምክር ስልሰማን ነው የከለከለችን" ብለው ወደ ገዳማቸው ተመለሱ።
❤ አቡነ እድርያስም ልጆቹ ከተመለሱ በኋላ ውሃ የሞሉ እንስራዎች ነበሩና ቢባርኩት የወይን ጠጅ ሆነ። እንደ ገናም "እግዚአብሔር ዘላለም" ብለው ሲጸልዩ ከሰማይ አርያም ስንዴ ዘነበላቸው ያንን ለ14 ዓመታት ተመገብ ይህ ሲያልቅ ደግሞ ወርቅ አዘነቡላቸው ወርቁ በእህል እየለወጡ ተመገበሩ። አባታችን ልጆቻቸውን "እኔ ወደ እግዚአብሔር የምሄድበት ቀን ደርሷል" አሏቸው። ልጆቹም "አንተ ከሆድክ ማን ከሰማይ ስንዴና ወርቅ እያዘነበ ውሃው ወይን እያደረገ ይመግበናል" አሏቸው እሷቸው "እኔ ከሞትኩ በኋላ እናተም ከዐሥር ቀን በኋላ ወደ ትመጣላች እኔ ቦታ ላዘጋጅላችሁ ነው የምሆደው" ብለዋቸው በ126 ዓመታቸው የካቲት 1 ቀን ዐርፈዋል። ልጆቻቸውም እንዳሏቸው በአንድ ቀን በአረማውናን ሰማዕትነት በመቀበል የካቲት 10 ቀን ዐርፈዋል። ከአባታች ከአቡነ እንድርያስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከኤርትራ ደብረ ጽጌ ሰፍኣ ገዳም የተገኘ ማስታወሻ።
✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ሲኖዳ፦ ሲኖዳ ማለት "ታማኝ" ማለት ነው፡፡ ትውልድ አገራቸው ጎጃም ሲሆኑ የሸዋ ባላባት ልጅ ናቸው፡፡ በጎጃም ደብረ ዲማህ አጠገብ ደብረ ፅሞና በተባለው ቦታ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያመልኩት የነበረውን ትልቅ ዘንዶ አቡነ ሲኖዳ በመስቀል ባርከው ከሁለት ሰንጥቀውታል፡፡ ሰዎቹንም አስተምረው አሳምነው አጥምቀው የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸዋል፡፡ ጻድቁ የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓይነት ገድል አላቸው፡፡ ለዘንዶ ምግብ እንዲትሆን ግብር ሆና የተሰጠችውን ሴት ልጅ ከጫካ አግኝተው ዘንዶውን በመስቀላቸው አማትበው ገድለው ልጅቷን አድነዋታል፡፡
❤ በዘመናቸው ነግሦ የነበረው "ሕዝበ ናኝ" የተባለው ንጉሥ በሰዎች ወሬ "ንግሥናዬ ለሌላ ይሰጣል ትላለህሳ" በማለት ጻድቁን እጅና እግራቸውን አስሮ ካሠቃያቸው በኋላ እጃቸውን አስቆረጣቸው፡፡ ነገር ግን ለአቡነ ሲኖዳ እመ ብርሃን የብርሃን እጅ ተከለችላቸው፡፡ በጌቴሴማኒ ያለችው ሉቃስ የሳላትና ስርጉት የተባለችው የእመቤታችን ሥዕል በየጊዜው እየተገለጠች ታነጋግራቸው ነበር፡፡ ንጉሡ በስደትና በግዞት ብዙ እያሠቃያቸው ሳለ መልአክ መጥቶ ዕለተ ዕረፍታቸውን ነግሯቸው እሳቸውም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ጠርተው ከተሰናበቷቸው በኋላ ነው ንጉሡ በኅዳር 17 ቀን አንገታቸውን ያሰየፋቸው፡፡ ከአንገታቸው ውኃ፣ ደምና ወተት ፈሷል፡፡