❤ ጻድቁ በሐይቅ ደሴት የተቀበሩ ቢሆንም ቀድሞ በሚያገለግሉበት በድፍን ምስራቅ ጎጃም ድርቅና ርኃብ ስለሆነ በደብረ ፅሞና ገዳም ይኖሩ የነበሩት አባ መቃርስ ዐፅማቸውን አፍልሰው በማምጣት በደብረ ዲማህ አጠገብ በስማቸው በተሰራው በደብረ ፅሞና ቤተ ክርስቲያን በክብር ሲያሳርፉት ወዲያው ዝናብ ጥሎ ድርቁም ጠፍቷል፡፡ ዐፅማቸውን ተሸክማ ያመጣችው በቅሎም ወልዳለች፡፡ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ሲኖዳ ለማይወልዱ መካኖች እጅግ ልዩ ቃልኪዳን ነው የተሰጣቸው፡፡ መቃብራቸውን እየዞሩ እምነታቸውን እየተቀቡ ገድላቸውን እየታሹ የማይወልዱ መካኖች የሉም፡፡ ከሩቅም ሆነው በስማቸው ተስለው እምነታቸውን ተቀብተው የሚወልዱ በጣም ብዙዎች ናቸው፣ እንኳንስ ሰው ይቅርና ዐፅማቸውን የተሸከች በቅሎም ወልዳለችና!።
❤ የጻድቁ ሌላኛው በስማቸው የተሰየመውና እጅግ ተአምረኛው ታቦታቸው ዛሬም አቡነ ሲኖዳ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከአ.አ 180 ኪ.ሜ ርቆ ከጣርማ በር አልፎ ሞላሌ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ በሰሜን ሸዋ በሚገኘው በዚህ ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በዘመናችንም በጣም በርካታ ተአምራት ይደረጋሉ፡፡ ለጻድቁ የተሰጠችውን የስዕለት በግ ጅብ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ገብቶ ሊበላ ሲል ቀንዱን ነክሶ ደርቆ ሞቶ ሲገኝ በጉ ግን ምንም አልሆነም፡፡ አቃቢቷም እንዲሁ ከትልቁ ተራራ ሥር በትልቅ ቅል ውኃ ቀድተው ሲመለሱ ገመዱ ተበጥሶ ቅሉ ከነውኃው ከትልቁ ገደል ገብቶ ድንጋይ ላይ ቢያርፍም ቅሉ ሳይሆን ድንጋዩ ነው የተሰበረው፡፡ የአካባቢው ነዋሪም "በጉ ጅብ ገደለ፣ ቅሉ ድንጋይ ሰበረ" እያሉ ጻድቁን ያወድሷቸዋል፡፡ ከአባታች ከአቡነ ሲኖዳ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL