የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጥር ወር ምርጥ አሰልጣኝ
ኢትዮጵያ መድንን እየመሩ በጥር ወር ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች በስድስቱ ድል የተቀዳጁት አሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በጨዋታዎቹም ቡድናቸው 10 ጎሎችን የተጋጣሚ መረብ ላይ አሳርፎ 2 ጎሎችን ብቻ በማስተናገድ ከተከታዩ ሀዲያ ሆሳዕና በአምስት ነጥቦች ርቀት ላይ ሆኖ ሊጉን እየመራ የመጀመሪያው ዙር ተጠናቋል። በዚህም በሶከር ኢትዮጵያ ኤዲቶሪያል እና በተከታዮች ምርጫ የድምር ውጤት ከሀዲያ ሆሳዕናው አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እና ከቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ተፎካክረው የጥር ወር ምርጥ አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።