የሸዋል ፍቺ ‼️
የሸዋል ፍቺን አስመልክቶ ከወንድም አዚዝ ጋር የተደረገ ውይይት :—
አዚዝ:— السلام عليكم ورحمة الله
ዘኪ:— وعليكم السلام ورحمة الله وبركاته
አዚዝ:— አብረን ለመወያየት ስለተቀመጥን ደስ ብሎኛል።
ዘኪ:— እኔም በጣም ደስ ብሎኛል ይበል ይቀጥል የሚያስብል ጅማሮ ነው
አዚዝ:— ወደ ርዕሳችን ስንገባ ትንሿ ኢድ የሚባል ጭማሪ(ቢድአ)እንዳለ ታውቃለህ?? በኢስላም ደግሞ ሁለት ኢድ ብቻ ነው ያለው ኢድ አልፊጥር እና ኢድ አል— አደሀ ከዚህ ውጪ ሌላ የጨመረ ስራው ተመላሽ ይሆናል።
ዘኪ:— ወንድም አዚዝ በመጀመሪያ ትንሹ ኢድ(የሸዋል ፍቺ) ሸሪአዊ ሳይሆን ሰዎች በተለምዶ የሚጠያየቁበት የሚዘያየሩበት ቀን ነው።
አዚዝ:— ዒድ እየተባለ ባህል ነው ማለት አይከብድም?
ዘኪ:— በመጀመሪያ በሸሪአ ስያሜ ምንም አይነት ፍርድ የለውም ፍርድ የሚሰጠው የሚሰራው ስራ ታይቶ ነው( የነገርየው ጭብጥና ምንነት ታይቶ ነው) ።
ለምሳሌ :— የሞተ ነገር ፍርዱ ምንድ ነው በሸሪአ?
አዚዝ :— ሀራም ነዋ
ዘኪ:መሞቱ ነው ሀራም ??
አዚዝ :አይደለም መብላቱ ና መሸጡ ነው።
ዘኪ :— መሸጥ እና መብላት የሰው ልጅ ስራ ነው ስለዚህ ሸሪአ ፍርድ ሚሰጠው የሰዎች ስራ ላይ እንጂ በስሙ ወይም በነገሩ ላይ አይደለም ከዚህ የበለጠ ምሳሌ ልስጥህ ኽምር ሁክሙ ምንድነው ??
አዚዝ:— መጠጣቱ ፣ መሸጡ፣ መግዛቱ.....ሁሉ ሀራም ነው እንጂ ኽምር ብቻው ፍርድ የለውም።
ዘኪ:— በትክክል ትንሹ ኢድ ስለተባለ ብቻ ኢድ ይሆናል አይባልም ለምሳሌ ኢድ አደባባይ ይባላል ፣ ኢድ ካፌ ፣ ኢድ ኤክስፖ.. የመሳሰሉት ዒድ የሚል ስያሜ ስላላቸው ብቻ አምስተኛ ስድስተኛ ዒድ ናቸው ማለት ነውን? ?
አዚዝ:— በጭራሽ ምክንያቱም በሸሪአ ኢድ ሚያስብል ነገራቶቸ አይተገበሩባቸውም።
ዘኪ:— ጥሩ መጥተሀል በትን ሿ ዒድ (በሸዋል ፍቺ)በኢድ የሚተገብሩ ተግባራቶችን የሚተገብር ሰው አለ ተክቢራ ፣መስገድ፣ዘካተል ፊጥር ፣ኡዱሁያ፣ለኢድ ነይቶ መታጠብ የመሳሰሉ ተግባራት ይፈፀማሉን?
አዚዝ:— በጭራሽ አይፈፀሙም ነገር ግን ቀን ለይቶ ዘመድ መዘየር ይቻላል?
ዘኪ:ጥያቄውን ወደ አንተ ልመልሰውና በአብዛኛው ጊዜ ሰዎችን የምታገኘውና የምትዘይረው ምን ቀን ላይ ነው?
አዚዝ:— እሁድ ምክንያቱም እኔም የምዘይራቸውም ሰዎች የሚመቻቸው በዚህ ቀን ነው በአጠቃላይ በተለምዶ ሚዘየረው በእረፍት ቀን ስለሆነ ነው ።
ዘኪ:— አይ ይህ የሸዋል ፍቺም ተለምዶ ነው፣ ሰዎች በፈለጉት ቀን መዘየር በሸሪአ ተፈቅዷል፣ የፈለጉትን ይዘው መሄድ ተፈቅዷል ሲፈልጉ በግ ፣ ዳቦ... እኛ ሀገር የተለመደው ብርትኳን ፣ ሙዝ ወዘተ ነው ይህን ጉዳያ ሸሪአው ለዘያሪው ነው የተወው።
* ከዚህ ባለፈ ትንሹ ኢድ ብሎ የጠራው ሰው በጣም ትልቅ ፈቂህ መሆን አለበት ምክንያቱም " ዒድ " ብቻ ሳይሆን ያለው " ትንሹ" የሚል " የትልቁን ዒድ " ክብር እንዳይጋፋ ገደብ አድርጎለታል በሌላ አገላለፅ " ዒድ— አል— ፊጥር " አላህ የደነገገው የኢስላም ትልቅ በአል ነው እያለን ነው።
አዚዝ:— ግንኮ ትንሹ ዒድ በጣም ይደምቃል
ዘኪ:— አንዳንድ ሰዎች እንደ ህፃን ልጅ በግና ዳቦ ከተመለከቱ " ዒድ " የሚለው ነገር ከጭንቅላታቸው ላይ አይጠፋም፣ ዒድና በግ የብርሀንና የቀን አይነት ተዛምዶ ያላቸው እስኪመስል ድረስ በግ ባለበት ሁሉ ዒድ አለ ማለት አይደለም በግ የለም ማለት ደግሞ ዒድ የለም ማለት አደለም።
❇️ በሸሪአ ዒድ ደመቀ አልደመቀም የሚያሰብለው የሰዎች ቁጥር መብዛት መንጫጫት ሳይሆን በዒድ ቀን የሚሰሩ ስራዎች ናቸው ፣ ድምቀቱ ሰው በቤት ውስጥ መብዛት ቢሆን ከኢድ ቀን የበለጠ የሰርግ ቀን ይደምቃል ወይም አንዳንድ ዝግጅቶች ከኢድ የበለጠ የደመቁ ናቸው ነገር ግን በጭራሽ ከዒድ ድምቀት ጋር ሚያወዳደር የለም።
አዚዝ:— ሹክረን ያ ሀቢቢ ‼️
ዘኪ: — ወለከ ያ ሀቢቢ ‼️
https://t.me/sufiyahlesuna