የዘመናች ፈተና ቀስቃሽ - አእመዲን ጀበል
================
አእመዲን ጀበል በግልፅ ከሸይኽ ዐብዱላህ ሀረሪ የጀመረ ዞሮ ተዟዙሮ በሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ አድርጎ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ጋር ደረሰና ክብራቸውና ክብራችን በሚነካ መልኩ እያልን መወዛገብ ጀመርን:: ይህንን ስጽፍ እንኳ ውርደትና ፍርሃት እየተሰማኝ ነው:: አእመዲን አጥፍቻለሁ እንደማለት ይብስ በሁለት ክፍል አቡካካና የሙፍቲ ዑመርን ጥፋት ወደ መዘርዘር ገባ:: እንደውም ሐሳቡን አጠናከረና > ይለናል:: የሚልም አንቀጽ አምጥቶ የማያውቀውን ተፍሲር ይዘበዝብ ጀመር:: (ሸይኾች ጋር እንደዘመተ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ጋር ወስዶ ጣለው)::
ነቢዩ ﷺ የደነገጡት እኮ ጂብሪልን ከእነ ሙሉ ተፈጥሮው ለመጀመሪያ ጊዜ ስላዩት ነው:: ከ600 የጂብሪል ክንፎች ውስጥ ሁለቱ ብቻ አድማሱን ይሞላል:: ከእነ600 ክንፉ ሲያዩት ደነገጡ:: ጂብሪልን ከእነሙሉ ተፈጥሮው ቀርቶ የአላህ ቃል ሲመጣ ከክብደቱ ብዛት ብዙ ጊዜ ልባቸው ይመታል:: ያልባቸዋል:: እንደ ቀደምት ነቢያት ሕዝቦች የሳቸውም ሕዝብ እንዳይጠፋ ይፈራሉ:: የአላህ ቁርአን ሲተላለፍ ጂብሪልም ሌሎች መላእክትም እራሳቸውን እንደሚስቱ በሀዲስ ተነግሯል:: የእኛ ልብ የማይመታው እኮ ከድርቀታችን ብዛት ነው:: አንዳንድ በቁርአን የተመሰጥን ቀን ድንገት ሊመታ ይችላል::
ሌላው የሚለው ነቢ አደም, ነቢ ኑህ, ነቢ ኢብራሂም, ነቢ ሙሳ ብለውታል, እኛም ሙስሊሞቹ በየሶላቱ መግቢያ እንለዋለን:: ከዚህም በተጨማሪ ሶላት እየሰገድን ለአላህ ቆመን > እንላለን:: ለምን? ነገ እንዳንጠም እና አሁንም ቢሆን ከነበርንበት ቅናቻ ይበልጥ እንድንቃና ነው::
የመጀመሪያ ሙስሊም እንድንሆን የታዘዝነው ወይም የመጀመሪያ ሙስሊም አድርገኝ የምንለው በእስልምናቸው ውበት ቀዳማይ ወይም እስልምናቸው የተሟላና ጸአዳ ሙስሊሞች ጋር አድርገኝ ማለታችን ነው:: ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ የሙስሊሞቹ የመጀመሪያ ናቸው:: በእስልምና የሚቀድማቸው ነብይም ይሁን መላእክት የለም:: ከአፈጣጠርም አኳያ ከአደም ይቀድማሉ:: በእሳቸው ሲታይ አባታችን አደም የትናንት ሕጻን ነው:: ይህንን ትምህርት የምንማረው ውስጥ ነው:: ኢስላም, ኢማንና ኢሕሳን የሚባሉ ትምህርቶች አሉ:: ዝርዝር ውስጥ አልገባም::
ከሚያሳዝነው ሁሉ የሚያሳዝነው አንድን ተራ ግለሰብ ተሳስተሃል ከማለት ይልቅ የነቢያችን ﷺ ክብር ላይ የሚረማመዱና እስልምናቸውን የሚመዝኑና የሚተቹ መንጋዎቹ ሁኔታ ነው:: ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ በአካል ቢመጡ ኖሮ መንጋው ብሎ ከእርሱ ጎን መሰለፉና ነቢዩን ﷺ መዋጋቱ አይቀርም ያስብላል:: ይህ የፈተና ሰው በቀጣይ በአላህ ላይ ሳያከራክረን አይቀርም::
ጽሑፉን ሲቋጭ ከፖሊስ ሰልጣኞች ጋር ፎቶ ለጥፎልናል:: ማንም አይነካኝም ማለቱ ይመስላል:: እርሱ በጠራው ፈተና ብዙ ሰው ታሰረ, ተገረፈ, ሞተ:: ሙስሊሙ በዘር ተቧድኖ የሚጋደልበትን ቀን ይጠባበቃል:: ረመዷን, ዒድ እና ጁምዓ ሲደርስ ውሾቹ እንዲያጉዋሩ ጃስ ይላቸዋል:: መስጂድ ሁሉ ይረበሻል:: ረመዷን የመከራ ወር ሆኖ ያልፋል:: እንዲህ ያለ ፈታኝ በጽሑፍ እንጂ በአካል አናውቅም::
©Hasen Injamo