" የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቶሎ ተጠናቆ ወደ ሌሎች የልማት ስራዎች ፊታችን ልናዞር ይገባል ሲሉ " ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ አስታወቁ ።
ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 11 የአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ የግድቡ ገቢ አሰባሳቢ አባላት ዋንጫውን ይዘው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ቢሮ በመገኘት ድጋፍና ምርቃት ተቀብለዋል ።
ተቀዳሚ ሙፍቲ የህዳሴ ግድቡ የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠበት ዕለት ጀምሮ አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ በተለያየ መልኩ ትግል ያደረጉ ታላቅ ሰው ናቸው !
ባለፈው ዓመትም የውሃ ሙሌቱን ተከትሎ የግብፁ አህዛር ዩንቨርስቲ ኢማም ከሀሰት ወግነው በአባይ ጉዳይ ለሰጡት ተገቢ ያልሆነ መግለጫ አግባብ ያለውና ዕውነቱን የሚያፀና ምላሽ ለአልጀዚራ ፣ ለቢቢሲ ፣ ለስካይ ኒውስና ለCNN መግለጫ መስጠታቸው ይታወቃል ።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ከእውነት ጋር መቆም የዘወትር መርሃቸው ነው ።
©የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት!