ለሐጅ መንገደኞች !!
እስካሁን 1663 ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች መዲና ደርሰዋል ።
በመጅሊስ ታሪክ እጅግ ፈታኙ የሐጅ መስተንግዶ የዚህ ዓመቱ ነው ። አንደኛ ለሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር ለመንገደኞች የሚከፈለው 30 ሚሊዮን ዶላር አለመገኘቱ ሲሆን ፤ ሁለተኛው የመጅሊሱን ስልጣን በኃይል ለመንጠቅ የሚመኘው ቡድን የሚፈጥረው ውዥንብር ነው ።
ዑለሞችና የመጅሊሱ አመራር በኮቪድ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሐጅ ፀሎት ከተፈቀደ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ዶላር ለማግኘት የሚቻለውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱን በተደጋጋሚ ስናሳውቅ መቆየታችን ይታወሳል ።
አሁንም ቢሆን መጅሊሱ ለ3000 ሺ ሁጃጆች ቪዛ ማውረድ እንደሚችልና ለ1000 ሺ ደግሞ በተጠባባቂነት እንዲጠብቁ ደጋግመን ስናሳውቅ ሰንብተናል ። ከ4000 ሺ በላይ የተመዘገቡ ደግሞ ብራቸው በአስገቡበት ባንክ ተመላሽ እንዲደረግ ዑለማ ምክር ቤቱ ወስኗል ። ደጋግሞም መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል ፤ እንደ ተቋም እውነቱ ይሄ ነው ።
ነገር ግን የሐጅ እድል በጉዞ ወኪሎች የመገኘት እድሉ ካለ በሚል ተስፋ መጅሊሱ የሚሰጠውን ድጋፍ አድርጎ ሰው ሐጅ እንዲያደርግ እና እንዳይቀር በማሰብ እንዲመዘግቡ ለድርጅቶቹ ይሁንታ ሰጥቷቸዋል ።
ስራቸውንም ግቢ ውስጥ ቢሮ ሰጥቶ በቅርብ ርቀት ሆኖ እየተከታተላቸው እና እየደገፋቸው ይገኛል ። ሆኖም እስካሁን አንዳቸውም ለሳዑዲ ሐጅ ሚኒስቴር የሚላከውን ዶላር አላስገቡም ። ዛሬ ማታና ነገ ያስገባሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። የተወሰነ ሓጃጅም በጉዞ ወኪሎች በኩል ቢሄድ ለተቋሙ ትልቅ ስኬት ነው ። ይሄም ተጀምሯል ፤ ከሆነ እሰየው ፤ ካልሆነ ደግሞ የሀጃጁ ገንዘብ ያለው በመጅሊስ አካውንት ስለሆነ ወዲያውኑ ወደ ሀጃጁ አካውንት ተመላሽ ይደረጋል ። የሓጃጁ መሄዱ ነው እንጅ ገንዘብ መመለሱ ለመጅሊሱ አያስቸግረውም ፤ በቀናት ውስጥ ያልሄደው ሀጃጅ ብር በሙሉ መመለስ የሚያስችል አሰራር ባንኮቹ ዘርግተዋል ።
ሌላው ፤ ዛሬ መጅሊስ ግቢ ትላንት የተነሱት አይነት የዶላር ጥያቄና የጉዞ ወኪሎች ምዝገባ ፍጥነት ይኑረው የሚል የሀጃጅ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር ።
ይህንን ሰላማዊ ጥያቄ ወደ ረብሻ ለመቀየር ተዘጋጅተው የመጡ እና ሐጅ ለማድረግ ያልተመዘገቡ ግለሰቦች ነበሩ ። ልክ ጥያቄውን ወደ ፉጨትና ጩኸት ከቀየሩ በኋላ ፤ " መጅሊሱ በ24 ሰዓት ውስጥ ስልጣን ይልቀቅ ፤ Dawn Dawn መጅሊስ ፤ Dawn Dawn መጅሊስ ወደሚል ያረጀና ያፈጀ የረብሻ መስመር ሐጃጁን ለማስገባት ሞክረው ነበር ። ህዝቡም አጀንዳው ሌላ መሆኑ ሲገባው መልሶ ፀጥ አለ ። ወዲያው የግቢ ፀጥታ ሃይሎች ሲመጡ ረባሾቹ ፤ ሮጠው ለማምለጥ ሞክረዋል ፤ የተወሰኑት ተይዘዋል ። እውነቱ ይሄው ነው ። እውነትም የአላህ ነው ።
©የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት።