የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡
አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አነስ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦
" ሙስሊሞች ሻዕባን በገባ ጊዜ በሙስሕፎች(ቁርኣን) ላይ ይደፉ ነበር፤ የሚያነቡ ሲሆን፣ ከገንዘቦቻቸው ዘካም ያወጡ ነበር። ይህንንም ያደረጉ የነበረው ደካማውን እና ድሃውን ለረመዳን ጾም ለማበረታታት ነው።

(ለጣኢፉ አልመዓሪፍ፣ ገጽ 135)


የማይሰለች ድምፅ!
ሸይኽ ሙሐመድ አዩብ ረሂመሁላህ
ሱረቱ ጣሀ
1414 አ/ሂ ከተራዊህ ሰላት የተወሰደ


https://t.me/sultan_54


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


አላህ የተቀሩትን የሻዕባን ቀናቶች በረካ አድርጎልን ረመዳን ይዞት የሚመጣውን ኸይሮች ሁሉ ይምናገኝ ያድርገን!!




الشيخ محمد أيوب رحمه الله


ከአቡ መስዑድ አልአንሳሪይ ራዲየሏሁ ዓንሁ እንደተዘገበው።
ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሶላት ወቅት ሰሓቦች ትከሻ ይነካሉ፣ ቀጥ ብለው እንዲቆሙ እና እርስ በርስ እንዳይለያዩ ያዝዙ ነበር። ምክንያቱም በሰፍ ውስጥ ያለው ልዩነት በልቦች ውስጥ ልዩነት ያስከትላል። ከዚያም ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም፦
" ከእኔ ቀጥሎ ያለው ሰፍ አጠገብ ለመቆም ተገቢዎቹ ሰዎች የአእምሮና  የጥበብ ሰዎች ናቸው፣ ከዚያም ከነርሱ ቀጥሎ  ያለ ሰው ከዚያም ቀጥሎ ሰው ነው።" አሉ።

ከዚያም አቡ መስዑድ ራዲየሏሁ ዓንሁ በዘመናቸው ለነበሩ ሰዎች እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ዛሬ የበለጠ ልዩነት ያለባችሁ ናችሁ"፣ ይህም በነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘመን ሲነፃፀር በአቡ መስዑድ ዘመን ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት እንደተጨመረ ያሳያል።




ነቢያችን በሸዕባን ወር ለምን አብዝተው እንደሚጾሙ ሲጠየቁ፣ እንዲህ በማለት መለሱ።
«ያ በረጀብና በረመዳን መካከል ሰዎች የሚዘነጉበት ወር ሲሆን በውስጡም ለዓለማት ጌታ ሥራዎች ከፍ ብለው የሚወጡበት ወር ነው።»
አሕመድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል/አልባኒ ሐሠን ብለውታል


🔴 የዛሬው የጁምዓ ኹጥባ

🎙 خطبة الجمعة
شهر شعبان يغفل عنه الناس

❗️
ወርሃ ሸዕባን
ብዙሃኑ የሚዘናጋበት ወር!

🕌 ቃሊቲ ሀምዛ መስጂድ

🗓 ሸዕባን 01/1446 አ/ሂ

http://t.me/sultan_54


ሰላማ ኢብን ኩሀይል (አላህ ይዘንላቸውና)**
እንዲህ ይላሉ፡
" የሻዕባን ወር የቁርአን አንባቢዎች ወር ነው። " ይባል ነበር።"


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
شهر شعبان


በወርሃ ሸዕባን ምን እናድርግ?…
⚀ ጾም ማብዛት። ሰኞና ሀሙስ እና ሌላውንም መለማመድ። ለረመዳን መዘጋጀት።…
⚁ በቀደሙ ረመዳኖች ያመለጡንን ቀዷ ማውጣት።…
⚂ ከሰዎች ጋር እርቅ መፍጠር። ጥላቻና ቂምን መተው። የሰዎችን ሐቅ መመለስ። የረመዳንን በረከት ከሚያሳጡ መካከል መጥፎ ስነምግባር እና  የሰዎችን ሐቅ መጣስና በደል መፈፀም  ዋነኞቹ ናቸው።
:
«አላሁመ ባሪክ ለና ፊ ሸዕባን ወበሊግና ረመዳን።»




قال رسول الله ـﷺـ
« إذا أراد الله بعبده الخير عجّل له العقوبة في الدنيا وإذا أراد الله بعبده الشر أمسك عنه بذنبه حتى يوافي به يوم القيامة » خرّجه الترمذي وحسنه 》.
“አላህ ለባርያው መልካምን ሲሻለት በዱንያ ላይ እንዲቀጣ ቀደም ያደርግለታል። በባርያው ላይ ሸርን ሲፈልግ ግን በወንጀሉ እንዲቀጣበት የቂያማ እለት ድረስ ያቆየዋል።”


ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

«የቁርኣን ድምፅ፤ ያረጋጋል፣ ስክነትን ይሰጣል እና ነፍስ ከፍ እንድትል ያደርጋል።»

በዳዒኡ– አት-ተፍሲር (143/2)


የሥነ-ምግባር ትምህርት ከዕውቀት በፊት ነው!!

ዐብዱላህ ኢብኑ አል ሙባረክ እንዲህ ብለዋል፡-
"የሥነ-ምግባርን ትምህርት ለ30 ዓመታት ተማርኩ፣ ዒልምን ለ20 ዓመታት ተማርኩ፣ ሠለፎች የሥነ-ምግባርን ትምህርት ከዕውቀት በፊት ይማሩ ነበር።"

- አል-ጋያህ 446/1 | 📚


ኢብን ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡-** 

"…እናም ስንት ሰዎች ኃጢአት ይሠራሉ፣ ከዚያም ግን ኃጢአታቸውን አስታውሰው ኢስቲግፋር ያደርጉሉ፣ ከተውበታቸው በኋላም ከበፊቱ  የተሻለ እና የተቃና ህይወት ላይ ይሆናሉ።" 

አልቀውል ሙፊድ ―3/178



Показано 20 последних публикаций.