Репост из: Bahiru Teka
✅ ሰለፍዮች በትግላችሁ ቀጥሉ
የአላህ መሺኣ ነውና የሐቅና ባጢል ግብግብ እስከ ቂያማ ይቀጥላል ። በዚህም እውነተኛች በጫፍ ላይ ካሉት ይለያሉ ። ነገሮች ሲመቻቹ ሁሉም አማኝ ነው ሁሉም ሱና ወዳጅ ነው ነገር ግን በፈተና ጊዜ ነው እንክርዳዱ ከፍሬው የሚለየው ። የተወሰኑ የአላህ ባሮች እሳት ውስጥ ገብቶ እንደ ወጣ ወርቅ የዲኑ ጌጥ ሲሆኑ አብዛኞች ጎርፍ ያመጣው አረፋ ሆነው ዳር ይቀራሉ ።
የአላህ መልእክተኛ ፈተናን አስመልክተው ሲናገሩ ከኋላ የሚመጣው የፊተኛውን ቀላል ያደርገዋል ብለውናል ። አሁን እያየን ያለነው ይሄው ነው ። ድሮ የኢኽዋን አንጃ በነ ሓሚድ ሙሳ አማካይነት ወደ ሀገራችን ሳይገባ በፊት ሁሉም ወደ ተውሒድና ሱና ሲጣራ ሱፍዮች ካጠቃላይ የተውሒድ ሰዎች ጋር ነበር ትግላቸው ።
የሱናው ወጣት በኢኽዋን አስተሳሰብ መጠለፍ ሲጀምር ሰለፍይና ኢኽዋንይ ተብሎ ተከፈለ ። ሰለፍዮች ከሱፍይና ኢኽዋን ጋር ትግል ጀመሩ ። ብዙም ሳይቆይ ኢኽዋኖች ከሱፍዮች ጋር ተደመሩ በጋራ ሰለፍያን ለመጣል መስራት ጀመሩ ። ሰለፍዮች በጋራ የተከፈተባቸውን ትግል ተቋቁመው ወጣቱን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል አደረጉ ። ተሳክቶላቸው የጥምር ሀይሉን መቋቋም ቻሉ ።
በዚህ ሁኔታ እያሉ የአሕባሽ አስተሳሰብ መጥቶ መጅሊሱን ተቆጣጥሮ የአወሊያ ተማሪዮችን ሲያባርር ኢኽዋኖች አጋጣሚውን ተጠቅመው መድረኩን ይዘው ከጫፍ እስከ ጫፍ ፀረ አሕባሽ ንቅናቄ አካሄዱ ።
ከአሽባሽ ጋር የነበረው ፀብ የስልጣን እንጂ የዐቂዳ አልነበረም ። ለዚህ ማስረጃው ኢኽዋን ያደርገው በነበረው ሀገራዊ ሰልፍ መፈክሩ " አሽ ሻዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ " ( ህዝቡ መጅሊስን መጣል ይፈልጋል ) የሚል የነበረ መሆኑ ነው ። በዚህ ንቅናቄ ኢኽዋን ካገኘው ያልጠበቀው ትርፍ አብዛኛው ሱና ሲደግፍ የነበረው ወጣትና ባለሀብት ወደ ትግሉ መቀላቀሉና የሰለፍያን ዳዕዋ ሲመራ የነበረውን ናጂያን መኮነኑ ነበር ። ጊዜው አብዛኛዎች የናጂያ ዱዓቶች አገር ጥለው የተሰደዱበት ወቅት ነበርና ይህ ሁኔታ ዋና ዋና የናጂያ መሪዮች አቋማቸውን እነዲቀይሩ አደረጋቸው ።
የሰለፍያው ዳዕዋ በተለያዩ መሻኢኾችና ዱዓቶች አማካይነት ትግል እያደረገ የነበር ሲሆን በሚዲያው ላይ በነኢብሙነወርና ሳዳት አማካይነት ዳዕዋው መነቃቃት ጀመሮ ከፍተኛ ትግል ይደረግ ነበር ።
በዚህ ጊዜ ትግሉ በዋነኝነት ወደ ኢብኑ መስዑድ ከተዘዋወረው ናጂያ አመራሮች ጋር ነበር ። በዚህም የሰለፍያው ዳዕዋ ትግል ከኢኽዋኖችና ኢብኑ መስዑዶች ጋር ሆነ ። ትግሉ ቀጥሎ የሰለፍያው ዳዕዋ ወጣቱን መልሶ መቆጣጠርና ከተቃራኒዮቹ መዳፍ አብዛኛውን ማውጣት ቻለ ።
ይህ በንዲህ እያለ ስርአቱ ከኢሀዲግ ወደ ብልፅግና ሲሸጋገር የመደመር ስሌት አሕባሽን ፣ ሱፍይን ፣ ኢኽዋንና ወደ ነሲሓ የተዛወረው ኢብኑ መስዑድ ተቋም አመራሮች አንድ ሆነው ወደ መጅሊስ መጡ ። ይህን የድምር ውጤት ያዩት እነኢብኑ ሙነወር መደመሩ ነው የሚያዋጣው ብለው የጥምሩ የእንጀራ ልጆች ሆኑ ። ባለውለታ ለመሆንም ሰለፍዮችን ባለ በሌለ ሀይላቸው መዋጋት ጀመሩ ። እነ ኢብኑ ሙነወር በእስክሪብቶ የጥምሩ መጅሊስ አመራሮች በመሳሪያ አፈሙዝ የሰለፍያ ዳዕዋ መዋጋት ጀመሩ ።
የጥምሩ መጅሊስ አመራሮች ሰለፍዮችን ከዳዕዋው ሜዳ ለማስወጣት መስጂዶችን መረከብ የመጀመሪያው ተግባር አድርገው ያዙት ። ይህ አካሄድ የሰለፍዮችንም መስጂዶች ጭምር መረከብን ያካተተ ነው ። ለዚህ ደግሞ በሰለፍዮች መስጂዶች ላይ ሁከትና ረብሻ በመፍጠር ሰለፍዮች የፈጠሩት በማስመሰል ለጅምላ እስር መንገድ ይከፍታል ብለው ነው ። በአሁኑ ሰአት በስራ ላይ ያዋሉት በስልጤ ዞን ላይ ሲሆን እንደሞመከሪያ ነው እየሰሩት ያሉት ። ሰለፍዮች መርሳት የሌለባቸው ኢብኑ ሙነወር ላይደርሱላችሁ መስጂዳችሁን ያሰነጥቁዋችኋል ማለቱን ነው ። ‼ ይህ ማለት እስትራቴጂውን ያውቀው ነበርና ለመጅሊስ እጅ ስጡ ነበር መልእክቱ ።
ማስገንዘቢያ ለሰለፍዮች :–
ሰለፍዮች ይህን እስትራቴጂ ማስቆም የምትችሉት በዳዕዋ ላይ በመፅናት ነው ። የተዘጋጀላችሁን ወጥመድ ተጠንቀቁ በፍፁም ስሜታዊ እንዳትሆኑ ። ከመስጂድ ቢያስወጡዋችሁ ጊቢ ውስጥ ዳዕዋ አድርጉ, ልጆቻችሁን እቤትችሁ አስተምሩ, አንዱ ዳዒ ሲታሰር ሌላው ይቀጥል ፍፁም ዳዕዋ እንዳታቆሙ, እነርሱ ይሰሩ እናንተ ዳዕዋችሁን ቀጥሉ, ሀይለቃልም ከመጠቀም ተቆጠቡ አብዛኛው ማህበረሰብ እናንተ ዲን ለማጥፋት የመጣችሁ ተደርጎ ስለተሳለለት እዘኑለት ። ትግላችሁ አፈር የለበሰውን ሐቅ አፈሩን ጠርጋችሁ ለማሳየት መሆን አለበት ።
ከአላህ ጋር እውነተኛ ሁኑ አላህ እውነተኞች ይረዳልና አብሽሩ ። ፅናት የትግል ድልድይ ናት ። ትግሉን ለመሻገር ፅኑ ። ለዚህ በሶብር ፣ በኢኽላስና ዱዓእ ታገዙ ። የነብዩ ሱና መርከብ ነውና ከሱ እንዳትወርዱ በቢዳዓ ባሕር እንዳትሰጥሙ ተጠንቀቁ ። ሌላው በፍፁም ዳዕዋ ላናደርግ ብላችሁ እንዳትፈርሙ ያለ ፈቃድ ለሚሉዋችሁ የህገመንግስቱ ፈቃድ በቂያችን ነው በመጅሊስ ደብዳቤ ከተሻረና ዳዕዋ ማድረግ ወንጀል ከሆነ ቅጣቱን ለመቀበል ዝግጁ ነን በሉ ። በሱና መርከብ ላይ ለመሳፈር ቆራጥ መሆን ያስፈልጋል ቆራጥ ያልሆናችሁ አላህ ፊት እንዳታፍሩ ፀንታችሁ ታገሉ ።
አላህ ተውሒድና ሱናን የበላይ ለማድረግ ሰበብ ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka