👉 የጭቅጭቅ ርእስ አለማንሳት !!!
የአዲሶቹና የቀድሞ ኢኽዋኖችና እንዲሁም እንባ ጠባቂዎቻቸው የማስተኛ አዲስ ፋሽን በየመስጂዶቹና መድረሳዎች አጨቃጫቂ ርእሶች ማንሳት አያስፈልግም ሁሉም በጋራ ተስማምቶ ማስተማር አለበት የሚል ነው ። ‼
ይህ " መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ " እንደሚሉት የነሲሓዎች ኢኽዋኖችና አሕባሾች እንዲሁም ሱፍዮችን ከእግዲህ ተስኒፍ ( እገሌ እንዲህ ነው ) ማለት የለም የሚለውን የባጢል ስምምነት መሬት ላይ ለማውረድና ስራ ላይ ለማዋል የሚጠቀሙበት ስልት ነው ።
ለመሆኑ አጨቃጫቂ ርእስ የሚባሉት ምንድናቸው ? አጨቃጫቂ ርእስ የሚባሉት ሽርክን በዝርዝር ማስተማር ፣ ቢዳዓን በዝርዝር ማስተማርና የመሳሰሉት ናቸው ። ይህ ማለት ሽርክን በጥቅሉ ቢዳዓም በጥቅሉ ማስተማር ይቻላል ማለት ነው ።
↪️ ሽርክን በጥቅል ማስተማር ማለት አንድ ኡስታዝ ወይም ሸይኽ
« ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ حُرُمَاتِ اللَّهِ فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُ عِندَ رَبِّهِ ۗ وَأُحِلَّتْ لَكُمُ الْأَنْعَامُ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ ۖ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ »
الحج ( 30 )
(ነገሩ) ይህ ነው ፡፡ የአላህንም ሕግጋት የሚያከብር ሰው እርሱ ጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ ነው ፡፡ የቤት እንስሳትም (ግመል ከብት በግና ፍየል) በናንተ ላይ (እርም መሆኑ) ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች ፡፡ ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ ፡፡ "
« حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ »
الحج (31 )
" ለአላህ ታዛዦች በእርሱ የማታገሩ ሆናችሁ (ከሐሰት ራቁ) ፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ፤ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ፣ ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው ፡፡"
« إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا »
النساء ( 48 )
" አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል ፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ ፡፡"
እነዚህና የመሳሰሉ አንቀፆችን ቀርቶ ሽርክን ማውገዝ ይችላል ። ነገር ግን መሬት ላይ ያሉትን የሽርክ ተግባራትን መዘርዘር አይቻልል ። ‼
ለምሳሌ : – ያብሬት ፣ የቃጥባሬ ፣ ያልከሶ ፣ የዳና ፣ የከረም ፣ የጀማ ኑጉስ ፣ የሸኸና ሑሰይን ፣ ያባድርንና የመሳሰሉትን የሙታን ቀብሮችን በዙሪያቸው ጠዋፋ ማድረግ ፣ የቀብራቸውን አፈር በጥብጦ መጠጣት ፣ እርዱኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ እጄን ያዙኝ ፣ አክብሩኝ ፣ አሽሩኝ ፣ ጠብቁኝ ፣ ዘር ስጡኝ ማለትና የመሳሰሉት ተግባራትና ንግግሮች ከእስልምና የሚያወጡ ሽርኮች ናቸው ማለት አይፈቀድም ።
ምክንያቱም የጭቅጭቅ ርእስ ስለሆነኑ ‼ ሱብሓነላህ መቼ ነው ይህ ርእስ በሙስሊች መካከል የጭቅጭቅ ርእስ የሆነው ? ይህ ርእስ የጭቅጭቅ ርእስ የሚሆነው በሙስሊሞችና በሙሽሪኮች መካከል ነው ። ነገር ግን አዲሶቹ ኢኽዋኖችና እንባ ጠባቂዮቻቸው ከቀብር አምላኪ ሱፍይና አሕባሾች ጋር አንድ ነን ሲሉ የጭቅጭቅ ርእስ ሆነና በዚህ መልኩ ሽርክን በዝርዝር ማውገዝ አይቻልም ተባለ ። ‼
እንዲሁም ቢዳዓን የሚያወግዙ የተለያዩ የቁርኣን አንቀፆችን ለምሳሌ : —
« وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ »
الأنعام ( 153)
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
« إِنَّ الَّذِينَ فَرَّقُوا دِينَهُمْ وَكَانُوا شِيَعًا لَّسْتَ مِنْهُمْ فِي شَيْءٍ ۚ إِنَّمَا أَمْرُهُمْ إِلَى اللَّهِ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُوا يَفْعَلُونَ »
الأنعام ( 159 )
" እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም ፡፡ ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው ፡፡ ከዚያም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ ይነገራቸዋል ፡፡
የሚሉና ሌሎችም የተለያዩ የሐዲስ መረጃዎችን በጥቅሉ እየጠቀሰ ቢዳዓን ማውገዝ ይችላል ። ነገር ግን በናኢዮች ፣ ቁጥቢዮች ፣ ሱሩርዮች ፣ ሙመዪዓዎች ፣ ሱፍዮች ፣ ተብሊጞች ፣ አሕባሾች እያለ በዝርዝር የቢዳዓ አራማጆችን መጥቀስ አይችልም ። ‼ ምክንያቱም የጭቅጭቅ ርእስ ስለሆነ ።
እንዲሁም ቁርኣንን ፣ ሐዲስንና የቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶች ( ሰለፎች) በአንድ ድምፅ ያፀደቋቸውን መርሆችን የጣሱ የቢዳዓ ባልተቤቶችን በስም እየጠቀሱ ማስጠንቀቅ አይቻልም ።
ለምሳሌ : – የሀገራችን የቀድሞ የኢኽዋን መሪዮችን እንደ ዶ/ር ጀይላን ፣ ሙሐመድ ሓሚዲን ፣ ሓሚድ ሙሳ ፣ ካሚል ሸምሱ ፣ አቡበከር አሕመድ ፣ አሕመዲን ጀበል ፣ ራያ አባመንጫ ፣ በድሩ ሑሴንና የመሳሰሉት
የአዲሶቹ ኢኽዋን መሪዮች እንደ :– ኢልያስ አሕመድ ፣ ሳሊሕ አሕመድ ፣ አዩብ ደርባቸው ፣ ኢልያስ አወልና ቡሽራ የመሳሰሉት
የእነርሱ እንባ ጠባቂ የሆኑት እንደ ኢብኑ ሙነወርና ግብረአበሮቹ ስም አንስቶ ማስጠንቀቅ አይፈቀድም ። ምክንያቱ ደግሞ የጭቅጭቅ ርእስ ስለሆነ ።
የዚህ ተልቢስ ሽፋኑ አጨቃጫቂ ርእሶችን አለማንሳት የሚል ሲሆን በሰፊው ዘመቻ እየተደረገበት ይገኛል ። ከላይ እንዳልኩት በዚህ ሽፋን በተለይ ዩንቨርሲቲ አካባቢ ለየት ያለ ትኩረት ሰጥተውት እየሰሩበት ሲሆን አብዛኛው ጠንካራ ሰለፍይ የነበሩ ወጣቶች በዚህ ምክንያት ከአቋማቸው እንዲወርዱ ተደርጓል ።
ልክ እንደዚሁ ጠንካራ አቋም የነበራቸው ሰለፍይ ወጣቶች የነበሩባቸው መስጂዶችም ከምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዲቋረጡ ተደርገው ከቆዩ በኋላ ሰለፍዮች የሚወነጀሉባቸው ለሙብተዲዖች ጥብቅና የሚቆምባቸው ቦታዎች ተደርገዋል ።
በመሆኑም በምንም መልኩ ሰለፍዮች የትም ቦታ የጭቅጭቅ ርእስ አለማንሳት የሚል ማስተኛ እንዳይቀበሉ መጠንቀቅና ተመዩዝ ማድረግ ይኖርባቸዋል ።
አላህ ተውሒድና ሱናን ባለቤቶቹንም የበላይ አድርጎ እንዲሁም ሽርክና ቢዳዐን ባለቤቶቹንም የበታች ያድርግልን ።
https://t.me/bahruteka