የደብረ ማርቆሱ ጥቃት !
ህዳር 11 ቀን 2017 ዓም ኢትዮ 251 ሚዲያ። ሚዛን አስጠባቂዋ የንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ በደብረ ማርቆስ።
በዛሬው እለት ከቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ተወርዋሪ ንስር ኮማንዶ ጋር በመሆን ከለሊቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ለሊቱ 10:00 ሰዓት ድረስ በደብረ ማርቆስ ከውኃ ጋን እስከ የብራጌ በተደረገ የደፈጣ ውጊያ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂው የአድማ ብተና እና ሚኒሻ ኬላ ላይ የነበረ ሁሉ ተደምስሷል።
የብልፅግናው ጀኔራሉ ከዚህ በኋላ ደብረ ማርቆስ ላይ የጥይት ተኩስ አትሰሙም እያለ ሲቀልድ እንዳልነበረ ዛሬ ሌላ ታምር ተሰርቶበት አድሯል።
ከአማራ ህዝብ ጎን የቆሙ ከውስጥ ሆነውም የጠላትን ኃይል እንዲፈርስ ከፍተኛውን ስራ እየሰሩ ያሉ አድማ ብተና እና ፖሊስ በተሰጡት መረጃ መሰረት ፋኖ ስራውን ሰርቷል።
በዚህ የተደናበረው የጠላት ኃይል ከደብረ ማርቆስ ተነስቶ ንጉስ ተክለሐይማኖት ብርጌድን እይዛለሁ ጮቄንም እይዛለሁ ብሎ ከሳምንት በላይ የተንቀሳቀሰው የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ቡድን ከየቦቅላ፣ከቀይ አቦ እና ደብረዘይት ከባቢ ሲቀጠቀጥ መሰንበቱ ይታወቃል።
በመሆኑም ዛሬ ደብረ ማርቆስ ላይ በተሰራው ታምር ይሔ አራዊት ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ሁሉንም ቀጠና ለቆ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጉዞ በመጀመር ደብረ ማርቆስ ተያዘብኝ በማለት ይዞት የሔደውን ስንቅ እንኳ ሳይቋጥር በለሊት ደብረ ማርቅስ ገብቶ አድሯል ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።
የንጉሱ ልጆች እና ተወርዋሪ ንስር ኮማንዶዎች የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቀኝ እጅ መሆናቸውን ያሳዩበት የዛሬው ውጊያ የጠላትን ቅስም ሰብረውት አድረዋል።
ጠላት ዳግም ወደየቀበሌዎች ወጥቶ በሰላም መመለስ እንደማይችል የተመለከተበት፣እኛ ፋኖዎች ደግሞ ጠላት የመጨረሻ እስትንፋሱ የቀረ መሆኑንና ምንም አይነት እርባና ያለው ወታደር እንደሌለው ያረጋገጥንበት አዳር ነበር።
እንግዲህ ከቁይ፣ከየሰንበት፣ከደብረ ማርቆስ፣ከደብረ ዘይት ተሰባስቦ የቦቅላን ይዞ የነበረው ኃይል ፤ የየሰንበቱ በጀርቤው ከሁለት ቀን በፊት ሲቀጠቀጥ ተመልሶ ወደ ካምፑ ሉማሜ ሲገባ የደብረ ዘይቱ ደግሞ ቀኝ አቦ ላይ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ ከደብረ ማርቆስና ከቁይ የመጣው ደግሞ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደየመጣበት መገስገሱ ታምር ነው።
ፋኖ ይችላል፣የትኛውም ምድራዊ ኃይል የፋኖን በትር መሸከም አይችልም የምንለው ያለምክንያት አድለም ።
ያም ሆኖ ያ ከደብረ ማርቆስም ከደብረ ዘይትም ተንቀሳቅሶ የነበረው የጠላት ኃይል ጠቅልሎ ማርቆስ በለሊት ሲገባ፣ ከቁይ ወደ የቦቅላ መጥቶ የነበረው ኃይል ተመልሶ ቁይ መግባት አልችል ብሎ እየተቁለጨለጨ ይገኛል።
የደብረ ዘይትን ህዝብ በየቤቱ እየዞረ ሀብት ንብረታቸውን ሲያቃጥል የነበረ ወንበዴ አውዳሚ ቡድን ማርቆስ ላይ ያለው ቅሪት አካል መጎዳቱን በሰማ ጊዜ ከተኛበት ምሽግ ተነስቶ ማርቆስ ገባ።ገና አባይን ትሻገራለህ!!!
በማታው ምት እስካሁን የተረጋገጠ ስድስት (6 ) እስከመጨረሻው የተሸኘ ሁለት (2) የቆሰለ ነው ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ተናግሯል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነፃነት አንደበት !