የፋኖ ምላሽ በወጣቱ ግድያ ዙሪያ
በሰሜን ሸዋ ታርዶ በተገደለው ወጣት ዙሪያ ምላሽ የሰጠው ፋኖ ድርጊቱን ብልጽግና እንደፈጸመው አጋለጠ
በሞት አፋፍ ላይ ያለ ስርዓት የሚፈፅመውን አረመኔያዊ ድርጊት ህዝባችን አምርሮ ሊታገለው ይገባል ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡
የዐቢይ አሕመድ የጥፋት አገዛዝ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ ሲያሻው በተመሳሳይ ሰዓት ሲፈልግ ደግሞ በፈረቃ ጅምላ ግድያና እልቂትን እየፈፀመ ቀጥሏል ሲል ገልጿል አርበኛው፡፡
አገዛዙ የከፈተውን ጦርነት ማሸነፍና መቋቋም ሲያቅተው አንዱ ሌላውን የገደለ ለማስመሰል ሲቀሰቅስ፣ ንፁሃንን ሲገድልና በእሳት ጭምር ከነነፍሳቸው ሲያቃጥል አሳይቶናል ያለው አርበኛው ፣የአማራን ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ደም ለማቃባትና በጥርጣሬ እንዲተያይ ለማድረግ የሚፈጽማቸው ግፎች በቀጠሉበት በዚህ ወቅት በኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ አካባቢ አሰቃቂ ግድያዎች ተፈጽመዋል ብሏል፡፡ ይህንን ድርጊትም ፈፅሞ እናወግዛለን ያለ ሲሆን ይሄን ማውገዝ እንኳን እንደኛ ካለ በደል እና መገደል አንገሽግሾት ለነፃነት ከወጣ ታጋይ ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሚጠበቅ ነው ሲል አክሏል።
መሰል ግድያዎችን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎችም ሆነ በአማራ ክልል ሲፈጽም የሚታወቀውም ሆነ አሰቃቂ ጅምላ ጭፈጨፋዎችን ሲያካሂድ በዓለም ጭምር ሲወገዝ የነበረው የብልጽግናው አገዛዝ ወንድም ከሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ጋር ሕዝባችንን ለመነጠል በማሰብ ይህንን ነውረኛ ተግባር መፈፀሙን መጠራጠር አያስፈልግም በማለትም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም አለም አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ይህንን ነውረኛ ተግባርና አሰቃቂ ወንጀል እንዲመረምረው የጠየቀው አርበኛ አስረስ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችም አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ ሲል ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም የአገዛዙን ሴራ ተረድተዉ መሰል ድርጊቶችን እንዲያወግዙ እና በመሰል ሴረኛ መንገድ ሕዝቦችን ለማጫረስ የቆረጠውን አገዛዝ እንዲታገሉት ጥሪ አቅርቧል፡፡
እንዲህ ያሉ አሰቃቂ ግድያዎች የሚያቆሙበት፣ ኢትዮጵያዊያን በተለመደው ወንድማማችነታቸው የሚኖሩበት አገር ለመፍጠር የምንታገለው እኛ የፋኖ ኃይሎች ይህንን ድርጊት የምናወግዘውና በምንቆጣጠራቸው ግዛቶችም ሆነ በምንሰጣቸው ስምሪቶች መሰል ጥፋት እንዳይፈፀም አበክረን የምንጠነቀቅ መሆናችን ልብ ሊባል ይገባል ብሏል፡፡
በመጨረሻም በጭካኔና ነውረኛ መንገድ አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበት የኦሮሞ ወንድማችን እና ሌሎች በጥይት ተደብድበው ለሞቱት የኦሮሞ ወንድሞቻችን ቤተሰቦች ከልብ መጽናናትን እንመኛለን ብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጃል መሮ የሚመራው የኦነግ ሸኔ ቡድን ይህን የሰሜን ሸዋውን ግድያ የፈጸመው የእነ ሽመልስ ኮሬ ነጌኛ ነው የሚል ምላሽ መስጠቱ ተነግሯል፡፡
ሮሃ