ፋኖ ኢንጅነር ማንችሎት መስከረም 2015 ላይ በፌስቡክ ገጹ ካሰፈረው ጦማር ይህ ወቅታዊ ጉዳያችንን የሚዳስስ በመሆኑ ልናጋራችሁ ወደድን።
በፋኖነት መጽሐፍ ውስጥ!
በክፍል አንድ፣ በትረ ፋኖን ማን ይጨብጠው ለሚለው ጥያቄ ይህን ምላሽ ይሰጣል፡- ‹‹የአንበሳ ልብን የታደለ፤ ለዓመታት አላማ ጽናትን ያነገበ፤ በጥቅም የማይታለል፤ ወንዜነትና እኔነት የማያሸንፈው፤ ለህዝባችን እስከመቃብር ድረስ የታመነ ሰው ሊመራን ይገባል።›› ይላል።
በክፍል ሁለት ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት፡-
ማን ተብለን እንጠራ ሲባል ‹‹እንደ አንበሳ ክንድ ብርቱ፤ እንደ ነብር ቁጡ፤ እንደ ርግብ የዋህ በሆነው… በዚህም ባህርይ በሽተኛን ጠያቂ፤ የተጣላን አስታራቂ፤ የደከመን አነቃቂ፤ ‘እኔ ሳይሆን እኛ’ በሚል ክንድ ብርቱ የዓላማ ሰው፤ ቁሞ ከሚሸነፍ ሙቶ ማሸነፍን የስነልቦናው መሰረት ያደረገ የአሸናፊነት ምልክት፤ በሞትና ሕይወት መካከል በሚደረግ ብርቱ ትግል በሚገኝ ወርቃማ ስም ‘ፋኖ’ ተብለን እንጠራ።›› በማለት ይመልሳል።
የአባት ልጅ መሆን ያለውን ጠቀሜታ ካስረዳ በኋላም፣ ፋኖ በፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ተሳትፎም አልተሳትፎም፣ የፋኖ ህብረት እንዲጠነክር ከሚያግዘው በላይ እንዲፈርስ የሚያምሰው ቁጥር ቀላል አይደለም በማለት፣ ‘ከሆዳም አማራዎች ጋር የሚደረገው ትግል’ ግብግቡ እንደሚፈትን ያሳስባል። በየትኛውም መልኩ ቢሆን ሹመኞች ጋር የሚለጠፍና ፖለቲከኞች አላማቸውን በኃይል የሚያስፈጽሙበት ተንበርካኪ ፋኖ ግን በጭራሽ ሊኖር አይገባም ሲል ፋኖንም ያሳስባል።
የጠራ አላማ ለማይሞት ትግል ሲልም፣ የአማራ ፋኖ እነዚህን አላማዎች አንግቦ መታገል አለበት በማለት ይመክራል። እነሱም፡-
• የአማራ ህዝብ ርስት፤ ታሪክ፤ እሴትና ባህል መጠበቅ
• በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኝ ሁሉም አማራ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር፤ በቋንቋና ባህሉ እንዲጠቀም ማስቻል
• የህዝብ ስልጣን ማገልገያ እንጂ መገልገያነቱ እንዲያከትም ማድረግ
• ‘እኔ ለሀገሬና ህዝቤ ምን ሰራሁ?’ የሚለውን ጥያቄ ‘ለሀገር ይሰጣል እንጂ ከሀገር አይወሰድም’ ብሎ በተግባር መመለስ
• በክፉ ጊዜ ወታደር፤ በደህና ጊዜ አርሶ አደር መሆን
• ዘወትር ከተገፉት ጎን መቆም
• አማራ ጠላትነትና በርካታ እንክርዳዶች የተሞሉበት ሕገ መንግስት እንዲቀየር ማስገደድ
• ውስጣዊ አንድነቱ የጠነከረ አማራን መፍጠር
• በአድካሚው የትግል ጉዞ ውስጥ በጎ የሰሩትን ማመስገን
እነዚህን አላማዎች ለማሳካት በሚደረግ ትግል ውስጥ የሚገጥም መሰናክል ካለም፣ ‹በመስዋዕትነት እናልፈዋለን እንጂ ወደኋላ መመለስ የሚባል ነገር ጨርሶ አይታሰብም› በማለት ፋኖ በትግል ሂደቱ ተተኪ የለሽ ሚና እንዳለው ያስገነዝባል።
ባህርያችንና ጠላታችን በሚለው ርዕስ ውስጥም እንዲህ በማለት ያስረዳል፡- ፋኖ ሊጠላቸው የሚገባቸው መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ፡-
• ሴረኝነት፤ ተንኮልና ባንዳነት
• አድሏዊነት
• ሌብነት ወይም ሙሰኝነት
• እብሪት ወይም ዘፈቀዳዊ የሆነ የኃይል አማራጭ
ናቸው።
ስለ ባህርይ ሲያስረዳም፣ ፋኖ ሊኖረው ስለሚገባ ባህሪዎች እነዚህ ናቸው፡-
• ሐቀኝነት
• ከራስ በላይ ለሆነ አላማ መኖር
• መዥገር ነቃይነት
• ህዝባዊነት
• ወታደርነትና አሸናፊነት
ናቸው በማለት ትውልዱ የመዳኛ መንገዱን በመሆን እንዲጀምር ያሳስባል።
በዚሁ ክፍል ‘እንታጠቅ ወይስ እንፍታ?’ ለሚለው መሰረታዊ ጥያቄም፣ ‹‹ለምን ወደዚህች ምድር መጣሁ? በዙሪያዬ ምን እየተካሄደ ነው? እኔ ምን ማድረግ አለብኝ? ትናንትን በምን መልኩ ልረዳው? ዛሬን እንዴት ልኑረው? ነገን እንዴት ልጠብቀው? ይህ ህዝብስ ምን ዓይነት ከበባ ውስጥ ነው?›› የሚሉትን ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የሀሳብና ቁስ ነፍጥን መታጠቅ እንጂ መፍታት አያስፈልግም በማለት በአጽንኦት ያሳስባል። በዚህ ክፍል መጨረሻም በላይ ዘለቀ፤ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስና ጎቤ መልኬ ‘የፋኖ የትግል አባት’ አድርጎ መነሳት ያስፈልጋል ሲል ክፍል ሁለትን ይዘጋዋል።
በየትኛውም የፖለቲካም ሆነ ሲቪክ አደረጃጀት ያላችሁ አማራዎች፣ ይህ መጽሐፍ ‘ለአንድ ህዝብ እስከታገልን ድረስ ተመሳሳይ አላማና ግብ እንዲኖረን ስለሚያደርግ’ ብታነቡት እመክራለሁ።
ታጋይ አምሓራ
18/3/2017 ዓ.ም

ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!
18/3/2017 ዓ.ም