የዳኝነት-ክፍያ-ደንብ (1).pdf
የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ ፀደቀ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ ደንብ አጽድቋል።
ደንቡ በጸደቀበት ወቅት የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጸገነት መንግስቱ እንደተናገሩት የዳኝነት አከፋፈል ሥርዓቱን ለማዘመን፣ ሥርዓቱም አጭር፣ ቀልጣፋና ለከፋዩ ያመቸ እንዲሆን ለማስቻል ሕጉን ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ።
የፌደራል ፍርድ ቤቶች እስከ አሁን ድረስ ሲጠቀሙበት የነበረው የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል የህግ ክፍል ማስታወቂያ ደንብ በ1945 ዓ.ም የወጣና ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ በደንቡ ያልተሸፈኑ በርካታ ጉዳዮች በመኖራቸው ወቅቱን ያገናዘበ የዳኝነት ክፍያን መወሰኛ ደንብ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በተጨማሪም የፌደራል ፍርድ ቤቶች አሁን ከደረሱበት ወቅታዊ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃና ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር ተመጣጣኝ የሆነ የዳኝነት ክፍያ ለማስከፈል የሚያስችል ሕግ በማስፈለጉ ደንቡ ተዘጋጅቷል።
ደንቡ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቂ ውይይት የተደረገበትና የሀገር ውስጥን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባትና የሌሎች ሀገራትንም ልምድ ታይቶ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
@samuelgirma
🌐 https://SamuelGirma.com
📱 https://fb.me/tebekasamuel
📱 https://t.me/tebekasamuel
ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
📻 0911-190-299
🔗 t.me/tebekasamuel
🔗 t.me/tebekasamuel
Join us on 👇
👉 @ethiopian_law
👉 @tebeka
#Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #ጠበቃ #law