በጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል ቴሌኮሙኒኬሽን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች የተመራ ልኡክ የኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገኘውን የኤክስፒሪየንስ ማዕከላችንን ጎበኙ፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የሥራ ኃላፊዎች የኩባንያችንን ረዥም የቴክኖሎጂ ጉዞን ጨምሮ ዘመኑ እስከደረሰበት ስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ማዕድን ልማት፣ ስማርት ቱሪዝም የመሳሰሉት የዲጂታል ሶሉሽኖች ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
ልኡካኑ ኢትዮ ቴሌኮም ለዲጂታል ሶሉሽኖች የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት እና የገነባውን ግዙፍ የመሰረተ ልማት አቅም በእጅጉ በማድነቅ ኢትዮ ቴሌኮም ለብዙ የአፍሪካ ኦፕሬተሮች አርዓያ መሆን እንደሚችል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አክለውም የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ ፈጠራን በማጎልበት እና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን በማሳደግ በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ጉልህ አሻራውን ለማሳረፍ የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኩባንያችን ከሀገር አቀፍ ባለፈ የአፍሪካን ዲጂታል የትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ በመጫወት ላይ ያለውን ሚና በማድነቅ የኢትዮ ቴሌኮም አመራር ለሁለገብ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት መረጋገጥ በሚያሳየው ቁርጠኝነት መደነቃቸውን ገልጸዋል፡፡
ለጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ልዑካን በኩባንያችን ለነበራቸው ፍሬያማ ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#RealizingDigitalAfrica #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #Ethiotelecom #DjiboutiTelecom #Sudatel