#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) ከሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ብቃትና ችሎታ ያላቸው ምሩቃንን በማፍራት ሂደት ውስጥ ተጠያቂነትን ከማስፈን ባለፈ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ስምምነቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አመራር እንዲከተሉ፣ አገሪቱ ለምታወጣው ሀብት ተመጣጣኝ ውጤት እንዲያስገኙ፣ የአፈጻጸም አቅማቸው እንዲገመገምና ለስኬቱም ዕውቅና እና ሽልማት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በስምምነቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብላቸው በጀት ባስመዘገቡት ውጤት ልክ እንደሚሆን" ገለፀዋል።
የስምምነት ውሉ በየዩኒቨርሲቲዎቹ ስር ወደሚገኙ ኮሌጆች፣ ትምህርት ክፍሎች እና ሌሎች ፅህፈት ቤቶች በየደረጃው እንደሚወርድ ይጠበቃል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete