🔊 #የሠራተኞችድምፅ
“ ያለፈቃዳችን ከአመት ደመወዛችን 100% እየተቆረጠብን ነው። ወዴት እንጩህ ? ” - ሠራተኞች
በምዕራብ አርሲ ዞን ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ያሉ ጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች “አመራሮች ደመወዛችንን እንደፈለጉ ነው የሚቆርጡት። ለምን? ብሎ መጠየቅም አይቻልም” ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ምሬታቸውን አሰምተዋል።
“‘የቀበሌ ቤት መስሪያ’ በሚል ያለፈቃዳችን ከአመት ደመወዛችን 100% እየተቆረጠብን ነው" ያሉት ስሞታ አቅራቢዎቹ፣ "ወዴት እንጩህ?” ሲሉ ጠይቀዋል።
“ለቀበሌ ቤት መስሪያ" እንዲሁም "ለቡሳ ጎኖፋ” በሚል ደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው እንደሚቆረጥ፣ የዲቲ ክፍያ በወቅቱ እንደማይከፈላቸው፣ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያም እንዳልተፈጸመላቸው አስረድተዋል።
“ዝም ብለው ነው የሚቆርጡብን ፈቃዳችንንም እንኳ አይጠይቁንም” ያሉ ሲሆን፣ የኑሮ ውድነቱን ተቋቁመው ቤተሰብ ማስዳደር ስላልቻሉ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።
ሠራተኞች ስላማረራቸው ጉዳይ ምን አሉ?
“ ከደመወዛችን እንደፈለጉ ነው የሚቆርጡት። ያለ ማንም ፍላጎት ሰሞኑን 100% ከደመወዛችን ቆርጠዋል። ደመወዙ የሚቆረጠው ለፈረሙትም ላልፈረሙትም ነው።
በአመት 100% በደመወዝ ስኬል ነው የሚቆረጠው። ይህ በወር ከ500 እስከ 800 ሊሆን ይችላል። እንደዬ ስኬሉ መጠኑ ይለያያል። በዚህ ወር ደመወዛችን ተቆርጧል።
የዱዩቲ ክፍያም የአሁኑ ዘግይቷል። ሌላው የሦስት ወራት የዱቲ ክፍያ አልተፈጸመልንም ገና እየጠበቅን ነው። ፋይናንስ ነው ያልከፈለን። ፎርሙ ፋይናንስ ጋ ደርሷል።
የሁለት ወራት አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ አልተከፈለንም። ደመወዛችንን አናውቅም የማይቆረጥ የለም። ዝም ብለው ነው የሚቆርጡት ያለምንም ፈቃድ። እኛን አይጠይቁንም። እንደፈለጉ ነው የሚያደርጉን። ሠራተኛም አይጠይቅም።
ገንዘባችን በብዛት እየተቆረጠ ያለው ‘የቀበሌ ቤት መስሪያ’ ተብሎ ነው። ከዚህም በፊት ያለፍላጎታችን ይቆርጡ ነበር። የትም አቤት ቢባል መልስ አይገኝም።
ይህ ድርጊት የሚፈጸመው እኛ ወረዳ ብቻ እንጂ ሌላ ወረዳ ላይ አልሰማንም ደመወዝ እየቆረጡ ያሉት ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለቅሬታው ምላሽ ለማካተት ከክልል፣ ዞን እንዲሁም ወረዳ ባለስልጣናት ለቀናት ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ምላሽ አልተገኘም። ሆኖም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች ከሆኑ በድጋሚ ጥረት ያደርጋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA