#አብክመ_ጤና_ቢሮ_ከሙስና_ጋር_የቆረበ_ተቋም!!
ይህ አንድ ቀን እንኳን ከፍትህ ጋር ተያይቶ የማያውቅ የሙሰኞች መናኸሪያ ቢሮ በቅጥር፣ በዝውውር፣ በትምህርት እድል የሚያደርገውን ብልሹ አሰራር ዛሬም በዚህ ነውረኝነቱ እንደቀጠለ ነው። ተቋሙን በውርስ የተረከቡት ይመስል ሁሉም ነገር በዘመድ አዝማድ፣ በገንዘብ፣ በማማገጥም ጭምር መሆኑ ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች ግልጽ ነው።
ሰሞኑንም ለ MNC technical advisor የኮንትራት ቅጥር ጉዳይም ይሄው ነው የሆነው። ለውጥ ይፈልጉ ይመስል ማስታወቂያውን ለሁሉም ግልጽ አድርገው አወጡ። ይሁን እንጂ በእከከኝ ልከክልህ ገብተው እንደ አሻንጉሊት ተጎልተው አበል ሲያወራርዱ የሚውሉ ጡረተኞች ለምን ወጣ ብለው አካኪ ዘራፍ አሉ። ያም ሆኖ ጥሩ ጥሩ ሰዎች ተመዝግበው የፈተና ቀን መጠባበቅ ከጀመሩ አንድ ወር በኋላ ምልመላው ቢታወቅም እነ አጅሬ ሊያልፉ ይችላሉ ብለው ያሰቧቸውን ተመዘጋቢዎች ተቀባይነት በሌለው አኳኋን ከውድድር ውጭ አድርገዋቸዋል።
ከውድድር ውጪ ከተደረጉ ተመዝጋቢዎች መካከልም በዘርፉ ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት (associate professors, PhD) እና ልምድ ያላቸው የዩንቨርሲቲ መምህራን፣ ስፔሻሊስት ሀኪሞች፣ program ላይ ሲሰሩ የቆዩ ባለሙያዎች እንዲሁም ልዩ ፍላጎቶች ይገኙበታል።
በደረሰን መረጃ መሠረትም ይህ እንዲሆን ያደረገው እዛው እናቶች እና ህጻናት ላይ የምትሰራን የስራ ባልደረባ ለማስገባት እድሏን ለማስፋት እንደሆነ ማወቅ ችለናል። ይህን መረጃ የሰሙ የ UNICEF ሰዎች ምልመላው ከእንደገና እንዲደረግ የተናገሩ ቢሆንም እስካሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።
እባካችሁ ተቋሙን ሀቅም ያለው ሰውም ይግባበት!