#FightCOVID19
ባደጉት ሀገራት ሳይቀር የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመዋጋት እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ። በርካታ ዶክተሮች ሕይወታቸው አልፏል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ናቸው።
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ቁጥር ምናልባትም የመመርመር አቅማችን እንዲሁም ከቫይረሱ ተጠቂዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች አፈላልጎ የማግኘቱ ስራ ከተጠናከረ በእጅጉ ከፍ ሊል ይችላል።
ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ኮሮናን በመዋጋት ከፊት ለፊት ለሚሰለፉት የጤና ባለሞያዎች ግብዓቶችን ከማማላት አንጻር ልዩ ትኩረት ሊሠጥ ይገባል። በመከላከያ ቁሳቁስ ዕጥረት ምክንያት ብዙ ዋጋ እንዳንከፍልም እንሠጋለን።
በሌሎቻችን ዘንድ ግን ይህ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] አሁንም መድሃኒት ያልተገኘለት ፣ በየዕለቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀጥፍ፣ ብዙ ሺዎችን ሆስፒታል እያስተኛ የሚገኝ አደገኛ በሽታ መኾኑን አውቀን ሳንዘናጋ ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል። የጤና ባለሙያዎችን ምክር መሥማትም ይበጃል!
መልካም ምሽት!
TIKVAH-ETH