የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ተቋቋመ!
ታዋቂውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ ተወዳጁ አርቲስት ዘለቀ ገሠሠ ፣ ወጣቱ ባለሃብት አቶ ሀብታሙ አዱኛ፣ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ፓዝዮን ቸርነት እና አካዳሚሽያን ዶ/ር መስከረም ለችሳን ያካተተ የበጎፈቃደኞች ቡድን ተቋቋመ።
ቡድኑ ቅዳሜ ረፋድ ላይ በሐርመኒ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው አሳሳቢው የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን ከገባ ጊዜ ጀምሮ መንግስት እያደረገ ያለውን እንቅስቅሴ በዘርፈ ብዙ በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በማገዝ ወገኖቻችንን ከበሽታው ለመታደግ አቅዶ ያለማንም ጎትጓች በበጎ ፈቃድ የተቋቋመ ነው።
"ሰው ነኝ!" ለ ሰው እደርሳለሁ ያሉት የሰበዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ፤ ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎችን አቅዶ የተነሳው ይህ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን በተለያዩ መንገዶች ማህበረሰቡ ስለ በሽታው አስከፊነት አውቆ እንዲጠነቀቅ በማድረግ፣ በዚህ በሽታ ምክንያት የገቢ ምንጭ ለተቋረጠባቸው ወገኖቻችን የገንዘብና የቁሳቁስ ማሰባሰብ ተግባራትን ለማከናዎን እና በማህበራዊ ሚድያ የሚለቀቁ ሀሰተኛና አወዛጋቢ መረጃዎችን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ለማረጋጋት በማሰብ ስራውን በይፋ ጀምሯል።
የዚህ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን አባላት በቀጣይም መንግስትን ለማገዝ በቅርበት እንደሚሰሩ ያስታወቁ ሲሆን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የህክምና ባለሙያዎች፣ በጎፈቃደኛ ወጣቶች፣ ባለሀብቶች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ሁሉም ተባባሪ አካላት አብረዋቸው እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።
አርቲስት ዘለቀ ገሠሠ በንግግሩ ከዛሬ ጀምሮ በሙያዬ ህብረተሰቡን ለማንቃት እሰራለሁ ፤ ሁሉም በሙያው ወታደር ሆኖ ወገኑን ለመታደግ ዘብ መቆም አለበት ያለ ሲሆን ወጣቱ ባለሀብት አቶ ሀብታሙ አዱኛ በበኩሉ የህክምና ባለሙያዎቻችን እንዲሁም የአገር መከላከያ ሰራዊትና የደህንነት አካላት በወረርሽኙ ከተጠቁ የአገራችንም ሉዓላዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፤ ቶሎ መንቃት አለብን ብሏል።
የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ፓዚዮን ቸርነት ይሄን ክፉ ወረርሽኝ በመታገል ወገኖቻችንን የምናግዝበት የውዴታ ግዴታ ወቅት በመሆኑ በቴክኖሎጂው ዘርፍ መንግስትን ለማገዝ በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል። የዚህ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን አባል እና የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ በበኩሉ "ሳይቃጠል በቅጠል!" ሁላችንም "የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች ነን!" በየተሰማራንበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ቀድመን ነቅተን ህብረተሰቡንም በማንቃት ይሄን ክፉ ጊዜ በጥበብ እንለፈው ብሏል።
ዶ/ር መስከረም ለችሳም እንዲሁ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደየቤተሰቦቻቸው የተመለሱ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለእራሳቸውም ተጠንቅቀው የየአካባቢያቸውን ህብረተሰብ ማንቃት ይገባቸዋል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዝግጅቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የእድር ሊቀ መናብርትና የጎሳ መሪዎች የተገኙ ሲሆን በእያካባቢያቸው ይሄን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
....
ፎቶ፤ Photo sisay guzay ፎቶ ሲሳይ ጉዛይ
(Solitary Movement For A New Ethiopia)
#SMNE