የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ተቋቋመ!
(ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ)
ታዋቂውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ፣ ተወዳጁ አርቲስት ዘለቀ ገሠሠ፣ ወጣቱ ባለሐብት አቶ ሐብታሙ አዱኛ፣ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ፓዝዮን ቸርነት እና አካዳሚሽያን ዶ/ር መስከረም ለችሳን ያካተተ የበጎ-ፈቃደኞች ቡድን ተቋቋመ።
ቡድኑ ቅዳሜ ረፋድ ላይ በሐርመኒ ሆቴል በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው አሳሳቢው የኮሮና ቫይረስ (COVID19) ወደ ሀገራችን ከገባ ጊዜ ጀምሮ መንግሥት እያደረገ ያለውን እንቅስቅሴ በዘርፈ-ብዙ በጎ-ፈቃድ አገልግሎቶች በማገዝ ወገኖቻችንን ከበሽታው ለመታደግ አቅዶ ያለማንም ጎትጓች በበጎ-ፈቃድ የተቋቋመ ነው።
"ሰው ነኝ!" ለሰው እደርሳለሁ ያሉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቴ፥ ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎችን ዓቅዶ የተነሳው ይኽ የበጎ-ፈቃደኞች ቡድን በተለያዩ መንገዶች ማኅበረሰቡ ስለ በሽታው አስከፊነት አውቆ እንዲጠነቀቅ በማድረግ፣ በዚህ በሽታ ምክንያት የገቢ ምንጭ ለተቋረጠባቸው ወገኖቻችን የገንዘብና የቁሳቁስ ማሰባሰብ ተግባራትን ለማከናዎን እና በማኅበራዊ 'ሚድያ' የሚለቀቁ ሐሰተኛና አወዛጋቢ መረጃዎችን በማጋለጥ ኅብረተሰቡን ለማረጋጋት በማሰብ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።
የዚኽ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ዓባላት በቀጣይም መንግሥትን ለማገዝ በቅርበት እንደሚሠሩ ያስታወቁ ሲኾን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሕክምና ባለሙያዎች፣ በጎ-ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ባለሐብቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ኹሉም ተባባሪ አካላት አብረዋቸው እንዲሠሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።
አርቲስት ዘለቀ ገሠሠ በንግግሩ "ከዛሬ ጀምሮ በሙያዬ ኅብረተሰቡን ለማንቃት እሠራለሁ፤ ኹሉም በሙያው ወታደር ሆኖ ወገኑን ለመታደግ ዘብ መቆም አለበት" ያለ ሲኾን ወጣቱ ባለሐብት አቶ ሐብታሙ አዱኛ በበኩሉ "የሕክምና ባለሙያዎቻችን እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊትና የደኅንነት አካላት በወረርሽኙ ከተጠቁ የአገራችንም ሉዓላዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፤ ቶሎ መንቃት አለብን" ብሏል።
የቴክኖሎጂ ባለሙያው አቶ ፓዚዮን ቸርነት "ይኼን ክፉ ወረርሽኝ በመታገል ወገኖቻችንን የምናግዝበት የውዴታ ግዴታ ወቅት በመኾኑ በቴክኖሎጂው ዘርፍ መንግሥትን ለማገዝ በመሥራት ላይ እንገኛለን" ብለዋል።
የዚኽ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ዓባል እና የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ጋዜጠኛ ማናዬ እውነቱ በበኩሉ "'ሳይቃጠል በቅጠል!'፤ 'ኹላችንም የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች ነን!' በየተሠማራንበት የሙያ ዘርፍ ኹሉ ቀድመን ነቅተን ኅብረተሰቡንም በማንቃት ይኼን ክፉ ጊዜ በጥበብ እንለፈው" ብሏል።
ዶ/ር መስከረም ለችሳም እንዲሁ "በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደየቤተሰቦቻቸው የተመለሱ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለራሳቸውም ተጠንቅቀው የየአካባቢያቸውን ኅብረተሰብ ማንቃት ይገባቸዋል" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዝግጅቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የዕድር ሊቀ-መናብርትና የጎሣ መሪዎች የተገኙ ሲኾን በያካባቢያቸው ይኼን የበጎ-ፈቃድ አገልግሎት ለመሥጠት ቃል ገብተዋል።
....
ፎቶ፦ ሲሣይ ጉዛይ
(Solitary Movement For A New Ethiopia)
#SMNE
@tenamereja
@shegye
Comments- https://www.facebook.com/1643743282507188/posts/2615687255312781/?app=fbl