"የ25ቱ የነቢያት ታሪክ መግቢያ ክፍል 1"
👉የነቢያት ማንነትና አስተምህሮአቸው
☑️በነቢያትና ሩሱሎች ማመን ከስድስቱ የኢማን ማእዘናት (አርካኑል ኢማን) መካከል እራሱን የቻለ አንድ ማእዘን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው የነቢያትንና የሩሱሎችን ነቢይነት አሞኖ ካልተቀበለ ትክክለኛ አማኝ ለባል አይችልም። የሚመደበውም ከከሀዲዎች ጎራ ነው፡፡ ምክንያቱም፡- ነቢያትን የነቢይነት ማእረግ ሰጥቶ ወደ ሕዝባቸው የሚልካቸው ፈጣሪ አምላክ የሆነው አላህ በመሆኑ፡ እነሱነ አለመቀበልና በነሱ አለማመን፡ የላካቸውን አላህ አለማክበርና በሱም አምላክነት አለማመን ማለት ነውና፡፡ መልክተኛን የሚንቅና የማያከብር ሰው፡ ለላኪው ጥሩ ግምትና መልካም አስተሳሰብ የሌለው ብቻ ነው፡፡ አላህን አክብሮ አለመገኘት ደግሞ ትልቅ ክህደት ነው፡፡ ነቢያት ሰዎችን ከጌታ አላህ ጋር የሚያስተዋውቁ፡ እሱ ያዘዘውንና የከለከለውን ነገር ያላንዳች ጭማሬና ቅነሳ በአግባቡ በማድረስ፡ በቃል በማብራራትና በተግባርም ሰርቶ በማሳየት መልካም አርአያ በመሆን፡ በአላህና በባሪያው መሀል ያሉ አገናኝ ድልድይ ናቸው፡፡ ትክክለኛ እምነትና ክህደት የሚታወቀውም በነዚሁ ነቢያት ባስተማሩት የእምነትና የህግ ሚዛን በመሆኑ፡ የነቢያትን መልክት አለመቀል ግለሰቡን ከአማኞች ጎራ አውጥቶ ወደ ከሀዲያን ቡድን ይጨምረዋል ማለት ነው። ይህ በመሆኑም ስለነቢያት ማንነትና አስተምህሮ የተወሰኑ መሰረታዊ ነገራትን መማር ይገባናል ማለት ነው።
👉የታሪኩ ባለቤት፡
- ስለ ነቢያት ማንነት መማርና መናገር ስንጀምር፡ እንዲህ የሚል አንድ ፍትሐዊ ጥያቄ ሊቀርብልን ይችላል፦ በነቢያት ዘመን በህይወት ነበራችሁን? ካልነበራችሁስ የነቢያትን ታሪክ የምትናገሩት ከምን ምንጭ ተነስታችሁ ነው? የሚል፡፡ የኛ ምላሽም፦ ስለ ነቢያት በልበ-ሙሉነት የምንናገረው ዓለማትን ከመፍጠሩ በፊት የነበረውና የነቢያት አምላክ የሆነው ሕያው አምላክ አላህ በመለኮታዊ ቃሉ “ቅዱስ ቁርኣን'' እና በነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንደበት በ”ሐዲሥ” ላይ ስለነገረን ነው፡፡ ከጌታ አላህ ይልቅ እውነት ተናጋሪ ፈጽሞ የስም ሊኖርም አይችልም፡፡ ከነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላም እውነትን ነጋሪና መካሪም አይታሰብም፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል- " اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا " سورة النساء 87 “አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?” (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡87)፡፡ " وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا " سورة النساء 122 ز
👉“እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሠሩ፣ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸወነ ገነቶች ዘላለሞ በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ እናገባዋቸዋለን፤ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንንገርሞ ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?” (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡122)። ይህ በመሆኑም፡ የአላህ ቃል የሆነው ቅዱስ ቁርኣን ስለ ነቢያት መሰረታዊ ነገራትን በመተረክ ቁም-ነገር ያስጨብጠናል ማለት ነው፡፡ نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ الْقَصَصِ بِمَا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ هَذَا الْقُرْآنَ وَإِنْ كُنْتَ مِنْ قَبْلِهِ لَمِنَ الْغَافِلِينَ " سورة يوسف 3 “እኛ ይህንን ቁርአን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሀለን እነሆ ከርሱ በፊት (ካለፋት ህዝቦች ታሪክ) በእርግጥ ከዘን2ዎቹ ነበርክ” (ሱረቱ ዩሱፍ 12፡3)። " طسم * تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ الْمُبِينِ * نَتْلُو عَلَيْكَ مِنْ نَبَا مُوسَى وَفِرْعَوْنَ بِالْحَقِّ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ " سورة القصص 1-3 “ጣ.ሰን ሚም ይህች ገላጭ ከሆነው መጽሐፍ አነቀጽ ናት ከሙሳና ከፈርኦን ዜና እውነተኞች ስንሆን ለሚያምኑ ህዝቦች ባንተ ላይ እናነባለን” (ሱረቱል-ቀሶስ 28፡1-3)። " كَذَلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنْبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ وَقَدْ آتَيْنَاكَ مِنْ لَدُنَّا ذِكْرًا " سورة طه 99 כ
👉“እንደዚሁ በእርግጥ ካስፋት ወሬዎች በአንተ ላይ እንተርካለን ከኛም ዘንድ ቁርአንን በእርግጥ ሰጠንህ” (ሱረቱ ጣሀ 20፡99): ነቢይነት የአላህ መስኮታዊ ምርጫ እንጂ የሥራ ውጤት አይደለም፡- ሌላው ልናውቅ የሚገባን ነገር፡ ነቢይነት በዘር፣ በቋንቋ፣ በጉልበትና በሕዝብ ምርጫ የሚከናወን አይደለም፡፡ ነቢይነት የአላህ ፈቃድ ብቻ የታከለበት አሞላካዊ ምርጫ ነው፡፡ ሕዝቦች ባሕሪውን ስለወደዱለት ነቢይ የሚሆን፡ ስለጠሉት ደግሞ ከምርጫው የሚቀር የለም፡፡ አላህ በራሱ መለኮታዊ ዕውቀትና ፍጹማዊ ጥበቡ የሚፈልገውን ለነቢይነት ይመርጣል፡፡ ያ የተመረጠው ነቢይ እንኳ፡ ‹ቆይ እስኪ ኣስብበት› የሚል ዕድል የለውም፡፡ በአላህ መለኮታዊ አሰራር ውስጥ፡ ፍጥረታዊ ሀሳብ ድርሻ የለውምና፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፦ " مَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَلَا الْمُشْرِكِينَ أَنْ يُنَزِّلَ عَلَيْكُمْ مِنْ خَيْرٍ مِنْ رَبِّكُمْ وَاللَّهُ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ " سورة البقرة 105 “እነዚያ ከመጽሐፍ ባለቤቶችና ከአጋሪዎቹም የካዱት በናንተ ላይ ከጌታችሁ የሆነ መልካም ነገር መወረዳን አይወዱም አላህም በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል አላህም የተላቅ ችሮታ ባለቤት ነው” (ሱረቱል-በቀራህ 2፡105)።
" يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ " سورة آل عمران 74 “በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው'' (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡74)። " اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بصير " سورة الحج 75 “አላህ ከመላእክት ውስጥ መስክተኞችን ይመርጣል ከሰዎችም (እንደዚሁ) አላህ ሰሚ ተመልካች ነው'' (ሱረቱል-ሐጅ 22፡75)፡
አ/መጅድ ከድር አቡሁዘይፍ 15/05/2017