🌍ተውሂድና ሱና ✍


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ቁርአንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ለመረዳት የሚያስችሉ ተውሂድ፣ሲራ አጠር አጠር ያሉ የነብዩ ﷺ ሓዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።ቻናሉን ይቀላቀሉ ኪታቦችን ይቅሩ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ረመዳን ቀን 6

ረሱል (ሰለላህ አለይህ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦

﴿فَصْلُ مَا بَيْنَ صِيَامِنَا وَصِيَامِ أَهْلِ الْكِتَابِ أَكْلَةُ السَّحَرِ﴾

“በእኛ ፆምና በአህለል ኪታቦች ፆም መካከል ያለው ልዩነት ሱሑር መብላት ነው።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1096


“ወላሂ ቀብር ላይ ያሉ ሰዎች ተመኙ ቢባሉ አንዲትን የረመዳን ቀን ይመኙ ነበር”

ኢብኑል ጀውዚ


ረመዳን ጋር የሚያያዙ ለማስረጃነት ብቁ ያልሆኑ በነብዩ ﷺ ስም ሊወሩ የማይገባቸው ደካማ (ዶዒፍ) ሐዲሦች”
~
1. “የረመዳን ወር መጀመሪያው እዝነት ነው፡፡ መካከሉ ምህረት ነው፡፡ መጨረሻው ደግሞ ከእሳት ነፃ መውጫ ነው፡፡” ሐዲሡ ደካማ እንደሆነ የገለፁ የሐዲሥ ሊቃውንት[አዶዒፋህ፡ 2/262]
2. “ፁሙ ጤናማ ትሆናላችሁ፡፡” [አድዶዒፋህ፡ 1/420]
3. “ከረመዳን አንድ ቀን ያለ ምክንያት ወይም ያለ ህመም ያፈጠረ አመት ቢፆም እንኳን አይተካውም፡፡” [ዶዒፉ ሱነኑ ቲርሚዚ፡ 1/626]
4. “ጌታዬ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን፡፡ ረመዳንንም አድርሰን፡፡” [ዶዒፉልጃሚዕ፡ 4395]
5. “ጌታዬ ሆይ ላንተ ፆምኩኝ፡፡ በሪዝቅህም አፈጠርኩኝ፡፡” [ዶዒፉልጃሚዕ፡ 4349]
6. “ለአላህ በእያንዳንዱ ፊጥራ ጊዜ ላይ ከእሳት ነፃ የሚወጡ አሉት፡፡” [አዶዒፋህ፡ 2/262]
ረመዳን በገባ ቁጥር በየመሳጂዱ ስለሚደጋገሙ ምናልባትም ለደረሰው መማሪያ ይሆን ዘንድ ሼር እናድርግ ባረከላሁ ፊኩም፡፡
IbnuMunewor


📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
⏰#አልዓርቢዓዐ 0⃣5⃣ #ረመዳን 1⃣4⃣4⃣6⃣ ሂ


ረመዳን ቀን 5️⃣

ከኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ አንሁ) ተይዞ፡ እንዲህ ይላሉ፦

﴿كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَجْوَدَ النَّاسِ بِالْخَيْرِ، وَكَانَ أَجْوَدُ مَا يَكُونُ فِي رَمَضَانَ حِينَ يَلْقَاهُ جِبْرِيلُ،﴾

“ነቢዩ (ﷺ) ከሰዎች መልካምን በመቸር አቻ አልነበራቸዉም። በተለይ በረመዳን ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ቸርነታቸው እጅግ ይጨምራል። ጅብሪል በየረመዳኑ እየመጣ ቁርአንን ይማማሩ ነበር።”

ቡኻሪ (1902) ሙስሊም (2308) ዘግበውታል


የረመዳን ጥያቄ 3. ፆመኛ ሲያፈጥር ሁለት ደስታዎች አሉት።
Опрос
  •   ሀ)ፆመኛ ሲያፈጥር
  •   ለ)ፆመኛ ጌታውን ሲገናኝ
  •   ሐ)ለይልል ሲሰግድ
  •   መ)ሀ እና ለ
47 голосов


ፆም #የማያበላሹ ነገሮች
~
ቀጥሎ የተዘረዘሩት ፆም አያጠፉም / አያስፈቱም።

1- መድሃኒት በመርፌ መወጋት (ለምሳሌ ኢንሱሊን)፣
2- ምግብ መቅመስ (ሆን ተብሎ ከተዋጠ ፆም ያጠፋል)፣
3- የአይን ጠብታ፣ ኩል መክኳል፣ የጆሮ ጠብታ፣
4- አካልን ለማቀዝቀዝ መታጠብ፣
5- የሽቶ ወይም የበኹር ሽታ፣
6- መፋቂያ በማንኛውም ሰዓት መጠቀም፣
7- ዋገምት/ሒጃማ (ሚዛን በሚደፋ አቋም ፆም አያበላሽም)፣
8- ማስታወክ ወይም ማስመለስ (ሚዛን በሚደፋ አቋም ፆም አያበላሽም።)
9- ለምርመራ ደም መስጠት፣ ደም መለገስ፣
10- በፊንጢጣ / በፈጋራ በኩል የሚገባ መድሃኒት፣
11- ዝንብ፣ አቧራ ፣ ... ድንገት መግባት፣
12- ምራቅን መዋጥ፣
13- የአስም ህመምተኞች በአፍንጫ የሚጠቀሙት Sprayer
14- ለምርመራ ወይም ለሌላ በብልት ወይም በፈንጢጣ የሚገቡ ነገሮች፣ ካቲተር፣ ሉፕ፣
15- የማደንዘዣ መድሃኒቶች፣ ኦክስጂን፣
16- በአፍ የሚገቡ እንደ ኢንዶስኮፒ ያሉ መመርመሪያዎች (ፈሳሽ ወይም ሌላ ነገር ይዘው የሚገቡ ካልሆኑ)
17- ጆሮ ማሳጠብ፣ ጥርስ ማስነቀል፣ ጥርስ ማሳጠብ (በፆም ወቅት ባይደረግ የተሻለ ነው)፣
18- ፆም የሚያበላሹ ነገሮችን ተገዶ መፈፀም

እነዚህ ነገሮች በሙሉ ፆም አያበላሹም። ከተለያዩ መረጃዎች የተሰበሰቡ ናቸው።

IbnuMunewor


ረመዳን ቀን  3️⃣

ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا ، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ، وَمَنْ قَامَ لَيْلَةَ الْقَدْرِ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا، غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ﴾

“የረመዳንን ፆም ግዴታ መሆኑን አውቆ (በኢማን)
ምንዳም አገኝበታለሁ ብሎ (በኢሕቲሳብ) የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ሁሉ ይማርለታል። የለይለተል ቀድርን በኢማንና ከአላህ አጅር በመፈለግ የቆመ ከዚህ በፊት የሰራው ወንጀል በሙሉ ይማርለታል።”
ቡኻሪ (2014) ሙስሊም (760) ዘግበውታል


ረመዳን ጥያቄ 2.አንድ ሙስሊም በረመዷን ዱዓ ለማድረግ የተሻለው ጊዜ የትኛው ነው?
Опрос
  •   ሀ)ከኢፍጣር በሃላ
  •   ለ)ከፈጅር በፊት
  •   ሐ)በቀኑ ክፈለ ጊዜ
  •   መ)በሌሊት
29 голосов


👉አንድ ሰው የዊትር ሰላት እንደ ጨረሰ ሶስት ጊዜ"ሱበሃነል መሊኪል ቁዱሱ"ማለት አለበት
"የአላህ መልእክተኛም ይሉት ነበር


የአላህ መልዕክተኛ 〽️🤍〽️ የዊትር ሰላትን በጨረሱ ግዜ ሶስት ግዜ እንዲህ ይሉ ነበር


🅰〽️ አልሃምዱ ሊላህ
[ اَلحَمدُ لِلهِ ]



🅰️〽️ ሱብሃነል መሊኪል ቁዱስ
【سُبْحَانَ المَلِكِ القُدُّوسِ】



🅰️〽️ ላ ሃውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ
【لاَحَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ】



ምርጫውን በመንካት ትክክል መሆናቹን አረጋግጡ

ትክክል ከሆናቹ ▫️Add ˢᵘⁿᵃʰ ʷᵃᵛᵉ ▫️የሚል ይመጣላቹሃል 🎴


ረመዳን ቀን 2️⃣
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿ثلاثٌ من أخلاقِ النُّبوةِ: تَعجيلُ الإفطارِ، وتأخيرُ السُّحورَ، ووضْعُ اليمينِ على الشِّمالِ في الصلاةِ

“ሶስት ነገሮች የነቢያት ባህሪ (መገለጫ) ነው። ፍጡሩን አቻኩሎ መመገብ፣ ሱህርን አዘግይቶ መመገብና በሶላት ግዜ ቀኝ እጅን በግራ እጅ ላይ አድርጎ በደረት ላይ ማስቀመጥ።”
ሶሂህ አልጃሚ: 3038


1.ረመዳንን የተመለከቱ ጥያቄ መልሶች፣ በሐዲሥ መሰረት አንድ ሰው ሲየፈጥር ምን  ማለት አለበት? "
Опрос
  •   ሀ)አልሀምዱሊላህ
  •   ለ)ቢስሚላህ
  •   ሐ)አላሁ አክበር
  •   መ) “ዘሃበ ዘመዑ ወብተለቲል ዑሩቁ ወሰበተል አጅሩ ኢንሻ አሏህ
2 голосов


እነዚህ አራት ዱአዎች በፍፁም እንዳትረሳ። ሀፍዘህ ባገኘዃው አጋጣሚ ተጠቀማቸው።


"ረመዳን የዱአ ወር ነው ፣ዱአ ስታረጉ ያዘል ጀላሊ ወልኢክራም የሚለውን አብዙ


👉"በሰላም ፁመን ውለን ሰግደን አፈጠርን።ስንትና ስንት በህመም የሚሰቀዩና ፆሙን ፆምኩ በሉበት ወደ አኬራ የሄዱ አሉ እኛ አልሀምዱሊላህ እንበል።


አንድ ሰው ሲያፈጥር የሚለው ዱአ


ፆም የሚያበላሹ ነገሮች
~
1- የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም፣
2- የዘር ፈሳሽን ሆን ብሎ ማውጣት፣
3- መብላትና መጠጣት፣
4- በአፍ መድሃኒት መዋጥ፣
5- ሲጋራና መሰል ነገሮችን ማጨስ፣
6- የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መምጣት፣
7- ፆምን የማቋረጥ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ (ባይበላም ባይጠጣም)

እነዚህ ነገሮችን ፆምን የሚያበላሹት የሚያፈርሱ እንደሆነ እያወቀ፣ አስታውሶ እና በምርጫው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከፈፀማቸው ነው።
* የሚያፈርሱ መሆናቸውን ሳያውቅ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም። ልክ እንደዚሁ ያልነጋ መስሎት ወይም ፀሐይ የገባ መስሎት ቢፈፅምም ፆሙ አይበላሻም።
* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እያወቀ ነገር ግን ረስቶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።
* የሚያፈርሱ መሆናቸውን እየወቀ ግን ተገዶ ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም።


➻ አዲስ ሙሓዶራ ከገጠር

🔷ርእስ ▻ በተውሂድ እና በኢስላም ላይ መፅናት።

🎙በወንድም አቡ ሹራ አህመድ ካሳየ

🕌በአልብኮ ወረዳ ሶባ ና ጀብል ቀበሌ ሶባ ቢላል መስጅድ የተደረገ
      🔗https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid


👉ሱሁር ብሉ📢📣📣📣
የሱሁር (የሌሊት ምግብ)፡- ሱሁር መብላት የዚህችን ኡማ የፆም ሥርዓት ካለፉት ህዝቦች የሚለይ ሲሆን በውስጡ ብዙ ኸይር ነገር ይዟል፤

👉ይህንንም ነቢያችን (ሦለላሁ አለይህ ወሰለም) እንዲህ በማለት ገልፀውልናል፡- “በኛና በመጽሐፍት ባልተቤቶች ፆም መካከል ያለው ልዩነት ሱሁር መብላት ነው” (ሙስሊም ዘግበውታል)። በሌላ ቡኻሪና ሙስሊም በተስማሙበት ሐዲስ ነቢያችን (ሦለላሁ አለይህ ወሰለም)
تسحروا فإن في السحور بركة
“ሱሁር ብሉ፤ ስሁር መብላት በረካ አለውና” ሲሉ ተናግረዋል (ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)።

Показано 20 последних публикаций.