እድለኞች ነን አላህን ልናመሰግን ይገባል!!
ጠለሓ ኢብን ዑበይደላህ ረድየላሁ ዐንሁ እንዳስተላለፉት:-
« ሁለት ሰዎች ወደ መልክተኛው ﷺ ይመጡና በተመሳሳይ ሰዓት ኢስላምን ይቀበላሉ ።
አንደኛው ዒባዳ ላይ በጣም ብርቱ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ፤ እናም አንድ ቀን ጅሃድ ላይ ይገደልና ይሞታል ፤ አንደኛው እርሱ ሌላኛው ከሞተ ከአንድ ዓመት በኋላ ያርፋል ።
ጠላሃ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፦
" አንድ ቀን በህልሜ ከነዚህ ሁለት ሰዎች ጋር በር ጀነት በር ላይ ቆሜ ነበር ፤ አንድ ነገር ከበሩ ይወጣና ከመጀመሪያው ሟች ቀጥሎ የሞተውን ሰው ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ድጋሚ ይመጣና መጀመሪያ የሞተውን ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ወደኔ ዞር ብሎ 'አንተ ሂድ ተመለስ ያንተ ጊዜ ገና ነው' ይለኛል" ::
ጠለሃ ከዕንቅልፉ እንደተነሳ ስላየው ህልም ለሰዎች ይነግራቸውና ሰዎቹም ይገረማሉ ፤ እናም ይህ ወሬ መልክተኛው ﷺ ጋር ይደርሳል ፤
እሳቸውም ፦ ሰዎቹን "ምንድ ነው ያስደነቃቹ?" ብለው ይጠይቃሉ። ሰዎቹም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ከነዚህ ሁለቱ ሰዎች አንደኛው ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ሸሂድ ሆኗልም ነገር ግን ቅድሚያ ጀነትን እንዲገባ የተደረገው ቀጥሎ የሞተው ነው።" አሏቸው
የአላህ መልክተኛም ﷺ " ቀድሞ ጀነትን የገባው ሰው ከመጀመሪያው አንድን ዓመት በሕይወት አልቆየምን?"
ሰዎቹም አዎን ሲሉ መለሱ። የአላህ መልክተኛም ﷺ "#ረመዳንን
አላገኘምን ?
#አልፆመምን? ፤ ይሄንና ይሄን ያክል ሰላት
አልሰገደምን ?"
ሰዎቹም "አዎን" አሉ ።
የአላህ መልክተኛም ﷺ :- " ታዲያ በርሱና በዛኛው ሰውዬ መካከል የሰማይና የምድር ያክል በላይ ልዩነት አለ" አሏቸው:: »
_
ኢብን ማጃህ (2/345, 346) ፤ ሸኽ አልባኒ በሲልሲላ አ'ሰሂሃ ሰሂህ ብለውታል ዘግበውታል
አድራሻችን ቴሌግራም
channel👉🏿@tewihd
Group👉🏿@tewihddd