🫴እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር April 22 2012 ማንችስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን 75,522 ደጋፊዎች በታደሙበት ኦልድትራፎርድ ስታድየም ላይ ዩናይትድ ሻምፒዮን ለመሆን ፣የዴቪድ ሞይሱ ኤቨርተን ደግሞ የቀድሞ የማህበረሰብ ዋንጫ የአሁኑ Conference league ለመሳተፍ ይጫወታል።ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቋሚ 11 ተጨዋቻቸውን ዴቪድ ዴሂያ ፣ሪዮ ፈርዲናንድ ፣ጆኒ ኢቫንስ ፣ራፋይል ዳሲልቫ ፣ፓትሪክ ኤቭራ ፣አንቶኒዮ ቫለንሲያ ፣ፖል ስኮልስ ፣ማይክል ካሪክ ፣ዋይን ማርክ ሩኒ ፣ሊዊስ ናኒ እና ዳኒ ሜንሳህ ኒኪታህ ዌልቤክ ሲጠቀሙ ፡ሪያን ጊግስ ፣ሀቪየር ሄርናንዴዝ ፣አሽሊ ያንግ እና ፓርክ ተቀያሪ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል።የዴቪድ ሞይስ ቋሚ 11 ቲም ሀዋርድ ፣ቶኒ ሂበርት ፣ፒል ጃክየካ ፣ሲልቪኔ ደስቲን ፣ፊል ኔቭል ፣ጆኒ ሄይቲንጋ [የአርኔ ስሎት ረዳት አሰልጣኝ ] ፣ሊዮን ኦስማን ፣ዳኒ ጊብሰን ፣ማርዋን ፌላኒ ፣ስቴቨን ፒናር እና ኒኪካ ጄላቪችን አሰልፈዋል! ቲም ካሂል ፣ሮዝ ባርክሌ እና ቪክተር አኒቼቤ ቤንች አስቀምጠዋል።ጨዋታውን ሚካኤል ጆንስ ይመሩታል።
✍️ በ33ተኛው ደቂቃ ላይ ኒኪካ ጄላቪች የግንባር ኳስ አስቆጥሮ ኤቨርተን ቀዳሚ ሆነ።ዋይን ማርክ ሩኒ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀሩት ዩናይትድን አቻ አደረገ !የመጀመሪያው አጋማሽ 1-1 ተጠናቆ ወደመልበሻ ክፍል አመሩ።ከእረፍት መልስ ዳኒ ሜንሳህ ኒኪታህ ዌልቤክ በ57ተኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ ዩናይትድን ቀዳሚ አደረገ !በሶስት ደቂቃዎች ልዩነት ልዊስ ናኒ ጨዋታውን ወደ 3-1 ወሰደው።ማርዋን ፌላኒ ኤቨርተን ወደ ጨዋታው የምትመልሰውን ኳስ በግንባር አስቆጥሮ ጨዋታው 3-2 ቀጠለ።ዋይን ማርክ ሩኒ ለራሱ ሁለተኛውን ጎል ለዩናይትድ አራተኛውን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው ያለቀ መሰለ!ጨዋታው ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃዎች ሲቀሩት ዴቪድ ሞይስ አጥቂያቸውን አውስትራሊያዊው ቲም ካሂል ከወንበር እንዲነሳ አደረጉ! ኤቨርተን በ83ተኛው ደቂቃ ላይ ጄላቪች ጨዋታው ላይ ነፍስ የዘራች ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 4-3 ሆነ! የዩናይትድ ተከላካዮች መረጋጋት አልቻሉም ! 85ተኛው ደቂቃ ላይ ስቴቨን ፒናር አራተኛውን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 4-4 ተጠናቀቀ !ግዙፉ ኦልድትራፎርድ ፀጥ ረጭ አለ !ዩናይትድ እና ኤቨርተን ካደረጓቸው ጨዋታዎች ሁሉ ይህ ጨዋታ ሁሌም በቀዳሚነት ይነሳል። በዛው አመት ኤቨርተን የአሁኑን ኮንፈረንስ ሊግ የቀድሞውን የማህበረሰብ ዋንጫ ሲቀላቀል ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲ ኢቲሀድ ላይ በተአምር ኪዊን ፓርክ ሬንጀርስን በተጨማሪ ደቂቃዎች ላይ አከታትሎ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች 3-2 አሸንፎ ከ44 አመት በኋላ ሻምፒዮን ሲሆን ፡ዩናይትድ በእኩል ነጥብ በ8 የጎል ልዩነት ተበልጦ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቀቀ !ዴቪድ ሞይስ ከአመት በኋላ በአገራቸው ሰው ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጥቆማ ኦልድትራፎርድ ደረሱ ! ዴቪድ ሞይስ የዩናይትድ ወንበር ሰፍቷቸው ብዙም ሳይቆዩ ተሰናበቱ! ሞይስ ከ12 አመት በኋላ በኤቨርተን ቤት ሆነው በጉዲሰን ፓርክ ለመጨረሻ ጊዜ ዩናይትድን ቅዳሜ 9:30 ይገጥማሉ።
https://t.me/Capybara_Store_VPN_bot?start=_tgr_bc1e8xQ5NDVk